Newsletter Signup

Sign-up to stay in touch with Saint George FC

Reagent/Protectorator
Yidnekatchew Tessema
Mengistu Worku

St. George Gallery

News

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገ/መስቀል የካፍ ስብሰባን ተካፍለው ተመለሱ

አቶ አብነት ገ/መስቀል የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የክለቦች የውስጥ ውድድር ኮሚሽን አባል ካፍ ካይሮ ላይ ባደረገው ስብሰባ ተሳትፈው ተመልሰዋል፡፡

ስብሰባውን የመሩት የወቅቱ የፊፋ ተጠባባቂና የካፍ ፕሬዝዳንት የሆኑት ካሜሮናዊው ሚስተር ኢሳ ሀያቱ ሲሆኑ አቶ አብነት ገ/መስቀልም ፕሬዚዳንቱ ፊፋን እንደገና ለማወቅርና የማሻሻያ ሥራዎች ለማከናወን በሚያደርጉት ጥረት የመላው አፍሪካውያን ትብብር የማይለያቸው መሆኑን በማረጋገጥ ሥራቸው የተቃና እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልፀውላቸዋል፡፡አቶ አብነት ገብረ መስቀል በስብሰባው ላይ ከአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ ሂቻም ኤል አምራኒ ጋር ባደረጉት አጭር ውይይትም ካፍ አዲስ አበባ ላይ የሚከፍተውን የካፍ የብቃት ማረጋገጫ ተቋም( Centre of Excellence) በአዲስ መልክ የሚጀምርበትን ሁኔታ እና አጠቃላይ የአመራር ሁኔታውን በማጥናት ሪፖርት እንዲያቀርቡ ተመድበዋል፡፡የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን እስከ አሁን ድረስ በካሜሩን ያውንዴ የሴንተር ኦፈ ኤክሰለንስ ተቋምን የከፈተ ሲሆን አዲስ አበባ ላይም እ.ኤአ. 2016 መጨረሻ ላይ እንደሚከፈት ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

ጆርጅን ፍለጋ

ታዳጊው ወጣትበሩን በሀይል ያንኳኳውን ሰው ለማየት በአጥር ላይተንጠልጥሎ መመልከት ጀመረ፡፡ከውጭ ያለው ሰው እንዳይመለከተው ከአጥሩአጠገብ በበቀሉት ዛፎች ቅርንጫፍ ተከልሎ ማንነቱን ለማውቅ ሞከረ፡፡ቤተሰብ አይደለም፡፡ከዘመዱቹ አንዱአልነበረም፡፡ ታዳጊው ወጣት ያንኳኳውንሰው ፊማየት አልቻለም፡፡ሰውየው እንደገናተመልሶ ወደ መንገዱ ሄደ ፡፡አጥሩ ላይያለው ወጣትሰውየውን ማንነት ባለማየቱ መረጋጋት አልቻለም፡፡ወታደር እንደሆን ጠርጥሯል፡፡ተመልሶ እንደሚመጣ ገምቷል፡፡ እዛው እንዳለ ሰውዬው ተመልሶ መጣ፡፡ፊቱን ሲያየው አወቀው፡፡ቶሎ ብሎ ከአጥሩ ወረደና እየሮጠ ወደ ቤቱ ውስጥ ገባ፡፡እንደገባ ቶሎ ብሎ‹‹ጆርጅ!!››አለ

‹‹አቤት››

‹‹ቶሎ በል››

‹‹ምነው?››

‹‹መጥተዋል ተደበቅ›››

                አየለናርጅ ከልብየሚዋደዱ ጓደኛሞች ና፡፡ ሰዎች አየለን ሲያገኙት ብቻውን ከሆነ ‹‹›ወንድምህ የት ሄደ ››ይሉታል ጆርጅንም ሲያገኙት እንደዚሁ፡፡ጓደኛሞች ሳይሆኑ እንደወንድማማች ነው የሚያስቧቸው፡፡በሀሳብ ተቀራራቢ ብቻ ሳይሆኑ የተዋሃዱም ናቸው፡፡ለሁለቱ ማስተወሻ ብለው ያቋቋሙ የጊዮርጊስ ቡድን ብዙ ጓደኞችን አሰባስቦሁሉም በፍቅር ቤተሰብ ሆነዋል፡፡አሁን ግን ጣሊያን ያን ወዳጅነታቸውን ለመበታተን በክለባው ውስጥ ገብቷል፡፡ጆርጅ ዱካስጣሊያኖች ከሚፈለጉ ታዳጊዎች አንዱ ነው፡፡ቤተቦቹ በጣሊያንእጅ ወድቀዋል፡፡በስለላ ስለተጠረጠእስር ከባድቅጣት ያገኛቸዋል ተብሎ እየተባለ ግዜ ጆርጅ አልተያዘም ነበር፡፡አየለ ዘመዱ ቤትው ያለው፡፡  አጎቱ ናቸው፡፡ አጎቱወደ ክፍለ ሀገር ለቅሶ ስለሄዱ እሱና ሰራተኞቹ ናቸውበቤት ውስጥያሉት፡፡ሰውየው ሁለቱን እንደወንድማማችስለሚያዩዋቸደዷቸዋል፡፡ለክለቡ የሚረቡትን ዶሮና የበግ ግልገሎች እዚሁ ቤት ነው ያኖሩት፡፡ዶሮዎቹ እንቁላል ሲሉ ጫጩቶችያረቡና ይሸጣሉ፡፡ከሽያጭ የተሰበሰወበውፍራንክገንዘብ ያዡ ካሳ ጋር ይቀመጥና ለክለባቸው አገልግሎት ይውላል፡፡ርብ የተገዙት የበግ ግልገሎችም እሁ ግቢ ከሌሎች ከብቶች ጋር አብረው ይኖራሉ፡ግቢውን አንዳንድ ግዜ ክለባቸውን ለሰብሰቢያነት ይጠቀሙበታል፡፡ዋናው መሰብሰቢያ እነጆር ቤትትየው በሰጧቸው ቤት ውስጥ ነው፡፡በቅርቡ ጣሊያን ሰፈር ቡድን ያቋቁል ስለተባለ በየቦታው እየተመዘገቡ ነው፡፡ጊዮርጊስ ቀድሞ ስለተቋቋመ መሰባሰብአያስፈልገውም፡፡ነገር ግንለቡ አዲስ ያሰራውን ማሊያ አድገው እንደማጫወቱ ያውቁታ፡፡ከመጀመሪው ማሊበኋላ ሁለተኛነጭ ሆኖ በሆዱ ላዙሪያውን የኢትዮጵያ ባንራ ያለበት ነው፡፡ይሄ ደግሞ የጣሊያን ደምፍላእንደሚጨምር ስለሚያውቁ አይጠቀሙበትም፡፡ ይሄን ማሊያ አድርገው አልተጫወቱበትም፡፡ ነገር ግን ሀገር ፍቅር ማህበር በጠራው ሀገራዊ ስብሰባ ላይ መዝሙር ዘምረውበታል፡፡ ጣሊያን ከገባ በኋላ ማሊያውን ለብሰውት ይተኛሉ፡፡ለነገሩ በጥቆማ እየተነጠቁ ነው፡፡ የቀረውም ሶት ማሊብቻ ነው፡አንድቀን  ተፈሪ መኮንን ለብሰውየተወሰኑትለማመዱሊያኖአስወልቀው ወሰ፡፡ካሳና ተስፋዬ አምልጠው ማሊያውን አተረፉት፡፡አዲሱን ማሊያ ሲገዙ የመጀመሪያዋን ለሁለተኛው በድን ሰጡት፡፡ አዲሱ ሲወሰድባቸውየበፊቱማሊያ ከሁለተኛ ቡድን ማስመለስ አልፈለጉም፡፡ደግሞስ ሁለተኛው ቡድን የታለና ያስመልሳሉ?፡፡ሁሉም ተበታትነዋል፡፡ጊዮርጊስ ገና አልጠነከረም፡ጥሩአቋም ለይ ነበረ፡፡ጣሊያን ሲገባ ነገሮች አንዳልነበሩ ሆነዋል፡፡በዚያ ላይ የክለቡ ተጨዋቾች ቤተሰቦቻቸው እየታደኑ ስለሆነ  እነርሱም ተሳዳጅ ሆነዋል፡፡አንም ጊዮርጊስ የመስራቾቹን የአየለና ጆርጅን እገዛ ይጠይቃል፡፡አየለ አሳዲጊዎቹ በጣሊያን ሰላዮች ክትትል ውስጥ ስለሆኑ ለእሱም አደገኛ ነው፡፡ጆርጅ ደግሞ ለእስር ወም ለግድያ እየተፈለገ በመሆኑ አስቸጋሪ ነው፡፡ስለዚህ መደበቂያ ፈለገና ሲሳደድ ቆይቶ አየለ ባዘጋጀለት አጎቱ ቤት ተሸሽጓል፡፡ ጆርጅ ከባድ ጉንፋን ይዞት ህመሙና ሳሉ አስቸግሮታል፡፡ትኩስ ፈሳሽ ነገር አዘጋቶለት ኩሽና ጉድ ጉድ ሲሉ ነው ሰውየው የመጣባቸው፡፡በሩ እንደገና መኳኳትጀመረ፡፡አየለ ግራ ተጋባሰውየው እንደሆነአውቋል፡፡ሄዶ ከፈተለት፡፡፡ሰውየው ‹‹አባትህ የለም እንዴ?›› አለው

‹‹የሉም››

‹‹የት ሄዱ?››

‹‹ለቅሶ››

‹‹ማን ሞተ?››

‹‹ዘመድነው››   

  አባቱ እንዳልሆኑ ውቃል፡፡ለምንእንዲህ ብሎሰውየውእንደጠየቀው አልገባውም፡፡ አየለ መከራከርአልፈለገም፡ተጠቁሞ እንደመጣአውቋል፡፡እዚህ ከተማ ውስጥ ሹምባሽና ቡሉቅባሽ የሚባሉ ወታደሮች አሉ፡፡አሁን ግቢ ውስጥየገባው ከእነርሱ አንዱ ነው፡፡እነዚህወታደሮች ከአስመራ ነው የመጡት፡፡አማርኛ ስለሚችሉጣሊያኖቹ  በእነርሱ ነው የሚጠቀሙት፡፡ይሄ ወታደር ሰላይ እንደሆሰፈርተኛው ያውቃል፡፡ቤቱን የተዘዋወረ አየ፡፡ወደጓሮ መሄድ ሲጀምር አየለ ስጋት ውስጥ ገባ፡፡ጆርጅ ጥቹ ከታሰሩበት ቦታ ከጭድ ክምሩ ጀርባ ነው የተደበቀው፡፡ ወደዚያ ለማለፍ ጥጆቹገለረግያስፈልጋል፡፡ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ብዙ  ተፈላጊ ሰዎችን ከተደበቁበት ስርቻ ውስጥ ፈልፍለው እንደሚያወጡ በመስማቱ አየለ ስጋቱ ጨመረ፡፡ደግሞም የጆርጅ ጉንፋን ሳል ከተቀሰቀሰ በቀጥታ ከተደበቀበት ይወስዱታል ፡፡የጆርጅነገር ያለቀለትእንደሆነ አመነ፡፡ይሄ ወታደር በመንደሩ ሰው ሁሉ የተጠላ ነው፡፡ጓሮ ሆነው አየለናወታደሩ ያራሉ፡፡ወታደሩ ለአየለ ‹‹አንተ እዚህ እንዴት መጣህ?››አለው

