Newsletter Signup

Sign-up to stay in touch with Saint George FC

Reagent/Protectorator
Yidnekatchew Tessema
Mengistu Worku

St. George Gallery

News

«ህልሜ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በአህጉራዊው ውድድር ስኬታማ መሆን ነው» ተስፋዬ አለባቸው

                                                                                                                ተስፋዬአለባቸው

ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብን በመቀላቀል በመሃል ሜዳ ተጨዋችነት ድንቅ እንቅስቃሴውን በማሳየት ላይ የሚገኘው ተስፋዬ አለባቸው(ቆቦ) ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት ከክለቡ ጋር የሚያቆየውን ውል ባሳለፍነው ሳምንት መፈረሙ ታውቋል፡፡ ተስፋዬ ባሳለፍናቸው አመታት ለተከላካይ ክፍሉ ሽፋን በመስጠት፤ ኳስን ከተቃራኒ ተጨዋቾች የሚቀማበት መንገድ እና በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ በሚያሳየው ፀባይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ደጋፊዎች እና በየዘመኑ ባሰለጠኑት አሰልጣኞች ተወዳጅ ነው፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር አመትም ምርጥ እንቅስቃሴን ከማድረጉም ባሻገር ለአመቱ ምርጥነት እጩ ከሆኑት ተጨዋቾች አንዱ ነበር፡፡

ተስፋዬ አለባቸው ለሁለት አመታት የሚያቆየውን ውል ከፈረመ በኋላም ከልሳነ ጊዮርጊስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ተከታዩን መልስ ሰጥቷል፡፡ « ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ጋር የሚያቆየኝን ውል በማደሴ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ደጋፊው የክለቡ አመራሮች እና አጠገቤ የሚገኙት የቡድን ጓደኞቼ አዲስ ተጨዋች ሆኜ እዚህ ስመጣ እንግድነት እንዳይሰማኝ የተቻላቸውን ነገር ሲያደርጉልኝ ነበር፡፡ አሁን እኔም ከታዳጊ ቡድናችን እና ከተለያዩ ቡድኖች የሚመጡ ተጨዋቾች ሲመጡ ያንን ነገር በማድረግ ላይ እገኛለሁ ሲል ገልጿል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2005 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ክለቦች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ስምንት ውስጥ ሲገባ የተስፋዬ አለባቸው ሚና ከፍተኛ ነበር፡፡ ሁሉንም ጨዋታዎች መጫወትም ችሏል፡፡ ተስፋዬ የወደፊት ቆይታውን በተመለከተ ሲገልፅም «ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ጀምረን ያልጨረስነውና ማሳካት የምፈልገው የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ስምንት ውስጥ መግባት ነው፡፡ የቀጣይ አመት እቅዴም በምሰለፍባቸው ጨዋታዎች ምርጥ እንቅስቃሴን በማድረግ ክለቤን በአፍሪካ መድረክ ያቀደውን እንዲያሳካ ማድረግ ነው፡፡ በአዲሱ አመት የሁላችንም ዋንኛ እቅድ ክለባችንን በ80ኛ አመት የምስረታ በአሉ ማክበሪያ አመት ላይ በሻምፒየንስ ሊጉ ስምንት ውስጥ እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡እዚህ ለመቆየት ፊርማዬን ያኖርኩትም ይህንን ከጓደኞቼ ጋር በመተባበር ለማሳካት ነው ሲል የሶስት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮኑ ተስፋዬ አለባቸው ተናግሯል፡፡

«ጫማዬን ስሰቅል በአሰልጣኝነት ሙያ መሰማራት እፈልጋለሁ» ደጉ ደበበ

ደጉደበበ

  • በሊጉ ታሪክ ስምንት ዋንጫዎችን በማንሳት ብቸኛው ነው፡፡
  • ለቅዱስ ጊዮርጊስ መጫወት ከጀመረ ዘንድሮ 10ኛ አመቱን ደፍኗል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ1990 ዓ.ም ጅማሮውን አግኝቶ ላለፉት 18 አመታት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ እስከ አሁን ድረስ ከተካሄዱት የውድድር አመቶች ውስጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ 12 አመታትን በበላይነት በማጠናቀቅ የማይደፈር ክብረ ወሰን ለማስመዝገብ በቅቷል፡፡ በፕሪምየር ሊጉ ቡድናችን ቅዱስ ጊዮርጊስ ለብዙ ጊዜ ሻምፒዮን በመሆን ክብረወሰኑን ሲይዝ ከተጨዋቾች ደግሞ በ1996 ዓ.ም የክረምት ወራት ክለባችንን የተቀላቀለው እና በአሁን ሰአት የቡድናችን አምበል የሆነው ደጉ ደበበ የሊጉን ዋንጫ ስምንት ጊዜ በማንሳት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ታሪክ በድል ያሸበረቀ የተጨዋችነት ዘመን ካላቸው ተጨዋቾች የመጀመሪያው እና ብቸኛው ያደርገዋል፡፡ የቀድሞዎቹ የቡድናችን ተጨዋቾች ሙሉአለም ረጋሳ እና ሳምሶን ሙሉጌታ ብዙ የሊግ ዋንጫዎችን በማንሳት ደጉ ደበበን ይከተሉታል፡፡

ደጉ ደበበ ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ጋር ለሁለት አመታት የሚያቆየውን ውል በመፈረሙ ደስተኛ መሆኑን እና የክለቡ አመራር በድጋሚ እምነት ጥሎበት የቀጣይ አመቱ እቅድ አካል አድርጎ ለቀጣይ ሁለት አመታት የክለቡን ማልያ እንድለብስ ስላስፈረመኝ ምስጋናዬን አቀርባለው ሲል ለልሳነ ጊዮርጊስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ተናግሯል፡፡

