Newsletter Signup

Sign-up to stay in touch with Saint George FC

Reagent/Protectorator
Yidnekatchew Tessema
Mengistu Worku

St. George Gallery

News

የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች ልምምድ ጀመሩየቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች ልምምድ ጀመሩ

የ2008 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ጥቅምት አስራ ሰባት ቀን ተጀምሯል፡፡ በዘንድሮው ውድድር ላይ አስራ አራት ተካፋይ ክለቦች ይገኙበታል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ስድስት የአዲስ አበባ እና ከተለያዩ ክልሎች ስምንት ተሳታፊ እየሆኑበት ይገኛሉ፡፡ የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በአንደኛው ሳምንት በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተማ ሜዳዎች በተስተናገዱበት ሰባት ጨዋታዎች ስድስቱ ጨዋታ በመሸናነፍ ሲጠናቀቅ አንድ ጨዋታ ብቻ አቻ ውጤት ተመዝግቦበታል፡፡ በነዚህ ሰባት ጨዋታዎች አስራ አንድ ግቦች ተቆጥረዋል፡፡ ሌላው በሁለተኛ ሳምንት በተካሄድው የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር አምስት ጨዋታ በመሸናነፍ ሲጠናቀቅ ሁለት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተለያይተውበታል፡፡

በሁለተኛው ሳምንት አስራ ሦስት ግቦች ተቆጥረዋል፡፡ እስካሁን በተካሄዱት የሁለት ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ ውድድሮች በአጠቃላይ ሃያ አራት ግቦች የተስተናገዱበት ሆኗል፡፡ በሜዳቸው ላይ ሁለቱንም ጨዋታዎች በመጫወት ያሳለፉት ክለቦች ከአዲስ አበባ ኢትዮ ቡና፣ ኢትዮ ንግድ ባንክ፣ መከላከያ ደደቢት ሲሆኑ አንድን ጨዋታ በሜዳቸው አንድ ጨዋታ ከሜዳቸው ውጭ ወደ ክልል ተጉዘው የተጫወቱት ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኤሌትሪክ ክለቦች ናቸው፡፡ ከክልል ተሳታፊ ስምንት ክለቦች ሁለቱንም ጨዋታ ከሜዳው ውጭ የተጫወተ የሲዳማ ቡና ክለብ ሲሆን ሁለቱንምጨዋታ በሜዳው ላይ ለመጫወት የበቃው የአዳማ ከተማ ቡድን ነው፡፡