‹‹ሰው ስለሌለ ነው››

‹‹ቤትህ ግን ሌላ ቦታነው አይደል?››

‹‹ዘመዴ ናቸው››

‹‹ቅድም አባትህ ስልህ አዎ አልከኝ››

‹‹እንደአባቴ ስላሳደጉኝ...››

ሰውየውየሆ  ሀገርጠርጥሯል፡፡ወደ ጥጆቹ ሲያይ አየለልቡትር እለ ይርበተበታል፡፡ወታደሩሰው ጠቁሞት እንደመጣ ነው የገመተው፡፡አየለሰራተኛዋን ጠረጠረ፡፡ከሰዓታት በፊትወደ ገበያ ሄዳነውየተመለሰችው፡፡ጆርጅ ደግሞ ለእሷ ጥሩ አመለካከት እንዳለው ያውቃል፡እሷም አትጠላውም፡፡ ግን እሷጠቁማበት ይሆን? ፡፡በዚህ ቅጽበት አንድየጣሊያን ወታደር ወደ ግቢው ዘለቀ፡፡በጣሊያንኛ ካወሩ በኋላ በጥድፊያ ወጡ፡፡አየለ በቁሙ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡ሰዎቹ ሄደናል በሚል ተመልሰው መጥተውርጅን ሊዙት እንደሚችሉ ስላወቀ እስኪርቁጣራት ነበረበት፡፡ከሄዱ በኋላቀስ  ከኋላ በርቀትተከተለ፡፡አቋራጩንአልፈው ዋናው መገድ ደረሱ፡፡አየለ እየተለከለከተመለ፡፡አንድ ካሚን መኪናላይ ሲወጡ አየ፡፡እዚህ አካባቢ አጠቃላይ አሰሳ እንዳለ ገመተ፡እየሮጠ ተመለሰና ጆርጅን ኩርምት ካለበት ስፍራ አወጣው፡፡አውጥቶም ተቃቀፉ፡፡እንደገናምተላቀሱ፡፡ዛሬ ባገኙትምነገ እንደሚይዙት ያውቃል፡ደግሞም ካስፈለገ ያገኙበት ቦታ እንደሚገሉት ይገዋል፡፡ ካለፉትወራቶች ጀምሮለእነርሱልተመቻቸውንና ሰላይ ብለው የሚጠረጥትን  በየቤቱ  ምሽት ላይ እየገቡ ሲገድሉ እንደነበር ሰምቷል፡፡ጆርጅንም እዚሁ ከተደበቀበት አውጥተው ፊቱ ላይ ደፍተውት እንሚሄዱ ሲያስብ እጅግ ሰቀጠጠው ፡፡ሰውየው ከሄደ በኋላ ጆርጅን ከተደበቀበት ጎትቶ ካወጣ በኋላ በመትረፉ ደስ ብሎት ተቃቅፈው ተላቀሱ፡፡ቤተሰቦቹ በአደገኛ ሰላይነትተጠቁሞባቸው እንደታሰሩ ያውቃል፡፡የግቢውን በር በደምብ ከዘጋ በኋላ ወደ ውስጥ ገቡ፡፡አሁን የመጣ አደጋ ሁለቱንም የሚለያይ ነው፡፡አደጋው የጆርጅ ቢሆንም አየለ ላይ አነጥሯል፡፡ቅድም የመጣው ወታደር ጆርጅን ፍለጋ እንደሆነአይጠፋውም፡፡አየለ እሱን እዚህ መደበቁና አሳላፎለመስጠቱ እሱንም ተጠያቂ እደሚያደርገው ያውቃል፡፡ነገር ግን ጓደኛውን አሳልፎ መስጠት እንደሌለበትም ያምናል፡፡እከመጨረሻው ላለመለያየትቃልተገባብተዋል፡፡ይሄ ደግሞ የክለባቸውም ቃል ኪዳን ነው፡፡ አየለየሚመጣውን ነገር ሁሉ ከጆርጅ ጋር ለመጋፈጥ ቆርጧል፡ይሄንን ጆርጅም ያውቃል፡፡በቀጣይ ምን ማድግ እንዳለባቸው መመካከር አለባቸው፡፡ጆርጅ ገና ታዳጊ ወጣት ነው፡፡ደዛም ሆኖ ጣሊያን ካገኘውአይለቀውም፡፡ ሁለቱ ጓደኛሞች ወጥተው ለመሄድ ተዘ፡፡ነገር ግን ቀጣይ ማረፊያቸውን ማቻቸት ላለባቸው፡፡አሁን ያሉበት  ቦታ ሳይነቃበትአልቀረም ቅም ወታደሩ ተጣድፎ ስለወጣ እንጂ በደምብ ቢፈትገኘው ነበር፡፡እናም አሁን ይሄን ቦታ መልቀቅአለባቸው፡፡እነሳ ቤት ወስደው ለመደበቅ ተስ፡፡ነገር ግን እነርሱ ቤትአካባቢላይየሚርመሰመስበት በመሆኑ  ለጊዜው ሀሳባቸውን ሰረዙ፡፡ሁሉም የክለቡ ተጨዋቾች ጆርጅ የደረሰበትን አደጋ ስላወቁ የሚተርፍበትን ነገር ለግዜው እየፈለጉ ነው፡፡ተስፋዬ አክሎክ ጉለሌ ያለ  ዘመዱ ቤቱ በጫካ የተከበበ በመሆኑ አመቺ ነው፡፡ግን እዛ ድረስእንዴት ይሄዳሉ?ደግሞምጣሊያኖችን ካምፕ ማለፍ አለባቸው፡ሹምባሽና ቡልቅባሾች የሚገኙበት መደርም ይሄን መገድሻገሩ በመሆኑ  አደገኛ ነው፡፡በጭለማ ማለፍቻላል ነገር ግን ካምፑን ለመሰለል ነው የመጣችሁት በሚል ሊይዟቸው ስለሚችል ወደዛ ለመሄድ የነበረውን ሀሳብ ሰረዙ፡የጆርጅ ዘመድ የነበረችው ባከሞተ በኋላ ለብቻዋ ትኖራለች፡፡ቤቱ ብዙ ሰውአይመጣም፡፡አየለ እሷ ጋር ሄዶ ሁኔታውን ከነገራት በኋላ ለአይን ያዝ ሲል እዛ ሊወስደውተስማሙ፡፡ከዚያበፊት ግን በክለቡ ጉዳይ መወያየትጀመሩ፡፡ይሄ ሁሌም የሚያደርጉት ነው፡፡ክለቡ ከተመሰረተ ጀምሮ አብረው ባሉበት ግዜ ሁሌም ምን ማድረግእንዳለባቸው ይነጋገራሉ፡፡ሁለቱም ሀሳብ አምጠው የወለዱትን ቡድን ለትልቅ ደረጃ ማብቃት ነው፡በሁለቱም መሀል የሚገኘው ክለቡ ነው፡፡ በቀጣዩ ጉዳይ ሀሳብ ከመለዋወጥ ይለቅ ተቃቅፈው መላቀስ ጀመሩ ፡፡የሚመጣውን አደገኛ ነገር አውውታል፡፡ጣሊያን ከመግባቱ በፊት በእነርሱ የተጠነሰሰውን ክለብ መሰረቱ፡፡በንካራጓደኝታቸው ላይ የክለቡቅር ተጨምሮ  ፍቅራቸው ከፍ ብሎ ነበር፡ሌሎች ጓደኞቻቸውን ቀላቅለው በክለቡ ውጥ ጠቤተሰብነትመስርተዋል፡፡ይሄ ደግሞ ከምንም በላይ አስደሳች ነው፡፡

የሁለቱን ጓደኝነት ይበልጥ ያስተሳሰረውለቡ በመሆኑ ስጊዮርጊስ ማሰባቸው አልቀረምጆርጅ መናገር ጀመረ፡፡‹‹አየለ››አለ

‹‹አቤት››

‹‹እኔን ይዙኛል››

‹‹እና››

‹‹ካገኙኝም ይገሉኛል››

‹‹ደርሱ አትበል››

‹‹ብዙ ወጣቶችን እየገደሉእኮነው››

‹‹አንተን አይነኩህም››

‹‹አንድ ቡሉቅሽ እኛ ቤትመጥነበር››

‹‹እና››

‹‹ቤተሰቦቼ ላይእየዛተ ነበር...ለኔም እንደማቀርልኝ ነግሮኛል››

‹‹አይዞህ አይነኩህም›››

‹‹የክለባችን ነገር ላንተ ነው አደራ የሰጡህ››

በዚህ አስቸጋሪ ሰዓት ስለ ክለቡም በጥብቅ እያሰቡ ነው ደግሞም ክለቡ በራሱ አደጋ ላይ ስለወደቀ አንድ ነገር ማድረግ ፈልገዋል፡፡እዚያው ቤት ሆነው ብዙ ከተነጋገሩ በኋላ አየለ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡

አየለ መገዱና አካባቢውም መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ለአይንያዝሲል ጆርጅን አስተማማኝ ነው ብሎ ወደአሰበው መደበቂያቦታይዞት ሄደ፡፡አየለ ጆርጅንካስገባው በኋላ እንደገናቃቅፈው ተላቀሱ፡፡በነጋታውአየለ ጆርጅ ቤተሰቦች ጋር ሄደ፡፡ወንድሙንድሮስን አገኘው፡፡ቴድሮስ አየለእንዳገኘው ዘሎ አቀፈው‹‹ጆርጅስ?››አለው

‹‹የለም››

‹‹የለምማለት››

‹‹አላየሁትም››

‹‹ምን ማለት ነው?››

‹‹አንተን የት እንዳለ ልጠይቅህ ነው የመጣሁት››

ሰራተኛዋ ወደ ውስጥ ስትገባ አየለ ቴድሮስን ይዞ ወደ ውጭ ወጣ ‹‹ጆርጅ አክስትህ ጋር ነው ያለው፡፡ለማንም እንዳትነግር ››አለው፡፡ቴድሮስ እየሮጠ አክስቱ ቤት ሄደ፡፡ምሽት ቴድሮስ መልእክት ይዞለት መጣ፡፡በነጋታው አየለ መሄድ ነበረበት፡፡በቀን ሶስትናአራትግዜ ቢአይሰለቸውም፡፡ነገር ግን ከተከተሉት ጆርጅን ያገኙታል፡፡በነጋታው ከትምህርት ቤት መልስ አየለወደ ጆርጅ ጋር ሄደ፡፡ጆርጅየተፈሪ መኮንን ተማሪ ነው፡፡አየለ ጊዮርጊስ ትምህት ቤት ነውየሚማረው፡፡ ጣሊያን ከመግባቱ በፊትሁለቱም ከክፍል እንደተለቀቁ መገድ ላይ ይገናኛሉ፡፡አየለ አራት ኪሎ ድረስ በመሄድ ጆርጅን ያመጣዋል፡፡አዳሪ ከሆነም በኋላው ድረስ ሄዶ ይጫወታሉ፡፡በፍጹም ለደቂቃ መለያየት አይፈልጉም፡፡አየለ ከትምህርት ቤት እንደተመለሰ ወደ ጆርጅ አክስት ቤት ሄደ፡፡ገና ወደ ግቢው እንደገባ ጆርጅን ለማግኘትለመተቃቀፍ  ወደ ቤቱ ውሰጥ መሮጥ ጀመረ፡፡ነገር ግን ጆርጅስጥ አልነበረም ምናልባትም ፈታሾች መጥተው ጆርጅ መደበቂያ ቦታ ውሰጥ ተሸሽጎ ይሆናልብሎ አሰበ፡፡ወደ ውሰጥ እንደገባ አክስቱን‹‹  ጆርጅየት ነው ያለው››አለ