በ1997 2005 ዓ.ም ለሁለት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተጨዋች ሆኖ የ1000 ብር ተሸላሚ የሆነው ደጉ ደበበ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ከፈረመበት ጊዜ አንስቶ ለወጣቶች እንደ አርአያ የሚታይ ሲሆን በፀባዩም አመለ ሸጋ የሚባል እና የሜዳ ላይ ብቃቱም የማይዋዥቅ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክሩለታል፡፡

ደጉ ደበበ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፊርማውን ካኖረ ዘንድሮ አስረኛ አመቱን የደፈነ ሲሆን ኮንትራቱን በሚጨርስበት 2009 ዓ.ም ላይም ለተከታታይ አስር አመት እና በላይ ከተጫወቱት የክለባችን ታላላቅ ተጨዋቾች አንዱ ይሆናል፡፡ ደጉ ይህንን አስመልክቶ ሲናገርም «እኔ ይህን ታላቅ ክለብ ይህንን ያህል አመት አገለግላለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፡፡ ነገር ግን እየቆየሁ ስመጣ እና እነ መንግስቱ ወርቁን የመሳሰሉ የክለቡን ታላላቅ ተጨዋቾች ታሪክ ሳነብ አብዛኞቹ ከአስር አመት በላይ የተጫወቱ መሆኑን በማየቴ እንደነሱ ረዥም አመት ለመጫወት ህልም ነበረኝ፡፡ ያንንም ለማሳካት አላማዬ አድርጌ ጠንካራ ስራን ስሰራ ቆይቻለሁ፡፡ በእንደዚህ አይነት ታላቅ ክለብ ይህንን ያህል አመት መጫወት ከጠንካራ ስራ በተጨማሪ እድለኝነትም ያስፈልጋል፡፡ነገር ግን እዚህ ክለብ ይህን ያህል ስኬትን እንዳስመዘግብ የረዱኝን የቡድን ጓደኞቼን፤የክለባችንን አመራር አካላት እና ሁሌም ከጎኔ ሆነው የሚያበረታቱኝን የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ፡፡

በክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የመታሰቢያ ውድድር ለወደፊት ተስፋ የሚጣልባቸው ታዳጊ ተጨዋቾች ታይተውበታል

በአህጉራችን አፍሪካ እና በሀገራችን ኢትዮጵያ ሁሌም ሲታወሱ የሚኖሩት ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ ሃያ ስምንት አመታትን አስቆጥረዋል፡፡ ነሐሴ አስራ ሁለት ቀን አሰራ ዘጠኝ ሰባ ዘጠኝ ዓ.ም ህይወታቸው አልፎ ነሐሴ አስራ ሦስት ቀን የቀብራቸው ስነስርዓት በቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን መፈጸሙ የሚታወስ ነው፡፡ የአፍሪካን እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመስራችነት፣ የተለያዩ አሳማኝ ህጎችን ሃሳቦችን በማፍለቅ ለታላቅ ደረጃ እንዲደርስ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት ኢትዮጵያዊው ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ከምስረታው ጀምሮ የተሻለ እድገት ላይ እንዲደርስ ክፍተኛውን አስተዋጾ በማበርከት አሳልፈዋል፡፡ በተጨዋችነት ዘመናቸው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ሃያ ሦስት አመታት ተጫውተዋል፡፡ በከፍተኛ አመራር እንዲሁም በአሰልጣኝነትም ማገልገላቸው ይታወቃል፡፡ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በተጨዋችነት እና በአምበልነት እንዲሁም ከጨዋታ ዘመናቸው በኋላም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ ሆነው ለረጅም አመታት አገልግለዋል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በመሆን ለአራት ተከታታይ ማለትም ለአስራ ስድስት አመታት ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡ ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የአህጉራችን አፍሪካን እግር ኳስ ከመመስረታቸው ባሻገር በፕሬዝዳንትነት ተመርጠው ከመስራታቸው በተጨማሪ የአለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፊፋ አባል እንደነበሩ አይረሳም፡፡ እኝህን ምትክ ያልተገኘላቸው ታላቅ የስፖርት አባት ሁሌም ማስታወሱ ተገቢ ይሆናል፡፡ ለዚህም የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ለአስር ተከታታይ አመታት የመታሰቢያ ውድድር እያዘጋጀላቸው ይገኛል፡፡ በታላቁ የሰፖርት አባት ስም የመታሰብያ ውድድር እንዲዘጋጅ ሙሉ ወጭውን በመሸፈን እንዲካሄድ የሚያደርጉት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የስራ አመራር የቦርድ ሊቀመንበር አቶ አብነት ገ/መስቀል ናቸው፡፡ የክቡር አቶ ይድነቃቸው ቶማሰ ውድድር መካሄዱ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ትልቅ አስተዋጾ እያበረከተ ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም ከጅማሬው አንሰቶ የተካፈሉ ተጫዋቾች በተለያዩ የውደድር ዘመናት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተመጠና አሁንም ድረስ ተመርጠው የሚጫወቱት ተጨዋቾችን ማፍራት ተችሎበታል፡፡

ዘንድሮ ለአስረኛ አመት ዕድሜቸው ከአስራ አምስት አመታት የታዳጊ ተጨዋቾችንም መመልከት ተችሏል በዘንድሮው ውድድር ላይ በቅድሚያ በጥሎ ማለፍ ውድድር የተካሄደው የታዳጊ ክለቦች ጨዋታ ተጋጣሚዎቻቸውን ያሸነፉት ክለቦች ወደ ምድብ ጨዋታ በማለፍ ከተለያዩ ክልሎች ስድስት ተሳታፊ ክለቦች ጋር በአራት ምድብ ተደልድለው ሃያ ስምንት የታዳጊ ክለቦች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እና በመድን ስፖርት ክለብ ሜዳ በየቀኑ ጨዋታቸውን እያካሂዱ ይገኛሉ፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን አሰልጣኝ ሆላንዳዊው ማርቲን ኩፕማን እንዲሁም ቢሾፍቱ እየተገነባ የሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኀበር የታዳጊ ፕሮጀክት አካዳሚ ቴክኒካል ዳይሬክተር ሚስተር ሬኒና የተስፋ ቡድን አሰልጣኝ አሳምነው ገብረወልድ፣ የወጣት ቡድን አሰልጣኝ በላቸው ኪዳኔ እና የሴቶች ቡድን አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ በወድድሩ ስፍራ በመገኘት ታዳጊ ተጨዋቾችን እየመረጡ ይገኛሉ፡፡ ሁለቱም ሆላንዳዊ የእግር ኳስ ባለሙያተኞች በውድድሩ ላይ በታዳጊ ተጨዋቾች የኳስ ክህሎት አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡ የክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የመታሰቢያ ውድድር ዛሬም በአበበ ቢቁላ ስታዲየም በሚካሄዱ ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል፡፡