የአዳማ ከተማ ቡድን በሜዳው ላይ ያደረጋቸውን ሁለቱንም ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሁለት ለዜሮ በማሸነፍ ስድስት ነጥብ ለማስመዝገብ በቅቷል፡፡ ሌላው የዳሽን ቢራ ቡድንም አንድ ጨዋታ በሜዳው እንዲሁም አንድ ጨዋታ ከሜዳው ውጭ በመጫወት ሁለቱንም ጨዋታ በማሸነፍ በተመሳሳይ ስድስት ነጥብ ያስመዘገበ ቡድን ሆኗል፡፡ ከአስራ አራቱ ተካፋይ ክለቦች በሁለቱም ጨዋታ ተሸንፎ ነጥብ መያዝ ያልቻለው የሀዲያ ሆሳዕና ቡድን ብቻ ሲሆን ሌሎቹ ሁሉም ክለቦች ነጥብ ለማስመዝገብ በቅተዋል፡፡ የዘንድሮው የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ጅማሬውን ያገኘው በጥሩ ወቅት ላይ ቢሆንም ሁለተኛው ሳምንት ጨዋታ በኋላ ከተጠናቀቀ ለአንድ ወር ከአስር ቀን እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ሀገራችን ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ዋንጫን አዘጋጅ በመሆኗ ነው፡፡ ይህም የሴካፋ ውድድር ህዳር አስራ ሁለት ቀን ተጀምሮ ለሁለት ሳምንት ያህል ይካሄዳል፡፡፡ ከምስራቅ አፍሪካው ዋንጫ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአለም ዋንጫ የማጣሪያ ማጣሪያ ጨዋታ እና ለአፍሪካ ቻን ውድድር የሚያደርጋቸው ኢንተርናሽል ጨዋታዎች ይኖሩታል፡፡ ከዚህ ሌላም ሀገራችንን በመወከል ቅዱስ ጊዮርጊስ በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና መከላከያ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚያደርጓቸው ኢንተርናሽል ውድድሮች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህ ሁሉ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች የዘንድሮውን የፕሪሚየር ሊጉን ውድድር የሚጠናቀቅበት ጊዜያት አስቸጋሪ የሚያደርገው ይሆናል፡፡ በዘንድሮው የፕሪሚየር ሊግ ውድድር እስካሁን የተካሄዱት የሁለት ሳምንት ጨዋታዎች ሲሆኑ በቀጣይነት የሚጀመረው የሦስተኛ ሳምንት ውድድር ታህሳስ ሁለት ቀን እንደሆነ የወጣው ፕሮግራም ያሳያል፡፡ በተለይ አሁን የተቋረጠበት የውድደር ወቅት ሲታይ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ አጓጊ በሆነበት የእግር ኳስ አፍቃሪያንን ስሜት ባነቃቃበት ወቅት ላይ እንደሆነም ማየት ተችሏል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ባደረጋቸው ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በአንደኛው ሳምንት ወደ አዳማ ተጉዞ ከአዳማ ከነማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ሁለት ለዜሮ ሲሸነፍ በሁለተኛው ሳምንት ከሲዳማ ቡና በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረገው ጨዋታ አምስት ለአንድ አሸንፏል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከነማ ተጫውቶ በተሸነፈበት ጨዋታም የቡድናችን የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ጥሩ እንደነበር እና ተስፋ ሰጭ ሆኖ የታየበት ነበር፡፡ ከሲዳማ ቡና ባደረገው ጨዋታም አምስት ለአንድ በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሽንፍ በሰፊ የግብ ልዩነት እንዲሁም በሜዳ ላይ በታየ ምርጥ የጨዋታ ብቃት ሲሆን የተቆጠሩትም ግቦች ማራኪ ጭምር ነበሩ፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን አምስት ለአንድ ሲያሸንፍ የመጀመሪያዋን ምንያህል፣ ሁለተኛውን ብራይን፣ ሦስተኛውን አዳነ፣ አራተኛውን ራምኬሎ፣ አምስተኛዋን አዳነ ማስቆጠር ችለዋል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር ለአርባ ቀን ያህል የተቋረጠ በመሆኑ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች የተወሰነ ቀናት እረፍት እንዲሰጣቸው ተደርጐ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ መደበኛ ልምምዳቸውን ጀምረዋል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የምስረታ በአሉን ከጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ጋር ያከብራል፡፡የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የምስረታ በአሉን ከጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ጋር ያከብራል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በ1928 .ም የተመሠረተ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ክለብ ነው፡፡ክለቡ በፋሺስት ጣሊያን የወረራ ዘመን የተቋቋመና ነፃነት ሲመለስ እሱም ነፃ የወጣ በመሆኑ ከኢትዮያውያን ትግል፣ መስዋዕትነት፣ አንድነትና ፍቅር ፅኑ ትስስር አለው፡፡

ሀገር በቅኝ ግዛት አስተሳሰብ በግራ ቀኝ ተወጥራ በምትተራመስበት በዛ አጣብቂኝ ጊዜ በየ ዱር ገደሉ የሀገር አንድነትንና ሉአላዊነትን ለማስጠበቅ የህይወት መስዋእትነትን ለሚከፍሉ አርበኞች ከከተማው ህዝብ ጋር መገናኛ ድልድይ ሆኖ መረጃ የሚለዋወጡበት ምክንያት ሆኖ ሀገራን ከቅኝ ገዢዎቿ ፍላጎት ነፃ እንድትወጣ ታሪክ የማይዘነጋው ትውልድ የሚደነቅበት፣ ከሀገር እድገትና ለውጥ ጋር ተያይዞ ምንጊዜም የሚነሳ ገድል ባለቤት እንደሆነ ከትውልድ ትውልድ ታሪካዊ አደራን እየተወራረሰ ለዚህ ዘመን መብቃቱ ለሀገራችን አንዱ የታሪክ ቅርስ   መሆኑን ያሳያል፡፡