‹‹ቁጭ በል››

‹‹ሄጄ ላምጣው?››

‹‹ግድየለም ቄጭ በል››

‹‹ምንድነው ነገሩ››

‹‹ጆርጅ የለም››

‹‹የለም?››

‹‹አዎ››

‹‹የት ሄደ?››

‹‹ዛሬ ጠዋት ወታደሮች ወሰዱት››

‹‹ወሰዱት››

‹‹አዎ››

‹‹እንዴት?››

‹‹በጥቆማ አገኙት››

  አየለ እዚያው ሆኖ እንባው ዱብ ዱብ ማለት ጀመረ፡፡የወደው ጓደኛው በላት እጅ ገብቶ ምን እንደሚያደርጉት ሲያስብ የባሰ አስለቀሰው፡፡አድ የሚወደውን ጓደኛውን ያጣውአየለ ወደ ቤተመለሰ፡፡ምድርና ሰማይ ዞረበት‹‹የክለቡን ነገር አደራ››ያለውን ደጋግሞ አስታወሰ፡፡ክለቡ የሁለቱም ማስወሻ ነው፡፡የጓኝነታቸው ጥብቅ መተሳሰሪያነው፡፡ሩቅያሰቡለት ክለምን ማድረግእንደለበት ግራ ገባው፡፡አንድ ነገር በክለቡ ጉዳይ ሲያስብ ጆርጅን ነው የሚረው፡፡አሁን ጆርጅየለምአየለ ይናገራሉ‹‹.....ጆርጅምሰረና ወደ ኮረም ተወሰደ፡፡ይድነቃቸውም እዚህ አልነበረም፡፡ክለቡ ችግር ላይ ወደቀ፡፡ለግዜው ምን እንደማደርግ ቸገረኝ፡በክለቡ ጉዳብዙሳብምነለዋወጠው ከጆርጅ ጋር ነበር፡፡እሱ ከታሰረበኋላ ሁሉም ነገር ጭለማ ሆነ፡፡››ይላል፡፡አየለ እንደገና የክለቡን ልጆች አሰባስቦ ለማስቀጠልእየተፍጨረጨረ ነው፡፡የክለቡ ንብረት እሱ ቤት እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡ከጆርጅ ጋር የነበረው ወደካሳ ቤት ተዛውሯል፡፡ነ ከሳቤት ሲቃጠል የክለቡም ንብረት አብሮ ወድሟል፡፡አሁን አየለ እጅ አንድ ጠገራ ብር ብቻ ነው የሚገኘው፡፡ ኳሱ እንጨቱ ና ሌላውን ነገር በቃጠሎ ጠፍቷል፡፡እንደገና ጊዮርጊስን የሚጠናከርበት መንገድ ማፈላለግ ጀመረ፡፡አየለ ከግዜ በኋላ ይድነቃቸው ቤት ሄደና መከረ፡፡እንደገናም በክለቡ ላይ ነፍስ ለመዝራት ተንቀሳቀሱ፡፡

የቃል ኪዳን መዝሙር

ስንዱ ገብሩ ሰብስባያመጣቻቸው ወጣቶች የተቀናጁናንቁ ናቸው፡፡ደግሞም  ፍጹም ኢትዮጵያነት የሚንጸባረቅባቸውናሀገራቸውንየሚወዱች ናቸው፡፡አቶ መኮንን ሀብተወልድ ቢሮ ገብታ ከልጆቹ ፊት በመቆም ስለጸባያቸው ስለትምህርት ችሎታቸው ስለጓደኝታቸው በልጆቹ ዙሪያ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ አስረዳቻቸው፡፡ ፋሽስቱ ጣሊያን በሀገራቸው ላይ ይዞ የመጣው አደጋ ያሳሰባቸው አቶ መኮንን ህዝቡን የሚቀሰቀሱበትና ህብረቱን እንዲያጠናክር የሚያስችልበትን ነገር ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ ቅስቀሳ አንዱ መንገድ ነው፡፡ ለመቀስቀስ መዝሙርና ከዚህ ጋር ተያያዥ የሆነ ነገር ይፈልጋሉ፡፡ለዚህ ደግሞ የተሰባሰቡ ታዳጊዎች ያስፈልጋሉ ፡፡ሀሳቡን ለስንዱ ገብሩ ሲነግሯት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በሚል የተሰባሰቡ ታዳጊዎች እንዳሉ ነገረቻቸው፡፡ስለልጆቹ ምን ያህል እንደምታውቅ ጠየቋት ፡፡ ያደራጀቻቸውና ከጅምሩ የእሷን ድጋፍ እየጠየቁ የተቋቋቋሙ መሆኑን ነገረቻቸው፡አቶ መኮንን ሀብተወልድም ልጆቹን አምጥታ እንድታሰዋውቃቸው  ነገሯት፡፡፡ያን ግዜ አቶ መኮንን የሀገር ፍቅር ማህበርን ከጓደኞቻቸው ጋር መስረተው ገና እየተደራጁ ነበር፡፡ጣሊያን ደግሞ ሀገርን ለመውረር መጣሁ መጣሁ እያለ ያኮበኮበበት ግዜ  ነበርና ስንዱም አቶ መኮንን ጋር የቡድኑን ተጫዋቾች ወስዳ አስተዋቀወቻቸው፡፡አቶ መኮንንም የልጆቹን ቤተሰብ፤ አላማቸውንና ፍላጎታቸውን ከጠየቁ በኋላ ከእነርሱ ጋር በምን መንገድ መስራት እንደሚገባቸው ነገሯቸው፡፡የቡድኑ መስራችና  ጸሀፊአየለ አትናሽ ይናገራሉ‹‹... ከአቶ መኮንን ጋር ከተዋወቅን በኋላ ሀገራችን አደጋ ላይ ነች የሁላችሁንም ትብብር እንፈልጋለን በሚል ነገሩን ያን ግዜ ከአራራት ጋር የመጀመሪያውን ጨዋታ ካደረግን በኋላ ብዙዎቹ ታዳጊዎች እኛ ጋር ለመቀላቀል ጥያቄ ያቀረቡበት ግዜ ነበር፡፡ የመጀመሪያውን ማሊያችንን ለሁለተኛው ቡድን ከሰጠን በኋላ አዲሱን ማሊያ ለማሰፋት በዝግጅት ላይ ነበርን፡፡ ከአቶ መኮንን ቢሮ ከወጣን በኋላ ለቀጣዩ ስራቀኝጌታ ዮፍታሄና ወይዘሮ ስንዱ ገብሩ ናቸው ያሰባሰቡን፡፡ማሊያውን በባንድራ እንድናሰራመከሩን እነርሱ ናቸው፡፡ማሊያውን ካሰራን በኋላ  ምኒሊክ ተፈሪመኮንንና ጊዮርጊስ ትምህርት ቤት ወስደው በተማሪዎች ፊት እንድንዘምር አረጉን፡፡ስቀሳ ነው የተካሄደው፡፡ሰኞ እለት አቶ መኮንን ሀብተወልድ ጋርበድጋሚሄድን  እሳቸውካነጋገርን በኋላ አቶ አገኘሁ እንግዳን አስጠተው ግጥም እንናጠና አደረጉን፡፡አንዷን ግጥም አስታሳታለሁ