Tesfaye Alebachew Targeting CAF Group Stage after St George Renewal

St George Football Club announced Friday that the 26-year-old midfielder renewed his contract with the club until 2017, putting pen to paper on a deal that will be well-received among supporters, given that he was arguably the Horsemen's one of the best players last season.

St George midfielder Tesfaye Alebachew has clarified the reasoning behind his decision to stay at the club this summer. He  put an end to any speculation surrounding his future by penning a new contract in late July, committing himself to the Horsemen for a further two  years, and has now stated that he is impressed by the direction St George seem to be heading and feels it is an exciting time to be at the club.

Tesfaye told saintgeorgefc.com , “I’ve had time to think about my next step and thought it best to stay. I am happy here and so is my family.”

The three time Ethiopian premier league winner outlined the club’s ambitions, declaring that he and his team mates are aiming for a big improvement from the last season’s performance.

“I believe in the new year as a team our main target is to qualify in the group stage of African champions league. We will be back in CAF Champions League and fight for the group stage. That’s why I’m here.”  

OFFICIAL: MINYAHEL SIGNS NEW CONTRACT WITH ST GEORGE, TIED TO THE CLUB UNTIL 2017

Minyahel Teshome has put pen to paper on a new contract at St George and revealed that his primary intention was always to stay at St George. Minyahel is one of the most beloved players by the St George fans and despite looking for more midfielders, Minyahel’s presence will be important for new boss Martin Koopman.

Minyahel is a playmaker, left footed, intelligent and always giving his full heart for the team. Despite being technically sound as a wing play-maker, he always has an eye for strikers. He unlocks defenses with his well-timed precise passes, knows when to time his run, and more importantly, how to put the ball in the back of the net. He is great with his first touch and a master at playing one two’s with team mates just near the edge of the box.

"It’s a big step for me and for St George,’’ said Minyahel.  “I have trust in this team and I think we will continue improving this year, and that’s good for me and for the club. I’m happy to have renewed my contract. “I’m so grateful of the faith St George has in me, and I have every confidence in the team, and my ability to keep growing as a player. My focus right now is to grow as much as I can as a footballer, and there’s no better way to do that than to stay here at St George. ’’

A player who is good with short passes and likes to show off his amazing skills and make a mockery of a defense by dribbling past them with his amazing pace like. A team player who makes the team clicks and makes the wingers a huge part of his off the ball generosity by making sublime passes.

Degu Debebe: Happy To Renew Contract with the Ethiopian Champion St George

Twelve times Ethiopian premier league champion, St George FC, has renewed its contract with footballer Degu Debebe as  officially announced by the club on Friday August 11, 2015 and he will continue to wear the St George jersey for another two years.

Degu Debebe, former national team player, joined St George Sports Association in the year 2005 from Arbaminch Textile Factory Club where he started his carrier as a midfielder. He was voted player of the 2005 season and received 1000 birr as a prize. Since his arrival Degu has been a model of consistency sportsmanship and has helped the club win eight premier league titles.

The news will be a relief for the staunch and ardent supporters of the club who have been eager for his decision to once more be part and parcel of the team. The 31 years old veteran player upon the expiry of his new contract agreement in 2007 would make him one of the very few footballers who played for the club for more than ten years in a row.

In his conclusion Degu said that he wants to thank his team mates for their kind cooperation, respect and assistance rendered to him; the club management for believing in him to serve the club for the next two years; the coaches for the time and effort they all put into coaching him during his stay in the club.    

 

ታሪክን ማስቀጠል መጋቢት 1929 ዓ.ም አዲስ አበባ አራት ኪሎ

አየለ አትናሽና ጆርጅ ዱካስ አብሮ አደግ ጓደኞች ናቸው፡፡ገና ታዳጊ ናቸው፡፡ሁለቱ ልጆች በጧት ተነስተው ሁለት በጎች እየነዱ ጣሊያኖች በብዛት በሚገኙበት ቦታ እየተዘዋወሩ ነው፡፡ ሁለቱ ልጆቹ በጎቹን ሳር ለማብላት አይደለም የሚነዱት ወይም ሊሸጧቸው አልነበረም፡፡ስሜታቸው የጎዳ ነገርና ጓደኝነታችውን የሚለያይ መጥፎ ስሜት ጣያሊያኖች በማሳደራቸው ያንን ነገር ለመቃወም ነበር፡፡አየለና ጆርጅ ጎረቤታሞች ናቸው፡፡ጊዮርጊስ ክለብን የመሰረቱት እነርሱ ናቸው፡፡ጆርጅ ነጭ ነው(ግሪካዊ)አየለ ደግሞ ሀበሻ ነው፡፡ሁለቱ ኳስ ለመጫወት ሲሄዱ አንድ ጣሊያናው አስቆማቸው፡፡ይህ ሰው ሲኞር ማርቲኔሌ(በኋላ ጣሊያን ባቋቋመው ፌዴሬሽን ውስጥ ሰርቷል)መንገድ ላይ እየተጓዙ አስጠራቸውና ‹‹ወዴት ነው የምትሄዱት?››አላቸው