በተለይም ሀገራችን ኢትዮጵያ በፋሺስት ኢጣልያ የወረራ ዘመን አርበኞች መረጃ እንዲለዋወጡ፤የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ክለብ በመሆን የነጭ ክለብን ለመጀመሪያ ጊዜ በማሸነፍ ለመላው ኢትዮጵያውያን ነጭ መሸነፍ እንደሚችል ያሳየ አርበኛ እግር ኳስ ክለብ ነው፡፡

ይህንን ጥንታዊ ታሪክ ለመዘከርና ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር 80ኛ አመት የምስረታ በአሉን በመጪው ታህሳስ ወር ሲያከብር ታህሳስ 21 ቀን 2008 ዓ.ም ከጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አባላት ጋር በመሆን የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን የአርበኝነት ታሪክ የሚያሳዩ ዝግቶችን በታሪካዊው ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ለማክበር ዝግጅቱ ተጠናቅቋል፡፡ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበርም ይህንን ታሪካዊ ክብረ በዓል ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ጋር በጋራ ለማክበር በመብቃቱ መደሰቱን ገልፆ ከዚህ በታች የተቀመጠውን የተሳትፎ ማረጋገጫ ደብዳቤ ልኮልናል፡፡

የግብፁ አል አህሊ እና የሱዳኑ ኤል ሜሪክ ክለቦች በቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማንያኛ አመት የምስረታ ክብረ በዓል ላይ እንደሚሳተፉ አረጋገጡ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሰማንያኛ አመት የምስረታ ክብረ በዓልን በመጪው ታህሳስ ወር እጅግ በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የግብፁ አል አህሊ እና የሱዳኑ አል ሜሪክ ክለቦች ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ አዲስ አበባ እንደሚመጡ በፃፉት ምላሽ አስታውቀዋል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ላለፉት ስምንት ወራት ለሁለቱ አንጋፋ ክለቦች አመራሮች ጋር በደብዳቤ እና በስልክ ግንኙነት ያደረገ ሲሆን ክለባችን የላከውን የግብዣ ደብዳቤን ተከትሎም ሁለቱ ክለቦች በምስረታ ክበረ በዓሉ ላይ እንደሚገኙ በላኩት ምላሽ አሳውቀዋል፡፡

የግብፁ አል አህሊ በፃፈው ደብዳቤም ምንም እንኳን በታህሳስ ወር አምስት ከባድ ጨዋታዎች ቢኖሩትም በዚህ ታላቅ እና ታሪካዊ በአል ላይ ለመገኘት መወሰኑን ሲገልፅ የሱዳኑ አል ሜሪክ ክለብ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በፃፈው ደብዳቤ የሁለቱ ክለቦች ትስስር ከሀምሳ አመት በላይ ያስቆጠረ መሆኑንና ለዚኅ ታላቅ በአል በመጋበዙ ትልቅ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል፡፡

የሰማንያኛ አመት ክብረ በዓል ውድድር አዘጋጅ ኮሚቴም ክለቦቹ የመመጡባቸውን ቀናት በመታወቁ የውድድር መርሀ ግብር አዘጋጅቶ ለክብረ በዓሉ አዘጋጅ አቢይ ኮሚቴ አቅርቦ ያስፀደቀ ሲሆን በመጪዎቹ ቀናትም የወዳጅነት ጨዋታውን መርሀ ግብር ለህዝብ የሚያሳውቅ መሆኑ ታውቋል፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ተሸላሚዎችን መርጦ ለመሸለም አባላትን የሚያሳትፍ መጠይቅ ተዘጋጀበቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ተሸላሚዎችን መርጦ ለመሸለም አባላትን የሚያሳትፍ መጠይቅ ተዘጋጀ

በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ተሸላሚዎችን መርጦ ለመሸለም አባላትን የሚያሳትፍ መጠይቅ መዘጋጀቱን የሽልማት ኮሚቴ ፀሐፊ አቶ ተስፋዬ ነጋሽ አሳታወቁ፡፡