                                    ኼ የመጣው ጠላት ሳይደርስ ከጠረፍ-

                                    ተነሱ እንነሳ ደማችን ይፍሰስ

                                  እንደ ሰኔ ውሃ እንደ ሀምሌ ጎርፍ

                                   ይሂድ ይቀላቀል ከአባይ ጋር ይውረድ

                                   ነጻነት ያጣ ህዝብ አይባልም ወንድ......የሚለው አንዱ ነው፡፡

በየካቲት ወር ፒያሳከጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በታችከኳስ ሜዳው ካለበት ትንሽ ከፍ ብሎ ዛፍ ስር ህዝቡ በየቀኑ ይሰባሰብ ነበር፡፡በአንደኛው ፕሮግራም አዲሱ ማሊችንን እንዳደረግን እንድዘምር ተደረገ፡፡በየቀኑ ንጋቷ ከልካይ እዚያ ታንጎራጉር ነበር፡፡በሀገራችንላት ስለገባና መጥፎ ነገር ስላንዣበበ ህዝቡም እሷ ስትዘፍን ያለቅስ ነበር፡፡እኛም ስንዘመር እነባን ነው፡፡የህዝቡ ስሜት እጅግ የተጎዳ ነበር፡፡........በዚህ መልክ በተለያየ ቀን እየመጣን እንዘምራለን፡፡የለበስነውን ባንድራው ያለበት ማሊያ ሲመለከት ህዝቡ ቢደስትም የጠላትን መምጣት አይቀሬ በመሆኑ ሀዘን ነበር፡፡ያን ግዜሀገር ፍቅርቲያትር ማህበርመመስረቱ ስለነበር ፒያሳ አፋፋ ላይ ነበር አዳራሹ፡፡ህዝቡ እየተሰበሰበ ይወያያል፡፡ ከውይይቱ በፊትና በኋላ እኛ ዛፉ ስር ባለቸው ትንሽ ቦታ ላይ ሆነን እንዘምራለን፡፡መዝሙሩን ያለማምደን የነበረው ሰዓሊ አገኘሁ እንግዳ ነበር፡፡ቡድናችን እየተሰባሰበ የእግር ኳሱን ይለማመድ ነበር፡፡ከአርመን በኋላ ሁለተኛውን ግጥሚያ ከህንዶች ቡድን ጋር ነበር ለመጋጠም ቀጠሮ የያዝነው፡፡ ነግር ግን እነርሱ አልተሟላንም ፤አልተዘጋጀንም በሚል ምክንያት እየበዛ ሳይደረግ ቀረ፡፡ ሌላ ቡድን ስናፈላለግ ኦሎምፒያኮስን ጠየቅን፡፡በየካቲት መጨረሻ ከእነርሱ ጋር ለመጫወት እተዘጋጀን ሳለ አይጋዝ ድጋሚ እንድንጫወት ጠየቀን፡፡ሀይጋዝ የአራራት አርመን ተጨዋች ነው፡፡በመጀመሪያ ጨዋታ ስላሸነፍናቸው በደምብ ተዘጋጅተው እንደገና እንድንገጥማቸው ስለጠየቁን የኦሎምፒያኮስን አቆየነው፡፡ ነገር ግን ከአርመን ጋር ለመጋጠም በያዝነው ቀጠሮ ሀገር ፍቅርትልቅ ዝግጅት አድርጎ ስለነበር እዚያ እንድንገኝ ፕሮግራም ስለተያዘልን የአርመኑ ጨዋታ ተሰረዘ፡፡  ኦሎምፒያኮስም በድጋሚ ጠየቀን፡፡ ተስማማንና ቀን ተቆረጠ ነገር ግን ጠላት እየገፋ ስለመጣ በዋናው ከተማ ሸብር እነገሰ ስለሄደ ጨዋታው ሳይደረግ ቀረ፡፡ እኛም ከግጥሚያው ይልቅ ለሀገራዊ ጥሪ ምለሽ የምንሰጥበት ግዜ በመሆኑ የአቶ መኮንን ትእዛዝ ቶሎ ቶሎ ሲመጣ እየሄድን በመዘመርና ታዳጊ ወጣቶችን ሀገራዊ በሆነ ጉዳይ በየትምህርት ቤቱ ማሊያውን እየለበስን በመሄድ ቅስቀሳ በማድረግ ስራ ላይ ስለተጠመድን የግጥሚያው ነገር ብዙ የተሳካ አልነበረም፡፡ጠላት ከወጣ በኋላ አቶ መኮንን ሀብተወልድ ከፈንሳይ ሲመለሱ ቢሮአው ቡድኑን አስጠሩ፡፡ ሁላችንም ተሰብስበን ሄድን አንድሰዓት ያህል አነጋገሩን፡፡አሁን የምንለብሰውን ማሊያ  ምንአይነትእንደሆንጠየቁን፡፡የበፊቱን ጣሊያን አንደቀማንነገርናቸው ፡፡የኛደጋፊና ተዋቾች በጣሊያን ደህንቶችና ፖሊሶች መታሰራቸውንመገደላቸውን አስረዳናቸው በጣም አዘኑ፡፡ አሁንጠንካራ የእግር ኳስ ቡድን እንዳለን ተናገርን፡፡ለቡድናችየገንዘብ እርዳታ ከሰጡን በኋላ ከእኛጎን እንደሚቆሙ ነገሩን፡፡በሌላ ቀን ቀኝፎታሄንጉሴ፤አገእንግዳእንዲሁም ቀኛዝማች መገሻ ከፈላ ባሉበት የተጠሩ ሌሎች ሰዎች በተሰበሰቡበት ቡድናችን በአምስቱ አመት የጠላት አገዛዝ ዘመን ያደረግነውን በጎ ስራ ካስዱ በኋላ ክለባችን እንዲሚረዱ ነገሩን፡፡ቀኝ ጌታ ዮፍታና አገኘሁ እንግዳ ያን ግዜ መዝሙር ስንዘምር የነበረውን ሁኔታ አስታውሰው ብዙ አመሰገኑን ፡፡አዲሱ የብሄራዊ መዝሙር ሲወጣ የጊዮርጊስ ተዋቾች ተጠርተን እንድናጠና ተደረገ፡፡የተወሰኑ ወጣቶች ከእኛ ጋር ተቀላቅለውነበር፡፡ይሄም የሆነው  የሰው ቁጥር ከ20 መብለጥ ስላለበት ነው ፡፡ከዚያ መዝሙሩን ቤተንግስት ሄደን ጃንሆይ ፊት ዘመርን ለቡድናችን 30 ጠገራ ብር ተሸለምን፡፡ጠላት ከወጣ በኋላ‹‹እነዚያንድራ ለብሰው የሚዘምሩት ልጆች የትቸው? እየተባለ ብዙዎቹ እጉን ይመጡ ነበር፡፡በዚህ የተነሳ ቡደናን ሀገራዊ በሆነው ጉዳይብዙዎቹደግፉን ነበር፡፡ቅዱስ ጊዮርጊስ በህዝቡ የመወደዱ ሚስጥ በሜዳ ላይ ከነበረው ውጤት በተጨማሪ እነዚህ ነገሮችም ትልቅ ቦታ ነበራቸው››ይላሉ የቡድኑ መስራች  አየለ አትናሽ፡፡    

አንድ ፊያሽኮ ነዳጅ

እነዚህ ሁለት ጓደኛሞች እኩዮች ናቸው ፡፡በሀሳብ በጣም ይግባባሉ፡፡ አንድ ሰፈር ነው ያሉት፡፡ በኋላ ግን አንደኛው ቤተሰቦቹ ሌላ አካባቢ ሲሄዱ መገናኘት አልቻሉም ነበር፡፡ሲፈላለጉ አንድ ቀን አንድ ሰው ተከትለው ሲሄዱ ድንገት ተገናኙ፡፡የሚከተሉት ሰው ኢትዮጵያዊ አይደለም፡፡አሜሪካዊ ነው ፡፡ጥቁር አሜሪካዊ፡፡ሰውየው ወደ አርመን ኮሚኒቲ ነበር የሚሄደው፡፡አርመኖች አመታዊ በዓል ያከብራሉ፡፡ የሙዚቃና የስፖርት ድግስ አላቸው፡፡ እርስ በእርስ የእግር ኳስ ግጥሚያ ያደርጋሉ፡፤ይሄን ውድድር በዳኝነት እንዲመራ አሜሪካዊውን ሰውዬ ጋብዘውታል፡፡ሰውየው ብዙዎቹ ጆንግ ይሉታል፡፡ቅጽል ስሙ ነው፡፡ለምን ብለው እንደሰየሙት ባይታወቀም፡፡ በዚህ ስሙ እሱም ተቀብሎት ይጠራበታል፡፡አሜሪካው ሰው የሚመጣው ራቅ ካለ ቦታ ነው የሚጠቀመው በፈረስ ነው፡፡ውድድሩን ለመምራት ቦታው ላይ ሲደርስ  ከፈረሱ ላይ ወርዶ ፈረሱን ከአንድ ጥግ እንጨቱ ላይ ማሰር ነበረበት፡፡ ነገር ግን ከፈረሱ አልወረደም፡፡ወደ ሜዳ የገባውም በፈረሱ ላይ እንደተቀመጠ ነው፡፡ተጋጣሚዎቹ ስለሚያውቁ አልገረማቸውም፡፡ነገር ግን አሜሪካዊውን ሰውዬ ተከትለው ከመጡት ወጣቶች ውስጥ ወሬውን ስለሰሙ ወደ ግጥሚያው ቦታ ተከትለውት መጡ ፡፡፡ሁለቱ ታዳጊዎች አልተያዩም ነበር፡፡ፈረሱ ላይ ያለውን ሰው እያዩ ሲጓዙ ድንገት ተያዩ ፡፡ቀድሞ ያየው አመለወርቅ ነበር፡፡በፈገግታ ‹‹ይድነቃቸው!!!!!›› አለ

‹‹እንዴት ነው››

‹‹አለሁ ››

‹‹ተጠፋፋን››

‹‹የት ሄደህ ነው››

‹‹ሰፈር ቀይረን››

‹‹የት ሰፈር››

‹‹አምስት ኪሎ ነው››

                  ይድነቃቸውና አመለ፡ ከልጅነት ጀምሮ ነው የሚተዋወቁት ድንገት ተለያይተው አሁን አሜሪካዊውን እግር ኳስ አልቢትር ሲከተሉ ድንገት ተገናኙ፡፡ሁለቱም ስለሰውየው ወሬ ሰምተዋል፡፡ጎበዝ ዳኛ ነው ነገር ግን ክብደቱ በጣም የገዘፈና የወፈረ በመሆኑ ሮጦ ማጫወት ስለማይችል ፈረስ ላይ ሆኖ ነው የሚያጫውተው፡፡ብዙ ግዜ የተፈሪ መኮንን መምህራን  ከምኒሊክ መመህራን ሲጫወቱ እየመጣ የሚዳኘው እርሱ ነው፡፡ያን ግዜ የሀባሻ ቡድኖች ስላልተቋቋሙ የትምህርት ቤት መምህራንን ነበር የሚያጫውተው፡፡የዚያን ቀን አመለና ይድነቃቸው እያወሩ ተመለሱ፡፡ ይድነቃቸው ‹‹ሰፈራችን እኮ ቡድን ተቋቋመ››አለ

‹‹የምን››

‹‹የእግር ኳስ››

‹‹እንዴት አይነት?››

‹‹እንደ አርመን››

‹‹እነማናቸው››

‹‹ተስፋዬ፤አየለ፤ጆርጅ......››.