‹‹ኳስ ለመጫወት››

‹‹የት?››

‹‹ወደ ሜዳ››

‹‹ከእንግዲህ ሁለታችሁ አብራችሁ መጫወት አትችሉም››

‹‹ለምን ?››

‹‹ህጉ ያግዳችኋል››

‹‹የምን ህግ?››

‹‹ሰሞኑን ተግባራዊ ይሆናል››

ሁለቱ ልጆች በቀለማቸው አብረው እንዳይጫወቱ ታገዱ፡፡ ያን ጊዜ ጣሊያን ጥቁርና ነጭ አንድ ላይ መጫወት አይችሉም ብሎ ህግ አወጣ፡፡አየለና ጆርጅ ነጭና ጥቁር በግ ይዘው መዘዋወር ጀመሩ፡፡እነዚህ በጎች በግ ናቸው ፡፡የሚለያቸው የቆዳ ቀለም እንጂ አንድ ናቸው፡፡ ሁለቱ ጓዶች ምንም ነገር መፍጠር ባይችሉም ለጊዜው ሃሳባቸውንና የተጎዳውን ስሜታቸውን በዚህ መንገድ ለመግለጽ ተገደደዱ፡፡እነዚህ ሁለቱ ልጆች ሃሳባቸውን ለሌላው በማካፈል ቅስቀሳ ጀመሩ፡፡ጆርጅ ነገሩን አጠንክሮ ገፋበት፡፡ በትምህርት ቤት ያሉ ጓደኞቹ ትግሉን ተቀላቀሉ ፡፡ትምህርት ቤት ውስጥ ይሄንን ውሳኔና ህግ የሚቃወም ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ተለጥፎ ተገኘ፡፡ማን እንዳደረገው ባይታወቅም ጆርጅ ላይ ተሳበበ፡፡ቡሉቅባሽ የሚባል ማዕረግ ያላቸው ወታደሮች ቤቱ ሄዱ፡፡ነጭ ሆኖ ዙሪያውን አረንጓዴ ፤ቢጫ ና ቀይ ያለበትን ማሊያ ተሰቅሎ አገኙ፡፡ይሄ ማሊያ ጊዮርጊስ ለሁለተኛ ጊዜ ያሰራው ነበር፡፡የክለቡ ማሊያ የሚቀመጠውና እንደ ጽህፈት ቤት የሚጠቀሙት የጆርጅ አባት ለቡድኑ በሰጡት አንዲት ክፍል ነበር፡፡፡ ጆርጅ ተያዘና ታሰረ ፡፡ብዙም ሳይቆይ ቢለቀቅም በሌላ ግዜ ሰላይ ነው በሚል ከነቤተሰቡ ታሰረና ኮረም አስር ቤት ተከተተ፡፡ጣሊያህ ህጉን አወጣ፡፡

ጥቁርና ነጭ አንድ ላይ መጫወት የለባቸውም በሚል በአዋጅ አስነገረ፡፡ ደንቦችን አወጣ፡፡ጥቁሮች መሳለሚያ አካባቢ ባለው ኳስ ሜዳ እንዲጫወቱ ነጮች ደግሞ አሁን ሳንጆሴፍ ትምህርት ቤት ባለው ስፍራ እንዲገለገሉ ተደረገ፡፡ለጥቁሮች ከወጡት ህጎች አንዱ ለእንግዳውና ለዳኛው የፋሽስት ሰላምታ መስጠት ግዴታ ነው፡፡ጎል ያገባ ተጨዋች ለዳኛ የፋሽስት ሰላምታ ካልሰጡ ግቡ አይጸድቅም፤ቡድኖች በጣሊያን ሀገር ያሉ ቡድኖችን አይነት ማለያ እንዲለብሱ ይገደዳሉ፤እያንዳንዱ ተጫዋች ተያዥ ካላመጣ አይጫወትም.......ህጎቹ ብዙ ናቸው፡፡ጣሊያን ከመግባቱ በፊት ጥቁሮች ከነጮች ጋር ይጫወቱ የነበሩት በመከልከሉና ህግ በመውጣቱ ኳስ ሜዳ ላይ ህጉን በመቃወም አመጽ እየተነሳ ብዙ ተጨዋቾች ታስረዋል ፤ተቀጠተዋል ፡፡