አቶ ተስፋዬ ነጋሽ ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም በስፖርት ማህበሩ የሬዲዩ ፕሮግራም ላይ በመገኘት ስለመጠይቁ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት መጠይቁ የተዘጋጀው በሽልማት ኮሚቴ መሆኑን ከገለጹ በኋላ ለሽልማት የሚቀርቡትን ተሸላሚዎች ለመጠቆም መላው ደጋፊ ቢሳተፍ በየአካባቢው ለክለቡ ከፍተኛ አስተዋጾ ለማበርከት የቻሉትን ለማግኘት ይቻላል ተብሎ ስለታመነበት ነው ብለዋል፡፡

ኮሚቴው ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ልዩ ልዩ ተግባራትን እንደፈጸመ የገለጹ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በመጀመያ መርሃ ግብር መነደፉን ገልጸው በመርሃ ግብሩ መሠረት መሸለም ያለባቸው የተሸላሚዎችን ዝርዝር ሁኔታ መለየት አሰፈላጊ መሆኑን ከተወያየንበት በኋላ ተሸላሚዎቹ

      መስራች ተጨዋቾች

      አመራር ሰጪዎች

      ደጋፊዎች

      አሠልጣኞች

      ተጨዋቾች

      ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች እንደሆኑ መወሰኑን ገልፀዋል፡፡

የተገለጹትን ተሸላሚዎች ለመምረጥ መመዘኛ መስፈርት መዘጋጀቱን ገልጸው መመዘኛዎቹ በአብይ ኮሚቴው ታይተው እንዲፀድቁ በመግለጽ በመጠይቅ መልክ ተዘጋጅተው ደጋፊዎች መጠይቁን በመሙላት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ ደጋፊዎች መጠይቁን ከጽ/ቤት በመውሰድ ከሞሉ በኋላ የሞሉትን ቅጽ በመመለስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እንዲያስገቡ አሳስበዋል፡፡ በመቀጠልም ኮሚቴው አባላቱ የሰጡትን ጥቆማ በማጣራት የተሸላሚዎችን ብዛትና ደረጃ እንደሚወስን ገልጸዋል፡፡ መጠይቆቹ ክብደት አይኖራቸውም ወይ የአሁን ወጣቶችስ እንዴት ሊሞሉ ይችላሉ ተብሎ ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ ወጣቱ ታሪክ ማወቅን ይፈልጋል ቴክኖሎጂ በደረሰበት ደረጃ ለተተኪው ትውልድ ታሪከን ማቆየት ከዚህ ትውልድ ይጠብቃል፡፡

ይህን መጠይቅ ይዘው ጥናት ካደረጉ ሪሰርች ካደረጉ ስለጊዮርጊስ ክለብ ታሪክ ለማወቅ ስለሚችሉና መረጃዎቹ በመጽሐፍ በመድሔትና በመሳሰሉት ታትመው ለትውልዱና ለመጪው ትውልድ ስለሚጠቅሙ ለደጋፊው ትልቅ የቤት ሥራ ሰጥተናል ብለዋል፡፡ በመቀጠልም እኛ ታሪካዊ ሰዎችን ማግኘት እንፈልጋለን ቡድኑ ሲመሠረት የነበሩ ደጋፊዎች ካሉ ዛሬ በሕይወት ኖሩም አልኖሩም የጊዮርጊስ ብራንድ ናቸውና መሸለም ይገባቸዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለክለቡ የለፉ ያልታውቁ በሕመም በእርጅና በመሳሰሉት ቤት ውለው በየአካባቢው ያሉ ይኖራሉ እነኚህን ደጋፊው በጥቆማ ሊያገኛቸው ይችላል፡፡ ከዚህም ሌላ ከፍተኛ ግልጋሎት ያበረከቱ በሕይወት ባይኖሩም የቤተሰባቸው ተወካይ ተገኝቶ ሸልማቱን መቀበል ይችላል ብለዋል፡፡