‹‹ባለፈው ግዜ ከአርመን ጋር ተጫወቱ የተባለው ቡድን ነው?››

‹‹ትክክል››

‹‹አዲስ ነገር ነው››

‹‹አዎ››

‹‹ታስገቡኛላችሁ?››

‹‹ልጠይቃቸው››

አመለወርቅ ከይድነቃቸው ጋር አንድ ክለብ ለመጫወት በጣም ይፈልጋል፡፡ከአርመኑ ጨዋታ በኋላ ጊዮርጊስ መነጋገሪያ በመሆኑ ብዙ ታዳጊዎች ጥያቄ እያቀረቡ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ክለቡ ዘለቄታ እንደሌለውና እንደማይቀጥል ያወሩ ነበር፡፡አመለወርቅ ኳስ ሲጫወት ጎበዝ ነው፡፡ የእግር ኳስ ጥበብ አለው፡፡ ደግሞም ጸባዩ ወርቅ ነው፡፡ ይድነቃቸው የሚወደውም በጸባዩ ጭምር ነው፡አመለወርቅ  የይድነቃቸውን መልስ ሳያገኝ ጣሊያን ገባ፡፡ ከአንዱ ሰፈር ወደ ሌላ መዘዋወር ጣሊያን ማእቀብ እየጣለ ነው ፡፡ከአመት በኋላ ጣሊያን በየሰፈሩ ቡድን ሲያቋቋም አመለወቅ ለስድስት ኪሎ ይደድነቃቸው ለደጃች ውቤ  ተሰለፉ፡፡ሁለቱ ቡድኖች ባላንጣ ሆኑ በተገናኙ ቁጥር ጸብ አይጠፋውም፡፡ እርስ በእርስ ይጋጫሉ ይደባደባሉ ፡፡ጣሊያን ደግሞ መደባደባቸውንና መጫረሳቸውን  ይወደዋል፡፡አንዱ ቡድን የሌላውን ተጨዋች ይሰድባል፡ ይወቅሳል፡፡ በመጥፎ አይን ያለያያሉ ፡፡ ወሬውን የሚያራግቡት የጣሊያን ሰዎች ነበሩ፡፡ በሁለቱ ቡድኖች ድንበር ተለይቶ ተጫዋቾች በተኳተረፉበትና በማይነጋገሩበት ግዜ እንኳን አመለወርቅና ይድነቃቸው ጓደኛሞች ናቸው፡፡ከሜዳ ውጭ አብረው ይውላሉ፡፡ ብዙዎቹ መቀራረባቸውን ባይወዱላቸውም ሁለቱ ግን የሚወራባቸውን ትተው አበረው ይውላሉ፡፡የስድስት ኪሎ ቡድን አሳዳሪዎች ለአመለወርቅ ከይድነቃቸው ጋር እንዳይውል ቢነግሩት አልተመለሰም፡፡አመለወርቅ ይድነቃቸውን ብቻ ሳይሆን የባላንጣውን ጊዮርጊስን ቡድንም በጣም ይወዳል፡፡ የክለብ ጓደኞቹ‹‹እኛ ጋር እየተጫወተ ልቡ ጊዮርጊስ ጋር ነው›› ይሉታል ፡፡አመለወቅ ይናገራል ‹‹........የጊዮርጊስ ቡድን ተጫዋቾች ችሎታቸው ብቻ ሳይሆን ህብረታቸው ያስቀናል፡፡፡የብዙዎቹ ወጣትና ታዳጊ መነጋገሪያ ነበሩ፡፡በእርግጥ ተጨዋች ጥራትና በአያያዝ የእኛ ክለብ ከጊዮርጊስ የተሻለ ነው፡፡የቡድናቸውን ስም በሰፈሩ መጠሪያ ስድስት ኪሎ ይባል እንጂ ብዙዎቹ ኮኛክ አሎቮ ነው የሚሉት ፡፡ኮኛክ አሎቮ መጠጥ ፋብሪካ ነው ፡፡የድርጅቱ ባለቤት ሲኞር ፋኑቺ ነው የሚረዳንና ያቋቋመን፡፡በግጥሚያና በትሬኒንግ ግዜ ድርጅቱ ውስጥ ባለው ክበብ ምግብ እንበላለን፡፡ ወተት ወደ ቤት ይዘን እንሄዳለን በአመት መጨረሻ ሙሉ ልብስ ያሰፋልናል፡፡ለሲኒማ ተብሎ ገንዘብ ይሰጠናል፡፡ ለተማሪዎች ደብተር ይገዛል፡፡ ለህክምና ይከፈልልናል፡፡አያየዙ ጥሩ ነው፡፡ ጊዮርጊስ ግን ለግጥሚያ ሆነ ለትሬኒንግ ምግብ አያገኙም፡፡ ወተትም የላቸውም ፡፡ልብስ ቀርቶ ህክምና ወጪ አያገኙም፡፡፡አንድ ቀን ተስፋዬ ተጎድቶ ለማሳከም ስንት ስቃይ እንዳዩ አውቃለሁ፡፡ ግን ምንም ባይኖራቸውም ህብረት አላቸው፡፡ ሰው ይወዳቸዋል፡፡ሰዎች የኛን ቡድን ባንዳ እያሉ ይናገራሉ፡፡ አንዳንዱ የጣሊያን ፍርፋሪ ለቃሚ ይሉናል፡፡ያን ግዜ ጊዮርጊስ የአርበኞች ቡድን ነው የሚባለው ፡፡ብዙው ደጋፊያቸው ከሜዳ በሰላዮች እየተለቀመ ሄዷል፡፡ ተጫዋቾችም ለአርበኞች መረጃ አቀብለዋል ተብሎ ተይዞባቸዋል፡፡ህዝቡ ደግሞ በጣም ይወዳቸዋል፡፡እነርሱ ባሸነፉ ቁጥር ከኳስ ሜዳ እስከ ሰፈራቸው እስኪደርሱ በየሰፈሩ ያሉ ወጣቶች እነርሱን ተከትለው እየጨፈሩ እናቶች እና መንገደኛው እያጨበጨበላቸው ነው የሚሄዱት፡፡ እኛ፤ ጉለሌ ወይም ቀበና ሲያሸንፍ አጀብም የለም፡፡ በተለይ እኛ አሸንፈን ከመርካቶ ወደ ሰፈራችን ስንሄድ መንገድ ላይ ድንጋይ  ይወረውሩብናል፡፡ጊዮርጊስ ከህዝብ ያገኘው ትልቅ ተቀባይነት ሁሌም ያስቀናኝ ነበር፡፡በተለይ ጄኔራል ዊንጌት ጣሊያን ከወጣ በኋላ እንደሸለማቸው ስናውቅ በጣም አስቀናን ፡፡ከጊዜ በኋላ በይድነቃቸው አማካይነት ጊዮርጊስን ተቀለቀልኩ፡፡ ብቻዬን አልነበረም ወንድሜ አፈወርቅም ከስድሰት ኪሎ ቡድን ወደ ጊዮርጊስ ገባ፡፡ በእርግጥ ቡድናችን የለም ፡ጣሊያን ሲወጣ  ስድስት ኪሎ ፈረሰ፡፡ ምክንያቱ በእነርሱ ድጋፍ የተቋቋመ ነበር፡፡ጊዮርጊስ በመግባቴ በጣም ነው የተደሰትኩት፡፡ያንግዜ ወታደር ነበርኩ፡፡ነገር ግን ከሶስት አመት በኋለ ጊዮርጊስ የምንጫወተውን ወታደሮች ከእንግዲህ እዛ እንዳትጫወቱ ብለው አገዱን፡፡ያን ግዜ ውሳኔውን ስሰማ በጣም ተናደድኩ፡፡ነገሩ በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡አለቆች  እኔን ጠርተው ከዛሬ ጀምሮ ከይድነቃቸው ጋር ብትታይ ክፍለ ሀገር ነው የምንልክህ ፡፡ በዚህ ብቻ አንተውህም  ከባድ ቅጣት ይጣልብሀል አሉኝ፡፡ግን እንዴት ከይድነቃቸው ሊነጥሉኝ ይፈልጋሉ፡፡ትእዛዙ ከባድ በመሆኑ ለአንድ ሳምንት ይድነቃቸውን ሳላገኝ ቀረሁ፡፡ከዚህ በፊት እንዲህ ተደርጎ አያውቅም በቀን በቀን ፒያሳ ስፖርተኞች የሚሰባሰቡት ካፌ ሳንቀጣጠር እንገናኛለን››ይላል አመለወርቅ፡፡

ሁለቱ የሚዋደዱትን ጓደኞች ከጣሊያን ግዜ ጀምሮ ለመለያየት ተሞክሮ ነበር፡፡ እነርሱ ግን አብረው ቆዩ ፡፡በኋላ ግን ከወታደር ክፍሉ የመጣው ማስጠንቀቂያ አመለወርቅ ላይ ስጋት ፈጠረ ፡፡ደግሞም በእርሱ ላይ ሰው ተመድቦ እንደሚከታተሉት ያውቃል፡፡አንድ ቀን ፍቃድ ተሰጥቶት ቤተሰቦቹን ሊጠይቅ ወደ ሰፈሩ ሄደ፡፡ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው ጀምሮ ቀደም ሲል ይሄድበት የነበረውን መንገድ ቀይሯል፡፡ከመሀንዲስ ተነስቶ ፒያሳን ሳይረግጥ በአሮጌው ቄራ አድርጎ በፓርላማ  አቋርጦ  በአምስት ኪሎ  አድርጎ ሰፈሩ ይገባል፡፡ዛሬም ቤተሰቦቹን ሊጠይቅ ከመሀንዲስ ተነሳ፡፡ የቄራን መንገድ ያዘ ነገር ግን ሀሳቡን ቀየረ ወደ ፒያሳ አመራ፡፡በራስ መኮንን ድልድይ አቋርጦ ወደ ሰፈሩ ይገባል፡፡ ቅርብ የሚሆነውም በዚህ መንገድ መሄድ ነው፡፡የራስ መኮንን ድልድይን አልፎ ሽቅብ ወደ ላይ እየወጣ ሳለ አንድ ሰው ስሙን ሲጠራ ሰማ ፡፡ይድነቃቸው ነው፡፡አመለወርቅ ፈገግ አለ፡፡ከልብ የሚወደው ጓደኛው ነው፡፡አመለወርቅ በሁለት ነገር መሀል ቆመ፡፡ከልብ በሚወደው ጓደኛ እና በአለቆቹ ማሰጠንቀቂያ፡፡ይድነቃቸው ስለ አመለወርቅ እገዳ አያውቅም፡፡አመለወርቅም አልነገረውም፡፡ደግሞም በቅርቡ መቻልና ጊዮርጊስ የጥሎ ማለፍ ወሳኝ ጨዋታ አለባቸው፡፡ሁለቱም የክለባቸው ቁልፍ ተዋቾች ናቸው፡፡ደግሞም እገዳው ባይኖር እንኳን ሁለቱ መገናኘት የለባቸውም፡፡ ድነቃቸው ሞተር ሳይክል ላይሆኖ ነው የሚናግረው፡፡‹‹አመለወርቅ ና ተሳፈር!!!››አለው

‹‹ወደ ቤት ልሄድ ነው››

‹‹በኋላትሄዳለህ››

‹‹ይቅርብኝ››

አመለወርቅ ከልቡ አልነበረም፡፡ ጓደኛውን ማግኘቱ ደስ ብሎታል፡፡ ደግሞም ናፍቆታል፡፡ ይቅርብኝ ወደ ቤት ልሂድ እያለ የሚራመደው ግን ወደ ይድነቃቸው ነው፡፡ይድነቃቸው በጓደኛው ሁኔታ ተገርሞ‹‹ምነው አዲስ ጠባይ አመጣህ ፡፡ፒያሳ ስትመጣ ሳታናግረኝ አትሄድም ነበር፡፡ አሁን ግን ቤቴን አልፈህ  ወሰፈርህ እየሄድክ ነው››አለው፡አመለወርቅ ጉዳዩን ሊነግረው አልፈለገም የተባለውን ማድረግ ነበረበትሞተር ሳይክሉ ኋላ ሄዶ ተፈናጠጠ፡፡ይሄ ቦታ የአመለወርቅ ነው፡፡ማንም ሰው እዚህ ቦታ አይቀመጥም፡፡የአለቆቹን ትእዛዝ ትቶ ጓደኛውን ተቀላቀለ፡፡ዛሬህች ሞተር ሳይክል ለይድነቃቸው የመጨረሻ ጉዞዋን የሚያደርግበት ነው፡፡የሚሰራው ጤና ጥበቃ ሚንስር ነው ፡፡ድርጅቱ ለመመላለሻ ሞተር ሳይክሉን እንዲጠቀምበት ተሰጥቶት ነበር፡፡አሁን ግን ስራውን ስለለቀቀ መስሪያ ቤቱ ሞተሩን እንዲመልስ ነግሮታል፡፡ይድነቃቸው ከራሱ ወጪ አንድፋሽኮ ነዳጅ ሞልቶበት ነበር፡፡ሞተር ሳይክሉን ነገ ስለሚመልስ ነዳጁን መጨረስ ነበረበት፡፡ለመጨረስ ደግሞንሸራሸር አለበት፡፡ይድነቃቸው ሞተሩንከቤቱ እንዳወጣ ነበር አመለወርን ያገኘው፡፡አመለወርቅ የአለቆቹን ትእዝ ትቶ ተፈናጠጠና፡፡ወሬውን ጀመረ ‹‹የት ነው የምንሄደው?››አለ

‹‹ሽርሽር››

‹‹ስራ አትገባምንዴ?