ጣሊያን ከሀገር እንደወጣ የጊዮርጊስ ክለብ ተጨዋችና ደጋፊዎች ህግ በጉዳዩ ላይ ተወያዩበት፡፡ ጣሊያን በዘርና በሀይማኖት ክለቦችን ለማስተዳደር የወጣውን ህግ መሻተር እንዳለባቸው ተነጋገሩ፡፡በተለይ በቀለም ልዩነት በተመለከተ ከነጮች ጋር ምንም ግንኙት እንዳይኖር ያወጣው ህግ መሻርና ኢትዮጵያው ስጥ ከሚኖሩ የውጭ ዜጎች ጋር ተወያይቶ አንድ መፍትሄ ማበጀት ነበረባቸው፡፡ በጣሊያን ግዜ ከተቋቋሙ የሀበሻ ቡድኖች ሳይፈርስ የቀረው ጊዮርጊስ ብቻ ነበር፡፡ሌሎቹ ቡድኖች የተቋቋሙት በጣሊያኖች ድርጅት ስር በመሆኑና ጣሊያን ሲወጣ ድርጅቶቹ ሲፈርሱ ክለቦቹም የመበታተን እጣ ገጣማቸው ፡፡ጊዮርጊስ ግን በተጨዋቾች የተቋቋመና የማንም ጥገኛ ስላልነበረ ጣሊያን ሲባበር በራሱ ቀጠለ፡፡በከተማው ውስጥ የቀረው ብቸኛ ክለብ ጊዮርጊስ ቢሆንም ጣሊያን ከፋፍሎ በሄደው ህግ የተነሳ ግንኙነት የሚፈር ስለጠፋ ሁሉም ተደብቆ ነበር፡፡ጊዮርጊስ ይሄን ለመስበርና ሁሉንም ለማገናኘት እንቅስቃሴ ጀመረ፡፡የክለቡ ደጋፊና ተጨዋቾች ተወያይተው ከፎርቲቲዲዮ ክለብ ጋር ግንኙነት ፈጠሩ ፡፡ፎርቲቱዲዮ የተፈለገው የጣሊያን ቡድን በመሆኑ ህጉን አንዲተገበር ካደረጉ ሰዎች ውስጥ አብዛኛው እዚያ ክለብ ውስጥ ስለነበሩ ነው፡፡በጊዮርጊስ በኩል ይድነቃቸው፤ አመለወርቅና ወንድምየው አፈወርቅ ተመላልሰው ጣሊያኖችን አሳመኑ፡፡በሀሳቡ ከተስማሙ በኋላ ፡፡በቅድሚያ ብዙ ተወያዩ ፡፡ተወያይተውም የጣሊንያ ስፖርት ጽፈት ቤት ያወጣውን መሻር ነበረባቸው፡፡ህጉ መሻሩን ምክኒያት በማድረግ ሁለቱ አንድ ግጥሚያ ለማድረግ ሀሳብ ቀረበ፡፡ግጥሚያን ለማድረግ ይድነቃቸውና አመለወርቅ ከ6ወር በላይ ተመላለሱ ፡፡ፎርቲቲዲዮ ቢስማማም ህዝቡ በጣሊያን ላይ ያለው አመለካከት ገና ስላልረገበ ጨዋታው ጸብ ቢነሳ ረብሻውን ተገን አድርጎ የሀገሬው ሰው ሊገለን ይችላል በሚል ፍራቻ ነው ፡፡በመጨረሻ ግጥሚያ ለማድረግ ቢስማሙም የፖሊስ ጥበቃ ያስፈልገናል አሉ፡፡ያኔ ግዜ ፌዴሬሽን አልነበረም፡፡ስፖርቱን የሚያስተዳድር ህጋዊ አካልም የለም ፡፡በዚህ የተነሳ ፖሊስን ለማስመደብ የሚያስችል አቅም አልነበረም ፡ጊዮርጊሶች‹‹›ፖሊስ እናንተን አያድናችሁነም እኛ ግን ልንጠብቃችሁ እንችላለን ፡፡የሁለታችን ግሚያ ለሌሎችም አስተማሪ ነው ›አሉ፡፡ ጣሊያኖች በሰላይ መኖር የሚችሉት ይሄን ህግ ፈርመው ግይሚያ አድረገው ሰለማዊ መነገድ መከተል ሲችሊሉ እንደሆ ነ አሳመኑዋቸው፡፡ጣሊያኖች በነገሩ ተስማሙ፡፡ በመጀመሪያ ፋሽስቱ ያወጣውን ህግ ሻሩ፡፡ምክኒያቱም ጣሊያን ተባሮ ስለወጣ ህጉ ሳይሻር እንደነበረ ተቀምጦ ነበር፡፡ነጭና ጥቁሩም ሳይገናኝ ተገድቦ ነበር፡፡ጊዮርጊስና ፎርቲቲዲዮ የቀድሞውን ህግ ሻሩና ጊዮርጊስ ባቀረበው ረቂቅ ላይ ተወያተው ነጭና ጥቁር ሳይለያዩ ለመጫወት የሚያስችላቸውን ደንብ አጸደቁ፡፡የህጉን መውጣት ለማብሰርና አንድነታቸውን ለማሳየት እንዲሁም ጣሊያን ያወጣውን ህግ መሻሩን ለማረጋገጥ ግጥሚያ ለማድረግ ቀን ቆረጡ፡፡ሁለቱም ተፈራረሙና 5 ሰዓት ላይ ሲኒማ ኢትዬጵያ ገቡ(እነዚህ ነገሮች በሌላ ግዜ በዘርዝር ይጠቀሳሉ) ከሰዓት በኋላ ኳስ ሜዳ ሄዱ፡፡፡ በወቅቱ በአንዳንዶቹ ዘንድ ተቃውሞ ቢኖርም አላማውን ከግብ ለማድረስ ተጫወቱ፡፡ጊዜው 1934 ነበር፡፡እለቱም ግንቦት አምስት ነው ፡በግጥሚያው ጊዮርጊስ 4ለ1 አሸነፈ ፡፡በዚህ ግጥሚያ የጉሉ ውጤት እንጂ ሁለቱም አሸናፊ ነበሩ፡፡ዋናው አላማ ጥቁርና ነጭ አብሮ እንዳይጫወት የሚገድበውን ህግ ሽረው በአንጻሩ እንዲጫወት የሚፈቅደውን ህግ አጽድቀው ግንኙቱን የሚበስረውን ግጥሚያ ማድረጋቸው ነው፡፡ሁለቱ ክለቦች የተፈራረሙበትን ወረቀት ለሁሉም የውጭ ቡድኖች ተላከ፡፡ በ1935 ሌሎች ቡድኖች የተካተቱበት የሙከራ ጨዋታ ተደረገ፡፡ ነጭና ጥቁር አንድ ነው የሚለውን ደንቡን አሻሽለው ለማስታወቂያ ሚኒስቴር ላኩ፡፡ በወቅቱ ፌዴሬሽን ባለመቋቋሙ እግር ኳሱን እንደ ፌዴሬሽን ሆኖ ለመምራት የተዘጋጀው ይሄው መስሪያ ቤት በመሆኑ ነበር፡፡ማስታወቂያ ሚኒስቴር(በወቅቱ ማስታቂያ መምሪያ) ወድድሩን ለመምራት የሙከራ ግጥሚያ አዘጋጀ፡፤አላማውን አሳወቀና ጊዮርጊስ ያወጣውን ደንብ ተነጋግረውበት ሁሉም ክለቦች ባሉበት አጸደቁት፡፡ ማስታወቂያ ሚኒስቴር የሚመራው የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ሻምፒዮና በ1936 ዓ.ም ተጀመረ፡፡የተካፈሉት የጣሉያኑ ፎርቲቲዲዮ፤የእንግሊዙ ቢ.ኤም.ኤም ፤የግሪኩ ኦሎምፒያኮስ፤የአርመኑ አራራት፤ከኢትዮጵያ ጊዮርጊስ ነበሩ፡፡ሁሉም ቡድኖች የቀለም ልዩነት ሳይኖር ለመጫወት ተስማሙ፡፡ህንዶች ቡድን ባይኖራቸውም በዳኝነት ይሳተፉ ነበር፡፡በናይሮቢ ህንዱና ኬንያዊው ለእንግሊዙ ጥቁር ነበር፡፡በኢትዮጵያ ግን ህንዱ ከእንግሊዙ ጋር እኩል መብት ነበረው፡፡የእንግሊዝ ደጋፊዎች በህንድ ዳኛ ላለመመራት ቢያንገራግሩም ፈርመዋልና ተቀበሉት፡፡ ህንዱና እንግሊዙ እዚህ እኩል መብት ነበራቸው፡፡ ጊዜው በ1936 ዓ.ም ሲሆን ህንድ ከእንግሊዝ ነጻ የወጣው በ1940 ዓ.ም ነበር፡፡እዚህ ቀድሞ ነጻ ወጥቷል፡፡ በማን? ጊዮርጊስ ባወጣው ህግ!!!

