Newsletter Signup

Sign-up to stay in touch with Saint George FC

Reagent/Protectorator
Yidnekatchew Tessema
Mengistu Worku

St. George Gallery

የቅዱስ ጊዮርጊስ 80ኛ አመት የምስረታ በዓል

የቅዱስ ጊዮርጊስ 80ኛ አመት የምስረታ በዓል በድምቀት ይከበራል ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2008 ዓ.ም ከተመሰረተ 80ኛ አመት ይሞላዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የተመሰረተው በ1928 ዓ.ም አራዳ (ፒያሣ) አካባቢ ይኖሩ በነበሩ ወጣቶች ነበር፡፡ እግር ኳስ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ብዙም ባለተለመደበት ዘመን ይኖሩ የነበሩት እነዚህ ወጣቶች ጣልያን ባወጣው የዘር ቀለም ልዩነት ህግ ምክንያት አንድ ኢትዮጵያዊ ክለብ ለመመሰረት ይነሳሳሉ፡፡ በ1928 ዓ.ም አካባቢ ኢትዮጵያ ውስጥ ቡድን አቋቁመው እግር ኳስን ይጫወቱ የነበሩት የአርመን፣ የግሪክ፣ የእንግሊዝ እና የጣሊያን ማህበረሰብ አባላት ነበሩ፡፡ በዚያን ወቅት አራዳ ቀበሌ አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ የሚኖሩት አየለ አትናሼ እና ጆርጅ ዱካስ ከውጭ ማህበረሰብ ቡድኖች ጋር መጫወት ቢፈልጉም ጣሊያን ባወጣው ጥቁር ከነጭ ጋር አብሮ መጫወት አይችልም በሚለው ህግ ምክንያት አብረው መጫወት እንደማይችሉ ተነገራቸው፡፡ ጆርጅ አርመናዊ ሲሆን አየለ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነው ሁለቱ አብሮ አደጐችም ከብዙ ውይይት እና ትግል በኋላ አንድ ኢትዮጵያዊ ክለብ ለማቋቋም ስምምነት ላይ ደረሱ፡፡ ስሙንም ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚል ስያሜ ሰጡት፡፡ ከላይ የጠቀስነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የአመሰራረት ቁንጽል ታሪክ ነው፡፡ ያኔ የተመሰረተው ቅዱስ ጊዮርጊስ አመታትን በደስታና በችግር አሳልፎ ብዙ ውድድሮችን አሸንፎ ዘንድሮ 78ኛ አመቱ ላይ ይገኛል፡፡ በቅዳሜው የሚሊየነም አዳራሽ ፕሮግራማችን ላይም የክለባችን ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረ መስቀል ለ8ዐኛ አመት አከባበር ቅድመ ዝግጅት የሚረዳን ዝክረ ተግባር ተዘጋጅቶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ስራ አመራር ቦርድ የፀደቀ ሲሆን ደጋፊውም ክለቡ በሚያቀርባቸው የኮሚቴ እና ንዑስ ኮሜቴ ውስጥ በመሳተፍ በዓሉን ስኬታማ ያደርግ ዘንድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ ከአቶ አብነት ገብረ መስቀል በመቀጠል የ80ኛ አመት ክብረ በዓል ቅድመ ዝግጅት ዝክረ ተግባር ያቀረቡት አቶ ሰለሞን በቀለ ናቸው፡፡ አቶ ሰለሞን በተሰጣቸው አጭር ደቂቃ ሙሉውን ዝክረ ተግባር ማቅረብ ባይችሉም ዋና ዋና ሃሳቦቹን እና በበዓሉ ላይ ሊዘጋጅ የታሰበውን ዋና ዋና ተግባራትን አቅርበዋል፡፡ 1- አለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ በ8ዐኛ አመት ክብረ በአሉ ላይ እንዲቀርብ የታቀደው ዝግጅት አለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ነው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ባሳለፋቸው ዘመናት ከተለያዩ የአፍሪካ አና የአውሮፓውያን ቡድኖች ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አድርጓል፡፡ በዚህ መሰረትም ለቅዱስ ጊዮርጊስ 8ዐኛ አመት ክብረ በዓል የአፍሪካና የአውሮፓ ክለቦች የሚሳተፉበት ኢንተርናሽናል የወዳጅነት ጨዋታ ይካሄዳል፡፡ 2. ቋሚ የገቢ ምንጭ መፍጠር የ8ዐኛ አመት ክብረ በዓል ማድመቂያ የሚሆነው ለክለቡ መተዳደሪያ የሚሆን ቋሚ የገቢ ምንጭ መፍጠር ሲሆን ይህንንም ለማሳካት የተለያዩ ኮሜቴዎች ተቋቁመው በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡ 3. ሲምፖዚየም እና ጥናታዊ ፅሁፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲመሰረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አልተመሰረተም ነበር፡፡ ፌዴሬሽኑን በ1949 ዓ.ም ያቋቋሙትን እና እንዲቋቋም ሃሣቡን ያቀረቡት ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ናቸው፡፡ በዚህ ሰማንያኛ አመት ክብረ በዓል ላይም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከምስረታው ጀምሮ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ምን አበረከተ የሚሉና ሌሎች ርዕሶች ላይ ጥናቶች ተጠንተው በሲምፖዚየም መልክ የሚቀርብ ይህናል፡፡ 4. የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ማዕከል ይመረቃል ቅዱስ ጊዮርጊስ በደብረዘይት ከተማ እያስገነባው የሚገኘው የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ማዕከል በመጪው መስከረም ወር ስራውን ይጀምራል፡፡ ከ80ኛ አመት የምስረታ በዓላችን ጋር ተያይዞም የሚመረቅ ይሆናል፡፡

5. የአርበኞች ቀን ይኖረናል ከላይ እንደጠቀስንላችሁ የቅዱስ ጊዮርጊስ የአመሰራረት ታሪክ በራሱ ከአርበኝነት ታሪክ ጋር ይያያዛል፡፡ አያቶቻችንን በጣሊያን እንዳልተገዙ ሁሉ ቅዱስ ጊየርጊስን የመሰረቱት አባቶቻችን በእግር ኳስ ውስጥ የቀለም ልዩነት እንዳይኖር ታግለው እሸንፈውልናልና ይህንን ለመዘከር ያስችለን ዘንድ ራሱን የቻለ የቅዱስ ጊዮርጊስ የአርበኞች ቀን እንዲኖረን ከመንግስት ጋር ተነጋግሮ ይህንን የሚያስፈጽም ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡ የክለባችን ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረ መስቀል እንዳሳሰቡትም የክለቡ ደጋፊዎች ክለባችን በሚያወጣው የድርጊት መርሃ ግብር መሰረት በኮሚቴ ውስጥ እና በንዑስ ኮሚቴ ውስጥ በመሳተፍ በዓሉን ለማክበር ከወዲሁ እንቅቃሴያችንን መጀመር ይኖርብናል፡፡