‹‹ዛሬ እረፍት ነው››

ሁለቱ እያወሩ ወደ አራት ኪሎ ሄዱ፡፡እንደገናም ወደ ስድስት ኪሎ አመሩ፡፡ጉዟቸው አላማ የሌለው በመሆኑ አመለወርቅበድጋሚመጠየቅ ጀመረ፡፡‹‹ የት ነው የምንሄደው?››አለ

‹‹አላውቅም››

‹‹አላውም ማለት››

‹‹ዝምብዬ››

‹‹አልገባኝም››

‹‹ነዳጁን ለመጨረስ ነው››

‹‹ለምን››

‹‹ለመስሪያ ቤቱ ነገ ልመልስ ነው››

‹‹ልትለቅ ነው?››

‹‹አዎ››

‹‹ለዚህ እነው የምንዞረው››

‹‹ብዙ ነዳጅ አለው››

‹‹አዎ››

‹‹ቶሎ ለመጨረስ ነው የፈለግከው››

‹‹አዎ››

‹‹እንዲህሆነ በፍጥነት ንዳው››

‹‹ሲፈጥን ነዳጁ ቶሎ ያልቃል?››

‹‹አዎ››

‹‹በምን አወቅክ?››

‹‹ከእንግሊዞችወታደሮችጋር አይደል የምሰራው!!!!፡፡ እነርሱ ሲያወሩ ሰማሁኝ››

ይድነቃቸው አመለ ያለውን ሰማው ፡፡ሰምቶም ማፍጠን ጀመረ፡፡ሞተሯፍጥነት እበረረ ከስድስት ከሎ ወደ አራትኪሎእንዲህ እየሰፈሩ መብረር ጀ፡፡አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ጋር ሲደርስ አንድ ሰው መንገዱን አቋርጦ ድንገትሲገባ ሞተሯ አጠገቡ ደርሳ ነበር፡፡እየፈጠነች የመጣችውሞተርሰውየውን በሀይል ገጨችው፡፡ሞተሯ ላይ የነበሩት ሁለት ጓደኛሞች በአየርላይ ተንሳፈው ጢሻ ውስጥ ተወረወሩ፡፡አመለ ከዛፍ ጋር ተጋጭቶ መሬት ተፈጠፈጠ፡፡ ይድነቃቸው ከመሬት ጋር ተጋቶ ጉድባ ወስጥ ወደቀ፡፡ሁለቱም ሰውነታቸው በደም ተበከለ፡፡ሁለቱምምን እንደተፈጠረም አውቁም ነበር፡፡ ይድነቃቸው ሆስፒታል ገባ፡አመለወርቅ ግን ወደ ህክምና መሄድ አልቻለም፡፡ምክንያቱ ደግሞሄ ነገር አለቆቹ ጋር ከደረሰ የሚደርሰበትን ነገር ያውቃል፡፡ደሙን እያዘራ እንደነገጠ ከአካባው ራቀ፡፡እያነከሰ ወደ ካምመለሰ፡፡በዋናው በር ከገባ ሰዎች ሊያዩት ነው፡፡፡ በኋለኛው አጥር በኩል ዘሎ ወደ  ውስጥ ገባ፡፡ ታላቅ ወንድሙ አፈወርቅ ይባላል፡፡ አብረው ነበር ውትድርና የተቀጠሩት፡፡ እሱን ጠራውና ጉዳዩን ነገረው፡፡ ልብሱን አውልቆ አሳየው፡፡ወንድምየው ሰውነቱንጥቦ አልል ቀብቶት አልጋ ላይ አስተኛው፡፡የሆድ ህመም እንደገጠመው ለጓደኞቹ ነግሮ አንድ ቀን አለፈ፡፡ለጉዳቱ አንድ ምክያት መስጠት ነበረበት፡፡ዛፍ ሲወጣ ቅርንጫፍ ተገንጥሎ መሬት እንደወደቀአስወራ ፡፡ ሁሉም ጉዳዩን አምነው ተቀበሉ፡፡ ነገር ግን አለቆቹ ደረሱበት፡፡ እድ እለት ከጊዮርጊስ ጋር በተደረገ ጨዋታ ክፍለ ሀገር እንዳይላክ ከነቁስሉ ተወተ፡፡ማስቆጠሩከቅት ተረፈ፡፡ ለይድነቃቸው ብዙ ቀን ሆስፒታል ቆየ፡የኢትዮጵያ ቡድን ወደ ጅቡቲ ለጨዋታ ሲሄድ ሳጓዝ ቀረ፡ ለይድነቃቸውኢትዮጵቡድን  ወደ ውጭ ሲወጣ የመጀመሪነበር፡፡አንድ ፊያሽኮ ነዳጅ ለመጨረስ በሚል ሁለቱ ጓደኛሞች ከፍተኛውን አደጋ ተጋፈጡ፡፡ አንድ ፊያሽኮ ነዳጅ ከአንድ ሊትር ከፍለ ነው፡፡አደጋው ግን ከነዳጁ በላይ ነበር፡፡

አራተኛው ሆላንዳዊ ፈረሰኞቹ ቤት ገብተዋል

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ረዥም ጉዞን ለመጓዝ ያለውን ዕቅድ ለማሳካት ሰፊ ልምድ ያላቸውን የውጭ ሀገር አሰልጣኞችን ማምጣት ከጀመረ ሰንበትበት በሏል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2008 ዓ.ም ለሚጠብቀው የአህጉራዊ እና የሀገር ውስጥ ውድድሮች እንደመሩት ሆላንዳዊውን አሰልጣኝ ማርቲን ኩፕማን ከቀጠረ ሁለት ወር ሆኖታል፡፡ እኛም ለአንባቢዎቻችን ይረዳ ዘንድ አዲሱን አሰልጣኝ ለዛሬ እንግዳችን አድርገን ጋብዘናቸዋል፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     በመጀመሪያ ደረጃ ለልሳነ ጊዮርጊስ ጋዜጣ አንባቢያን እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ስም እንኳን ደህና መጡ

ማርቲን፡-      አመሰግናለሁ

ል.ጊ.ዮ፡-     የት ነው የተወለዱት

ማርቲን፡-      የተወለድኩት እ.ኤ.አ 1956 በሆላንድ ውስጥ በምትገኘው ዌዝፕ ከተማ ነው

ል.ጊ.ዮ፡-     ወደ እግር ኳስ እንዴት መጡ

ማርቲን፡-      በልጅነቴ እንደማንኛውም ሆላንዳዊ እግር ኳስን በህፃናት እግር ኳስ ማሰልጠኛ ውስጥ ገብቼ ሰልጥኛለሁ፡፡ ከዚያም ከ1976-1982 ጐ ኤሄድ ኤግልስ ለተባለው የሆላንድ ቡድን የመጀመሪያ የፕሮፌሽል ተጨዋችነት ፊርማዬን በ18 አመቴ ተፈራርሜ ተጫውቼያለሁ፡፡ ከዚያም ኤፍሴ ቲዌንቲ ለተባለው የሆላንድ ቡድን ከ1982 – 1990 ድረስ ተጫውቼ የመጨረሻ ቡድኔ የሆነውን ካምቡር እግር ኳስ ቡድንን እስከ 1991 ድረስ በመሀል አማካይነት እና በመሀል ተከላካይነት ማገልገል ችያለሁ፡፡ በአጠቃላይ ለ15 አመታት በዋና ቡድን ውስጥ በትልቅ ደረጃ ተጫውቻለሁ፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     ስራዎትን ከተጨዋችነት ወደ አሰልጣኝነት ለመቀየር ብዙ ጊዜ ወሰደቦት

ማርቲን፡-      ብዙም አልፈጀብኝም በተለይም በመጨረሻው አመት የተጨዋችነት ዘመኔ የአሰልጣኝነት ትምህርት ከመውሰዴም ባሻገር የካምቡር ወጣት ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት በኋላም የዋናውን ካምቡር ቡድን በምክትል አሰልጣኝነት በመስራት የአሰልጣኝነት ዘመን ጀምሬያለሁ፡፡ ከዚያም በኋላ ሆላንድ ውስጥ ያሉትን ጐ ኤ ሄድ ኤግልስ እና ኤርሲ ቦሰክን የመሳሰሉ ክለቦችን በማሰልጠን ልምዴን አግኝቻለሁ፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     የአፍሪካ የአሰልጣኝነት ልምድዎ ምን ይመስላል

ማርቲን፡-      በአፍሪካ ረዘም ያለ አመትን አሳልፌያለሁ፡፡ አህጉራችሁ እጅግ ድንቅ ተሰጥኦ ያላቸው ተጨዋቾች ባለቤት ናት፡፡ ለዚህም ሆላንድ እና ፈረንሳይ ሊግ ውስጥ የሚጫወቱ ተጨዋቾችን በአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡ እኔም በተለይም ከ2000 ጀምሮ በኮንጐው አ ኤስ ቪታ ክለብ፣ በጋና የወጣቶች መልማይ በመሆን የሰራሁ ሲሆን ከአህጉር አፍሪካ በሳውድ ውጭ አሪቢያ እና በቻይና ክለቦችም ተዘዋውሬ ሰርቼአለሁ፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     በተጨዋችነት ህይወትዎ ለሆላንድ ብሔራዊ ቡድን ተሰልፈው ነበር

ማርቲን፡-      አዎ የማንኛውም ተጨዋች ህልም ሀገሩን ወክሎ መጫወት ነው፡፡ እኔም በሆላንድ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ተመርጬ ሀገሬን ማገልገል ችያለሁኝ፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     የትዳር ሁኔታዎ እንዴት ነው፡፡

ማርቲን፡-      አግብቻለሁኝ ባለቤቴ አስተማሪ ናት፡፡ አሩባ ውስጥ ትኖራለች፡ ከእሷ ጋር አብረን በመኖራችን ኩራት ይሰማኛል፡፡ የተባሉ ሁለት ልጆች አሉኝ አንደኛው አሩባ ውስጥ በስራ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ በዩኒቨርስቲ ውስጥ ስፖርት አስተማሪነትን በማጥናት ላይ ይገኛል፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     ምን አይነት የጨዋታ ዘይቤ ይመችዎታል

ማርቲን፡-      በቁጥር ግለፀው ካልከኝ በ4-3-3 አሰላለፍ ገብቶ ተጋጣሚን የሚያስጨንቅ እና የሚያጠቃ ቡድን ያስደስተኛል፣ ከጨዋት በፊት ሁልጊዜም ተጋጣሚዎቼን ማጥናት እፈልጋለሁ፡፡ ካየሁ በኋላ የቱ ጋር ነው እነሱን ማጥቃት እና ማሸነፍ የምችለው የሚለውን እፈልጋለሁ፡፡ በአጠቃላይ 4-3-3 እመርጣለሁ ግን የተጋጣሚውን የጨዋታ ዘይቤ ተመልክቼ ሌላም አሰላለፍ መጠቀም እችላለሁ

ል.ጊ.ዮ፡-     ኢትዮጵያን እንዴት አገኟት ሲመጡ ምን ጠብቀው ነበር

ማርቲን፡-      ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ይህ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ ከመምጣቴ በፊት ብዙ ሰዎችን ወደ ኢትዮጵያ ልሂድ ነው ስላቸው «በእግዚያብሔር ስም ኢትዮጵያ ልትሄድ ነው´ ብለው ይጠይቁኝ ነበር እዚህ ሀገር ስትመጣ የምታየው እና ውጪ የምትሰማው ነገር በጣም የተለየ ነው ሁሉም ቦታ ስትሄድ ግንባታዎች ተጀምረው ትመለከታለህ፡፡ ሁሉም ስው ስራ ላይ ነው፡፡ ኢኮኖሚውም እያደገ እንዳለ መመልከት ትችላለህ፡፡ ወደ እግር ኳሱም ከመጣህ ስታዲየም በተገኘሁባቸው ጥቂት ጨዋታዎች ህዝቡ እግር ኳስ ወዳድ እንደሆነ ተመልክቻለሁ፡፡ ለታዳጊዎች ትኩረት መስጠታችሁ ደግሞ በቀጣይ አመታት በእግር ኳሰ የት ለመድረስ እንዳሰባችሁ አመላካች ነው፡፡ ክለባችን የዚህ ሂደት ባለቤት በመሆኑ ደስተኛ ነኝ፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     ኩፕማን ማለት ምን ማለት ነው