  በዳኝነት ፤በኮሚቴነት፤በክለብ የተመዘገቡት የውጭ ኮሚኒቲዎች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጠቅላላ ጉባኤ አባል ሆነው ይሰራሉ፡፡ በድምጽ ይወስናሉ፡፡የፈረሙት ህግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ደንብ ሆኖ ጸደቀ፡፡የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በ1949 ዓ.ም ሲቋቋም የኢትዮጵያ ተወካዮች በምስረታው ላይ ክለቦች ያወጡትን ህግ አቀረቡ፡፡ግብጽና ሱዳን የቀለም ልዩነትን ህግ በተመለከተ ብዙም በይገፉበትም የኛ ተወካዮች ‹‹ሞተን እንገኛለን ይሄ ህግ መካተት አለበት›› በማለታቸው በብዙ ክርክር ጸደቀ፡፡የደቡብ አፍሪካ ቡድን በአፓርታይድ ህግ ስለሚተዳደር ነጭና ጥቁር ተጫዋች አብሬ አልቀላቅልም በማለቴ በህጉ መሰረት ከውድድሩም ከካፍም ተባረረ፡፡ደቡብ አፍሪካ የፊፋ አባል በመሆኗ ሌላ ችግር መጣ፡፡ፊፋ‹‹የኔን አባል አንድ አህጉራዊ ፌዴሬሽን ማገድ አይችልም ››በሚል ጫና አሳደሩ፡፡በወቅቱ ፊፋን የሚመሩት እንግሊዛዊ በደቡብ አፍሪካ ድርጅት ያላቸውና የጥቅም ተጋሪ ስለነበሩ ካፍ ላይ ጫና አሳደሩ፡፡ይሄን ህግ በመተዳዳሪ ደንቡ ውስጥ ያካተተውና ባለጉዳዩ ኢትዮጵያ በመሆኗ ጫናው እኛ ላይ አረፈ፡፡ፊፋ እኛን አስወግዶ የደቡብ አፍሪካ አከባቢ ያሉትን እነማላዊና ዘምቢያን በመጨመር ሌላ ‹‹የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ››በሚል ለማቋቋም ማዘጋጀቱን እነአቶ ይድነቃቸው ደረሱበትና አጋለጡ፡፡ደቡብ አፍሪካ የፊፋ አባል በመሆኗ ካፍ ያወጣው ህግ እንዲፈርስ ብዙ ጥረት አደረገች፡፡ኢትዮጵያም ህጉ በፊፋ እንዲጸድቅ ለአስራ ስድስት አመት በፊፋ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ህጉ እንዲጸድቅ ታገሉ፡፡በየጉባኤው ሲያነሱ ውድቅ ሲደረግባቸው ከቆየ በኋላ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1974 ዓ.ም ፍራንክፈርት ላይ በተካሄደው የፊፋጠቅላላ ጉባኤ ላይ   ጸደቀ፡፡

ኢትዮጵያ ያቀረበችውና የጸደቀው የደንብ ረቂቅ ‹‹በኢንተርናሽናል ፉትቦል ፌዴሬሽን እንቅስቃሴ ውስጥ ባንድ አገር ወይም ባንድ ሰው ላይ በዘር፤በሀይማኖት በጎሳ የተነሳ ልዩነት ማድረግ አይፈቀድም፡፡የዘር ፤የሀይማኖት፤የጎሳ ልዩነት በህግ በመሰረተ ሀገር የሚገኝ ብሄራዊ ፌዴሬሽን ከፊፋ አባልነት ጨርሶ ይታገዳል››የሚል ነበር፡፡ኢትዮጵያ በፊፋ ስብሰባ ለረጅም አመታት ላይ ስታነሳ በድምጽ ብልጫ ሲወድቅባ ተራማጅ የሆኑትን በማሳመንና ድጋፍ በማሰባሰብ በመጨረሻ ሊጸድቅ ችሏል፡፡ይሄ ለኢትዮጵያ ትልቅ ድል ነበር፡፡ውሳኔው በአፓርታይድ ህግ የሚተዳደረውን የደቡብ አፍሪካ ፌዴሬሽንን ከፊፋ ያሳገደ ሲሆን በአለም ያሉ ጥቁር ተጨዋቾች በፈለጉበት ሀገር በነጻነት ለመጫወት የሚያስችል ህግ ነበር፡፡

የዚህ ህግ መጽደቅ ኢትዮጵያ ለሰው ልጅ መብት፤እኩልነትና ነጻነት ያደረገችውን ተጋድሎ ያመለክታል፡፡ አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል ሲሆን ይሄኛው ደግሞ በአለም ላሉ ጥቁር ተጫዋቾች ነጻነትን ያጎናጸፈ ነው፡፡ ጉዳዩን አቶ ይድነቃቸው በየስብሰባ ላይ ያቅርብ እንጅ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌረዴሬሽን የወሰነው ነው፡፡ነገር ግን ይሄ ጉዳይ አንድም ቀን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያለለመነሳቱ ብዜ ነገር እንደ ጉዳት የሚታይ ነው፡ብሄራዊ ቡድኑ ደቡብ አፍሪካ ለአፍሪካ ዋንጫ በሄደ ጊዜ ትንሽ አዳራሽ ተከራይተው ጋዜጠኞችን ጠርቶ መጠነኛ የፎቶ ኤግዚቢሽን አዘጋጅቶ ‹‹እኛ ለአፍሪካውያን ስፖርተኞች ነጻ መውጣት ብዙ ታግለናል፡፡ነጭና ጥቁር በአንድ መድረክ እንዲጫወቱ ትልቅ አስተዋኦ አድርገናል›› ቢሉ ሀገራችን በአለም ስፖርት አደባባይ ያበረከተቸው አስተዋጽኦ ይታወሳል፡፡ ትልቅ ቦታ ያገኛል፡፡የአንድ ሀገር እግር ኳስ የሚለካው በውጤት ብቻ ሳይሆን ለስፖርቱ በሚያበረክተውቁም ነገር ነው፡፡ይሄ ጉዳይ የሀገራችን ስም በከፍተኛ ጉዳይ የሚያስጠራ ሀፐኖ ሳለ ያንን ትልቅ ታሪካችን ደብዝዞ ና ተረስቶ መቅረቱ ያሳዝናል፡፡አሁን ያለው ትውልድ ስለዚህ ነገር እምብዛም አያውቅም፡፡ እንዳያውቅ ያደረግነው እኛው ነን፡፡ጭንቅላቱ ውስጥ ስለአውሮፓ ፉትቦል እንዳይረሳ እየጨቀጨቅነው ትቀልቁን ነገራችን ቦታ አሳጥተን አስረሳነው፡፡ደቡብ አፍሪካ ነጻ ስትወጣ ማንዴላ ለኛ ሰዎች ሽልማት ሲሰጡ ድካማችንን አስታወሰው ነው፡፡እኛ ግን ይሄን ትልቅ ታሪክ ቦታ አልሰጠነውም፡፡ይሄንን ያደረጉት ኬንያ ወይም ሌላው ሀገር ቢሆን ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ያወራሉ ፤ያስወራሉ አመታዊ በዓል አዘጋጅተው ያከብራል፡፡

  ህጉ ገፍራንክፈርትላ ሲጸድቅ አቅራቢዋ ሀገራችን ትሁን እንጅ እዚህ የነበሩት ኪሚኒቲዎች ትልቅ ሚና ነበራቸው፡ በወቅቱ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይሰሩ የነበሩ የውጭ ዜጎች ማለትም የሀንጋሪ፤ግሪክ፤አርመን፤የመን፤እንግሊዝ ፤ፈረንሳይ፤ስዊድንና ሌላ ሀገር ዜጎች የሀገራቸውን እግር ኳስ ፌዴሬሽን በማግባባትና በመጫን በፊፋ ድል እንዲገኝ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡የእነዚህ ሀገር ዜጎች ገና ትግሉ ሲጀመር አብረው የነበሩ ናቸው፡፡ትግሉ የተጀመረው ኳሰ ሜዳ በመሆኑ ከዚያ የተነሳው ነገር ተቀጣጥሎ በፊፋ ህግ ሆኖ ወጣ ፡፡ይሄ በአለም እግር ኳስ ታሪክ ትልቅ ቦታ ያለው ነገር እንዴት በዋዛ ዝም ይባላል?አሁንም ጊዜው አልረፈደም ይሄ ትግል የተጀመረበት ቦታ አንድ መጠነኛ ሀውል ቢቆም በሀውልቱ ላይ ፤ይድነቃቸው ተሰማ፤አመለወርቅ ተክለዜና፤ገብረስላሴ ኦዳ፤ዲሚትሪ ስጎሎምቢስ፤ኦኔ ኒስከን፤ፒየር ኮንቲ፤ሙሴ ሌንታኪስ.....ቢኤም ኤም፤ፎርቲቲዲዮ፤ኦሎምፒያኮስ ፤ጊዮርጊስ የሚሉ ጽሁፎች ቢቀመጡ ትልቅ ማስታወሻ ነው፡፡ሀውልቱን የሚያዩ ምክኒያቱን ይረዳሉ፡፡የሀገራችንየስፖርት ሰዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ያደረጉትን ትግል ይገነዘባሉ፡፡ከዚሁ ጋር ተያያዞ በያመቱ ግንቦት አምስት ቀን የቀለም ልዩነት ትግል የተጀመረበት(ፎርቲቲዲዮና ጊዮርጊስ ተፈራርመው የተጫወቱበት) በሚል ቢከበር