ማርቲን፡-      ኩፕማን ማለት በገበያ ውስጥ ነገሮችን የሚሰጥ ነጋዴ ማለት ነው

ል.ጊ.ዮ፡-     ቅዱስ ጊዮርጊስን በምን ሁኔታ ተዋወቁት

ማርቲን፡-      ለጥቂት ጊዜያት ኑሮዬን አሩባ አድርጌ ነበር፡፡ ሬኒ ደግሞ አዲስ ለሚከፈተው የይድነቃቸው ተሰማ ስፖርት አካዳሚ ዳይሬክተር ሆኖ ተሾመ፡፡ ወዲያው እኔ ጋር መጥቶ ቅዱስ ጊዮርጊስን ታውቀዋለህ ወይ አለኝ፡፡ እኔም ኢትዮጵያን አልኩት የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገ/መስቀል ሲቭህን አይተውት በጣም ወደውሃል እና ለምን አትሰራም ብሎ ጥያቄውን አቀረበልኝ፡፡ ወደያውኑ ኢንተርኔት ላይ የክለቡን ዌብሳይት፣ ስለክለቡ የተፃፉ ነገሮችን አነበብኩና ትልቅ ክለብ መሆኑን ስለተገነዘብኩ ጥያቄዎችን ተቀብዬ ማሰልጠን ተዘጋጅቼአለሁ፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     የኢትዮጵያን እግር ኳስ ደረጃ እዚህ ጋር ነው ብለው መናገር ይችላሉ

ማርቲን፡-      ሁለት የሊግ ጨዋታዎችን ብቻ ነው የተመለከትኩት እና ደረጃውን ይሄነው ልልህ አልችልም፡፡ ነገር ግን ኦማን ነበርኩ የኦማን እግር ኳስ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ በጥቂቱም ቢሆን የተሻለ ይመስለኛል፡፡ በተለይም በመሰረተ ልማት ረገድ የኢትዮጵያ ሜዳዎች ሁሉም ጥሩ ናቸው ማለት አንችልም፡፡ ጥሩ ሜዳ ከሌለህ ደግሞ ችሎታ አላቸው የምትላቸውን ተጨዋቾች ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ለወደፊት መታሰብ ያለበት ጥሩ እግር ኳስ መመልከት የሚቻለው ጥሩ የመጫወቻ ሜዳ ሲኖር ስለሆነ ሜዳዎችን ማስተካከል እና መገንባት ላይ ብታተኩሩ መልካም ይመስለኛል፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ምን ለመስራት አሰበዋል

ማርቲን፡-      ሻምፒዮን እንዲሆንና የክለቡን ባህል ማስቀጠል አላማዬ ነው፡፡ በተለይም ሁሉም ቡድን ቅዱስ ጊዮርጊስን ለማሸነፍ ስለሚመጣ በጠንካራ ሁኔታ መስራት እንዳለብኝ አውቃለሁ፡፡ በትልቁ ግን የክለቡ የረጅም ጊዜ እቅድ የሆነውና በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ስምንት ውስጥ መግባት ህልም ለማሳካት ከወዲሁ ስራዬን ጀምሬያለሁ፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     ለየትኛው ቅድሚያ ይሰጣሉ ለፕሪሚየር ሊጉ ወይስ ለሻምፒዮንስ ሊጉ

ማርቲን፡-      ሁለቱንም በእኩል ደረጃ ነው የማያቸው፣ በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉም ጨዋታ አዲስ ነው፡፡ ነገ እሁድ የሊግ ጨዋታ እንዲሁም የሚቀጥለው እሁድ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ካለብኝ ትኩረቴን የማደርገው በሊጉ ጨዋታ ላይ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም ለሻምፒዮንስ ሊጉ ጨዋታ መዘጋጀ ስድስት ቀን ስላለኝ ሁሉም ለእኔ አስፈላጊ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     ከቦርድ አመራር አባላት ጋር የመገናኘት እድል ገጥሞዎት ነበር

ማርቲን፡-      ከቅዱስ ጊዮርጊስ የስራ አመራር ቦርድ ጋር በአጠቃላይ ወደ አራት የሚደርሱ ስብሰባዎችን አድርጌያለሁኝ፡፡ የሚፈልጉትን የሚያውቁ Realistic የሆኑ አመራሮች አሏችሁ፡፡ ለቅድመ ውድድር ዝግድት የሚሆነኝን ስብሰባ እና እቅድ ለቦርዱ አቅርቤ ተስማምተውበት በቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ዝግጅቱን በጥሩ መልኩ የሚጀምር ይሆናል፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-    ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ቡደን አሰልጣኞች ጋር ያለዎት ግንኙነት እንዴት ነው ይሆናል

ማርቲን፡-      እንደአጋጣሚ ሆኖ የ17 ዓመት ቡድኑ ሁለት ዋንጫዎችን ሲያነሳ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝቼ ተከታትዬዋለሁኝ፡፡ ለእኔ ከሁለቱ የታዳጊ ቡድኖች ጋር አብሬ መስራት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ እኛ ሆላዳዉያን አሰልጣኞች ወጣት ተጨዋቾችን ማሳደጉ እና ለዋናው ቡድን ማብቃት ባህላችን ነው፡፡ ያንን ባህል እዚህ ማምጣት እፈልጋለሁ፡፡ አካዳሚ፣ ከ17 አመት በታች እና ከ20 አመት በታች ቡድኖች ውስጥ ጥሩ ተጫዋቾች ካየሁ እና ወደ ዋናው ቡድን ሲመጡ ደጋፊው እንዲታገሱም በቅድሚያ እጠይቃለሁኝ፡፡ ለምሳሌ ከ17 አመት በታች ቡድኑ ውስጥ አራት ምርጥ ታዳጊዎችን መመልከት ችያለሁኝ፡፡ እነዚህ ታዳጊዎች ከተሰራባቸው በሁለት አመት ውስጥ የዋናውን ቡድን በብቃት ማገልገል ይችላሉ አሰልጣኙ የሚፈቅድ ከሆነም በቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ከዋናው ቡደን ጋር የሚጓዙ ይሆናል፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     ማርቲን ምን አይነት አሰልጣኝ ነው

ማርቲን፡-      ራሴን ግለጽ ካልከኝ ለስነስርዓት ቅድሚያ የምሰጥ አሰልጣኝ ነኝ፡፡ ከሁሉም የክለባችን አባላት ጋር ጥሩ ግንኙነት በመፍጠር ቤተሰባዊ ግንኙነት እንዲኖረኝ እጥራለሁ፡፡ የግለሰቦች የጋራ ጥረት ጥሩ የእግር ኳስ ቡድንን እንደሚፈጥር አምናለሁኝ፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     አዲስ ቡድን፣ አዲስ ባህል፣ አዲስ ተጨዋቾችን፣ የቋንቋውን ችግር እንዴት ሊያስተካክሉት አስበዋል፡፡

ማርቲን፡-      ብዙ ሀገሮች ዞሬያለሁ፡፡ ከሀገሬ ስወጣ የመጀመሪያ አይደለም ቻይና ነበርኩኝ ነገር ግን አስተርጓሚ ነበረኝ፣ ኦማን፣ ጋና፣ ኮንጐ አና ሳውድአረቢያ ነበርኩኝ ቋንቋ ግን የእኔ ችግር አልነበረም፡፡ ነገር ግን በቀላሉ ሊረዱኝ የማይችሉ ተጨዋቾች ካሉ በማስተርጐም እና በመርዳቱ በኩል ዘሪሁን ስላለ ችግር አይፈጥርብኝም ከሁለም በላይ የእግር ኳስ ቋንቋ ያን ያህል አስቸጋሪ አይደለም፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችን እንዴት ተመለከቷቸው

ማርቲን፡-      ድንቅ ናቸው የመጀመሪያ ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝቼና በስልኬ ቀድቼ በማህበራዋ ድረ ገፅ ላይ ለቅቄው ሁሉም ሰው ወዶት ነበር ቡድናቸውን ሲያበረታቱ ስመለከታቸው ከውስጤ የሚነዝር ነገር ተሰምቶኛል በጣም የሚገርሙ ነበሩ

ል.ጊ.ዮ፡-     ምን አይነት ቡድን እንጠብቅ

ማርቲን፡-      እንደ ቤተሰብ የሚዋደድ ቡድን መስራት እፈልጋለሁ፣ አንዱ ተቀያሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ሌላው እየተጫወተ ሲያገባ የማይደሰት ከሆነ ይሄ ቡድን አይደለም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ታጋይ የሆነ የሚያጠቃ እና ሣቢ የሆነ ጨዋታን የሚጫወት ቡድን መስራት እፈልጋለሁኝ፡፡

ል.ጊ.ዮ፡-     በሻምፒዮንስ ሊግ ስኬታማ ለመሆን ምን መስራት አለብን

ማርቲን፡-      ጥሩ ዝግጅት ከማድረግ በተጨማሪ ተቃራኒ ቡድንን በደንብ ማጥናት እና ደካማ ጐኑ ምን እንደሆነ ማወቅ ይገባሃል፡፡ በጥሩ ሁኔታ ከተዘጋጀህና የተጋጣሚህን ደካማ ጐን ካወቅክ ስህተቶችን ካልሰራህ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ትችላለህ

ል.ጊ.ዮ፡-     በመጨረሻ ለደጋፊዎች ማስተላለፍ የሚፈልጉት ነገር ካለ

ማርቲን፡-      በመጀመሪያ በጥቂት ወራት በፊት ሊቢያ ላይ በአይ ኤስ አይ ኤስ ለተባለው የሽቡር በተገደሉት ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ሞት ምክንያት የተሰማኝን ሀዘን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ሁኔታው በደረሰ ወቅት እዚህ አልነበርኩም ነገር ግን ዜናዎችን በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ሰምቼያለሁ እናም በጣም ማዘኔኔ ለቤተሰቦቸቸውም መጽናናትም ተመኝቻለሁ፡፡ በሁለተኛም ደረጃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ቡድናቸውን እንዴት ማበረታት እንዳለባቸው የሚያውቁ ናቸው ባለፈው ያየሁትን የሚያምር የስታድየም ድባብ በቀጣይ አመትም እንዲቀጥሉበት እጠይቃለሁ፡፡