1ኛ ትላንት ለዚህ አላማ የታገሉትን እናስታውሳለን

2ተኛ ቱሪስቶች ሲመጡ እንዲጎበኙና አላማውን እንዲረዱ ይደረጋል

3ተኛ መጪው ትውልድ ታሪኩን ይዞ እንዲያስቀጥል ያስችላል

4ተኛ ሀገራችን በአለም እግር ኳስ ያበረከተቸውን አስተዋጽኦ አመላካች ይሆናል

የሊቨርፑሉ ታዋቂ ተጫዋች የነበረው ጆን ባርነስ አዲስ አበባ መጥቶ በነበረ ጊዜ ናይት ክለብ ወስደው አዝናኑት፡፡ ባርነስ በጥቁርነቱ በባለጋራ ደጋፊዎች ከሚሰደቡ ተጨዋቾች አንዱ ነበር፡፡‹‹አንተና ሌሎች ጥቁሮች ነጻ የወጣችሁት እዚህ ቢታ በተጠነሰሰ ትግል ነው›› ተብሎ ቦታው ድረስ ሄዶ ቢያይ ወደ ሀገሩ ሰመለስ‹‹ጥቁር ተጫዋቾች ነጻ የወጡበትን ቦታ አየሁ›› ብሎ ቢናገር ለኢትዮጵያ ትልቅ ማስተዋወቅ ከመሆኑም በተጨማሪ ትላንት ለዚህ ጉዳይ ለታገሉት ሁሉ ትልቅ ውጤት ነው፡፡ የስዊድን ፤ሆላንድ፤ፈረንሳይ ዜጎችም ሲመጡ ሀውልቱን በማሳየት‹‹እዚህ የነበሩት የናንተ ሰዎች ከኛ ጋር ታግለው ይሄ ህግ እንዲጸድቅ አድርገዋል›› ብሎ ማስተዋወቅ ቢቻልና ቢሰራበት ትልቅ ዋጋ አለው፡፡ታዲያ ምንድነው ዝምታው?ትላንት ጊዮርጊስ ሀሳቡን አንስቶ ሌሎችን ክለቦችና አሳትፎ ከብዙ ጥረት በኋላ ይሄ ህግ ከሀገር አልፎ በአህጉር ተሸግሮ በአለም ህግ ሆኖ እንዲወጣ ክለቡ ጥረት አድርጓል ፡፡ትላንትም ከሌሎችጋር በጋራ ሰርቶ ዳር አድርሷል ዛሬ ይሄን ታላቅ ነገር ተዳፍኖ እንዳይቀር ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የ2007 ዓ.ም. ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የመታሰቢያ ውድድር የተሳታፊ ክለቦች ምዝገባ ሊጀመር ነው ፡፡

የአህጉራችን አፍሪካና የሀገራችን ኢትዩጵያ የስፖርት አባት የነበሩት ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ ሃያ ሰባት አመታት አስቆጥሯል፡፡ እኝህ ታላቅ የስፖርት አባት በህይወት ዘመናቸው ያበረከቱት አስተዋፅኦ መቼም ቢሆን የሚረሳ አይሆንም፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ከጅማሬው አንስቶ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ በርካታ ቁም ነገሮችን ሰርተዋል፡፡ የአህጉራችን አፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዲመሰረት የተለያዩ ሃሳቦችን በማፍለቅ ግንባር ቀደም የነበሩትን እርሳቸው ነበሩ ማለትም ለአስራ ስድስት ዓመት መምራታቸውም ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ለረጅም አመታት በዋና ፀሃፊነት አገልግለዋል፡፡

ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በተጫዋችነት፣ በአምበልነት እና በአሰልጣኝነት አሳልፈዋል፡፡ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብም ለሃያ ሶስት ዓመታት ተጫውተው በማሳለፍ በሪከርድነት ለመመዝገብ በቅተዋል፡፡ እኝህ ታላቅ ሰው ሁሌም እንዲታወሱ ለማድረግ በየዓመቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የመታሰቢያ ውድድር እንዲዘጋጅላቸው ያደርጋል፡፡ እስካሁን ድረስ ለዘጠኝ አመታት የመታሰቢያ ውድድር ተዘጋጅቶላቸዋል ዘንድሮ ደግሞ ለአስረኛ ጊዜ ይካሄድላቸዋል፡፡ የውድድሩን ሙሉ ወጪ በመሸፈን እንዲካሄድ የሚያደርጉት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አብነት ገ/መስቀል ናቸው፡፡

እንደሚታወቀው የክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የመታሰቢያ ውድድር የሚካሄድበት ወቅት ክረምት ወራት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም ህይወታቸው ያለፈው ነሐሴ ወር ውስጥ በመሆኑም ነው፡፡ የዘንድሮውን ውድድር በተለየ መልኩ ለማካሄድ ከወዲሁ የውድድሩን የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡ ሌላው ጥሩ አጋጣሚ የሚሆነው ደግሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሰማንያኛ ዓመት ክብረ በዓል በመጪው ታህሳስ ወር ስለሚካሄድ የተለየ ድምቀት የሚሰጠው ይሆናል፡፡ በዘንድሮው ውድድር ላይ ከአዲስ አበባ ተሳታፊ ቡድች በተጨማሪም የክልል ቡድኖች ይሳተፉበታል፡፡ በውድድሩ ላይ የሚሳተፉት እድሜአቸው ከአስራ አምስት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ሲሆኑ ምዝገባውም ከሰኞ ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

የክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ

መታሰቢያ ዋንጫ ውድድር የምዝገባ መለኪያዎች

2007 ዓ.ም. የክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የመታሰቢ ዋንጫ ውድድር ከዚህ በታች የተመለከቱትን የምዝገባ መለኪያዎች መሠረት በማድረግ ከሰኞ ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 14 ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ ምዝገባው በቅሎ ቤት በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ጽ/ቤት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

  1. የተወዳዳሪ ቡድን ተጨዋቾች ዕድሜ ከ13 ያላነሰ ከ15 ያልበለጠ
  2. ተወዳዳሪ ቡድኖች ከተመሠረቱ ቢያንስ ሁለት ዓመት የሞላቸውና የሰለጠኑ ለዚሁም ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. ሃያ ተጫዋቾችን ማስመዝገብ የሚችሉ
  4. አሰልጣኝ፣ የቡድን መሪና ወጌሻ ማቅረብ የሚችሉ
  5. የእያንዳንዱ ተጫዋች ሙሉ ሶስት ጉርድ ፎቶግራፍ ማቅረብ
  6. የ2006 ዓ.ም የተጫዋቾቹን የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  7. የተወዳዳሪ ቡድኖች ተጫዋቾ ጥሩ ስነ ምግባር ያላቸውና ስፖርታዊ ጨዋነትን የሚያከብሩ ለዚህም ቃል የሚገቡ
  8. አወዳዳሪው አካል ለሚያወጣቸው መመሪያዎችና ደንቦች ተገዥ ለመሆን ፈቃደኛ የሆኑ