«ቅዱስ ጊዮርጊስን ክለብን የማየው እንደ ቤቴ ነው» አለማየሁ ሙለታ

ሰለሞን መኮንን(ሉቾ) እና ሙሉአለም ረጋሳ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ውስጥ ከታዳጊ ቡድን ጀምሮ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ ከአስር አመታት በላይ በመጫወት ድንቅ እንቅስቃሴያቸውን ሲያሳዩን የነበሩ ተጨዋቾች ናቸው፡፡ እነዚህን ሁለት ተጨዋቾች ሁለት ነገር ያመሳስላቸዋል፡፡ ሁለቱም በተለያየ ዘመን ከታች ቡድን አድገው የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን አስራ አራት ቁጥር ማልያን በመልበስ እና ጫፍ በደረስ የመሀል ሜዳ ጨዋታ ብቃታቸውም ይታወቃሉ፡፡ በሁለተኛ ደረጃም ከታች ቡድን አድገው ዋናው ቡድንን በአምበልነት ሠርተዋል፡፡ በዚህ ዘመን ከታዳጊ ቡድናችን ተነስቶ ወደ ፊት ጥሩ ችሎታን ያሳየናል ብለን ተስፋ ያደረግንበት አለማየሁ ሙለታ ደግሞ የዚህ ዘመን የ14 ቁጥር ባለተራ ይመስላል፡፡

ይህ ታዳጊ ከላይ የጠቀስናቸውን የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ባለታሪኮች ላይ ለመድረስ በትዕግስት ጠንክሮ መስራት እንደሚጠበቅበት ቢያውቅም ህልሙ ግን የክለቡ ህያው ተጨዋች መሆን ነው፡፡ «ከልጅነቴ አንስቼ ለዚህ ክለብ በመጫወት አሁን ለዋናው ቡድን እስከ መጫወት ደርሻለሁ፡፡ እዚህ ለመድረስ ብዙ የሰራሁ ቢሆንም ትልቁ ፈተና የሚጠብቀኝ ግን እዚህ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ለዚያም ራሴን አዘጋጅቼያለሁኝ፡፡ ባለፉት አመታት ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያየሁት እና የሰማሁት በክለቡ ታሪካዊ የሆኑት ተጨዋቾች ያለ ስራ ባለታሪክ እንዳልሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም እኔም ጠንክሬ ሰርቼ ክለቤን በማገልገል በክለባችን ውስጥ የራሴን አሻራ ማስቀመጥ እፈልጋለሁኝ፡፡» ሲል ገልጿል፡፡

አለማየሁ ሙለታ የቅዱስ ጊዮርጊስን ታዳጊ ቡድን የተቀላቀለው በኤፍሬም (ቤቢ) መልማይነት በ2001 ዓ.ም ነበር፡፡ እስከ 2004 ዓም በታዳጊ እና በተስፋ ቡድን ሲጫወት ከቆየ በኋላም በ2004 ዓም የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኝ በነበሩት ዳንኤሎ ፔርሉጂ አማካይነት የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን ከአየር ሀይል አቻው ጋር ባደረገው የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ የመሰለፍ እድሉን አገኘ፡፡ ከዚያ አመት በኋላም በዛ ባሉ ጨዋታዎች ላይ ቡድናችንን በመወከል ለመጫወት ችሏል፡፡

አለማየሁ ባሳለፍነው ሰኔ30/ 2007 ዓ.ም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበረው ውል መጠናቀቅን ተከትሎ ባሳለፍነው ሳምንት ለመጪዎቹ ተጨማሪ ሁለት አመታት በክለቡ የሚያቆየውን ውል መፈረም ችሏል፡፡ ይህንን አስመልክቶ በሰጠው አስተያየትም «ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን የማየው እንደ ቤቴ ነው፡፡ የውጪ እድልን እስካላገኘሁ ድረስ ክለቤን ስለመልቀቅ አላስብም፡፡ ማንኛውም ተጨዋች የኮንትራት ማራዘሚያ ጥያቄ ሲቀርብለት የክለቡ የወደፊት እቅድ አካል መሆኑን እና በክለቡ እንዲቆይ መፈለጉን ይረዳል፡፡ እኔም የክለቡ ሃላፊዎች ሲደውሉልኝ እና ጥያቄውን ሲያቀርቡልኝ የተረዳሁት ይሄን ነው፡፡ በመቆየቴ ክለቤንም እኔንም መጥቀም እንደምችል አውቃለሁ፡፡ አሁንም ጠንክሬ ሰርቼ እምነት ጥለው ተጨማሪ እድል የሰጡኝን የክለባችን ደጋፊዎች እና ሃላፊዎችን ለማስደሰት ቃል እገባለሁ፡፡»

አለማየሁ ሙለታ ከወዲሁ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ውስጥ ብዙ አመት ከቆዩ ተጨዋቾች አንዱ ሆኗል፡፡ ተጨዋቹ በዋናው ቡድን ሶስት አመታትን ያሳልፍ እንጂ ከዚያ በፊት የነበሩትን ሶስት አመታት በታዳጊና ተስፋ ቡድን ውስጥ ቆይታውን ማድረጉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ውስጥ የቆየባቸውን አመታት ስድስት ያደርሰዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ጥቂቶች ብቻ የሚሳካላቸውን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለሶስት ጊዜያት ማለትም በ2004 በ2006 በ2007 ማንሳት ችሏል፡፡ ተጨዋቹ በእነዚህ አመታት ውስጥ ላሳለፋቸው መልካም ጊዜያቶች የሚያመሰግናቸው ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ «እኔ እዚህ እንድደርስ የረዳኝን ልዑል እግዚያብሄርን አመሰግናለሁ፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች እና አመራር አካላት ለእኔ እዚህ መድረስ አስተዋፅኦዋቸው የበዛ ነው፡፡ በመቀጠልም አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከተስፋ ቡድን ጀምሮ እንደ ታላቅ ወንድምም እንደ አሰልጣኝም በመሆን እዚህ እንድደርስ ትልቁን ሚና ተጫውቷል፡፡ ከሱ በተጨማሪም አቶ ኤፍሬም ግዛቸው፤ ዘሪሁን ሸንገታ፤ ሰላም ዘርዐይን በጣም ላመሰግን እወዳለሁ፡፡»

«እዚህ የደረስኩት ጊዮርጊስ ውስጥ ስለሆንኩ ነው» ናትናኤል ዘለቀ

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ለቀጣይ ሁለት አመታት ለመጫወት ውሉን ያራዘመው ናትናኤል ዘለቀ ውሉን በማራዘሙ እጅግ በጣም ደስተኛ መሆኑን እና እዚህ ደረጃ የደረስኩት ጊዮርጊስ ውስጥ ስለሆንኩ ነው ሲል ለልሳነ ጊዮርጊስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ተናግሯል፡፡

ናትናኤል ዘለቀ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ እና ተስፋ ቡድን ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን ከ2005 ዓ.ም ጀምሮም ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን በመቀላቀል ቡድናችንን ላለፉት አራት አመታት በዋናው ቡድን ተጨዋችነት አገልግሏል፡፡ ለናትናኤል ዘለቀ ለዋናው ቡድን እንዲጫወት እድሉን የሰጡት የቀድሞው የቡድናችን ጀርመናዊ አሰልጣኝ ማይክል ክሩገር ሲሆኑ የናትናኤል የመጀመሪያ ጨዋታም ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2005 ዓ.ም ከደደቢት ክለብ ጋር ያደረገው ጨዋታ ነበር፡፡

ናትናኤል በክለብ እና በብሄራዊ ቡድን ደረጃ እንደ ደጉ ደበበ ያሉት ተጨዋቾች የደረሱበት ደረጃ መድረስ እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ውስጥ መጫወት ህልሙ እንደሆነ ገልፆ አሁን ብሄራዊ ቡድንም የተያዘው በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ውስጥ በመጫወቱ መሆኑን አብራርቷል፡፡ «ቅዱስ ጊዮርጊስ ስትጫወት በጫና ውስጥ በማለፍህ እና በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ስለምትፈተን የሁሉም አሰልጣኝ አይን ቡድኑ ላይ ነው፡፡ ለዚህም ነው እኔ ከወጣት ቡድን ወደ ዋናው ቡድን እንዳደኩ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሊመለከተኝ የቻለው፡፡»

ወጣቱ አማካይ ናትናኤል ዘለቀ ለዚህ ስኬቱ ብዙዎችን ያመሰግናል፡፡ «በመጀመሪያ ደረጃ ለዚህ ያበቃኝን

አምላኬን አመሰግናለሁኝ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የክለቡ አመራሮች እና ደጋፊዎች ሁልጊዜም ከጎኔ

ነበሩ፡፡ የቡድን ጓደኞቼ እና በተለያየ ዘመን ያሰለጠኑኝ አሰልጣኞች ለእኔ እዚህ መድረስ ትልቁን ድርሻ

ይወስዳሉ እና ሁሉንም አመሰግናቸዋለሁ፡፡»

«ካለፉት አመታት በተሻለ አስተዋፅኦ ለማድረግ እጥራለሁ»ምንያህል ተሾመ

ምንያህል ተሾመ ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለው በሀምሌ ወር 2005 ዓ.ም ነው፡፡ባሳለፍነው ሰኔ ወርም ኮንትራቱ ተጠናቅቆ የነበረ ቢሆንም ከአሰልጣኞች እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሀላፊዎች ጋር ውይይት ካደረገ በኋላ በቡድናችን ውስጥ ለቀጣይ ሁለት አመታት የሚያቆየውን ውል መፈረም ችሏል፡፡

ምንያህል ተሾመ በግራ እና በመሀል ሜዳ ከአጥቂ ጀርባ ባለው ቦታ ላይ መጫወት የሚችል ሲሆን በተለይምበጨዋታ እንቅስቃሴ በተጋጣሚ ሜዳ ላይ የግል ችሎታውን ተጠቅሞ ግቦችን በማስቆጠር እና ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል አድናቆትን ያተረፈ ተጨዋች ነው፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር አመትም ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉ ሻምፒዮን ሲሆን ጥሩ እንቅስቃሴን ካሳዩ ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ምንያህል በክለቡ ውስጥ ያለውን ቆይታ በማራዘሙ የተሰማውን ደስታ ትልቅ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ ባለፉት አመታት ካሳየው አቋምም የተሻለ ነገር ለማሳየት ጠንክሮ እንደሚሰራና የመጀመሪያ አላማው የነበረውም ቅዱስ ጊዮርጊስ ውስጥ ቆይቶ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን የክለቡን እቅዶች ማሳካት እንደነበር ገልጿል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ31 አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ስትመለስ ድንቅ ችሎታውን በማሳየት ለብሄራዊ ቡድኑ ስኬት ቁልፍ አስተዋፅኦን ያደረገው ምንያህል በቀጣይ አመት በሆላንዳዊው አሰልጣኝ እየተመሩ ጥሩ ስኬት ላይ መድረስ እንደሚቻል ያምናል፡፡ «ቅዱስ ጊዮርጊስ ታላቅ ክለብ ነው፡፡ ከሀገራዊው ሻምፒዮንነት በተጨማሪ የአህጉራዊው ድልም ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህም ሁሉም የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ቤተሰብ ለዚህ ስኬት ጠንክሮ መስራት ይኖርበታል፡፡ በጥቂት አመታት ውስጥም ያሰብነው ደረጃ ላይ እንደምንደርስ አልጠራጠርም ሲል ለልሳነ ጊዮርጊስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ተናግሯል፡፡