በአንዳንድ ቦታ ላይ መጠይቁ የተሸላሚዎትንቁጥር ይገድባል ይህ ለምን ሆነ ተብለው ተጠይቀው ሲጠየቁ የሰጡት መልስ ገደብ ካላደረግን ተሸላሚዎች ይበዛሉ፣ ሁሉንም መሸለም አይቻልም፡፡ ስለዚህ ቆም ብሎ በማሰብ ማን ከማን ይልቅ የበለጠ ግልጋሎት ለክለቡ ሰጥቷል እያለ በቅደም ተከተል ለመምረጥ ስለሚያስችል የተሸላሚው ቁጥር ውስን መሆን ይኖርበታል ብለዋል፡፡ ይህ የሽልማት ሂደት የመጀመሪያ ቢሆንም ለወደፊቱ ከአሁኑ ተሞክሮ በመነሳት በየወቅቱ ባለውለተኞችን የመሸለም ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ይታመንበታል፡፡

                      የመጠይቅ ፎርሙን ከዚህ ማግኘት ይችላሉ                            

ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ለታዳጊዎች ማሰልጠኛ አካዳሚ የተጨዋቾች ምርጫ እየተካሄደ ነው

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በቢሾፍቱ ከተማ የታዳጊዎች የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ በመገንባት በመሆኑ በመጪው ታህሳስ ወር በታላቅ ድምቀት በሚከበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሰማንያኛ አመት ክብረ በዓል ላይ ለምርቃት ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለወደፊቱ የሀገራችንን እግር ኳስ ለማሳደግ ግንባር ቀደም ተዋናይ እንደሚሆን የታመነበት ይህ ማሰልጠኛ ተሸላሚ በርካታ ተተኪ ተጨዋቾችን ለሀገራችን የምናፈራበት ስለሆነ ለስልጠናው የሚረዱ ልዩ ልዩ የስልጠና መሣሪያዎችንና ዕቃዎችን ለማሟላት አስፈላጊው ጥረት ሁሉ እየተደረገ ነው፡፡ በችሎታቸው ብቁ ሆነው አካዳሚውን የሚቀላቀሉት እድሜአቸው ከአስራ ሦስት አመት በታች የሆኑ ታዳጊ ተጫዋቾች ይሆናሉ፡፡ የማሰልጠኛ አካዳሚው ቴክኒካል ዳይሬክተር በመሆን ለተሾሙት ሆላንዳዊ ሚስተር ሬኒ ሄድንከን ከወዲሁ ስራቸውን ለመጀመር እንዲያስችላቸው ሁኔታዎች እንዲመቻቹላቸው ተደርጓል፡፡ በቅድሚያም በየአመቱ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አዘጋጅነት በሚካሄደው የክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የመታሰቢያ ውድድር ላይ በ2007 ዓ.ም ክረምት ላይ እድሜቸው ከአስራ ሦስት አመት በታች ለሆኑ የታዳጊ ቡድኖች ውድድር እንዲካሄድ ተደርጓል፡፡ በዚህ ውድድር ላይ ከአዲስ አበባ እና ከተለያዩ ክልሎች በርካታ የታዳጊ ቡድኖች ተወዳድረውበታል፡፡ ባለፈው ክረምት ወራት በአበበ ቢቂላ ስታድየም እና ቃሊቲ በሚገኘው የመድን ድርጅት የእግር ኳሰ ሜዳ ላይ በተካሄደው ውድድር የታዳጊዎች ማሰልጠኛ ቴክኒካል ዳይሬክተር ሚስተር ሬኒ ሄድንከ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን አሰልጣኝ ሆላንዲዊው ማርቲን ኩፕማን የታሳታፊ ታዳጊ ቡድኖችን ጨዋታ በመከታተል አሳልፈዋል፡፡ በወድድሩ ላይ ብቁ የኳስ ክህሎት ያላቸውን ታዳጊዎች ሲመርጡም አብረዋቸው የተስፋ ቡድን አሰልጣኝ አሳምነው ገ/ወልድ፣ የታዳጊ ቡድናችን አሰልጣኘ በላቸው ኪዳኔ እንዲሁም የሴቶች ቡድናችን አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ አብረዋቸው በመሆን የተጫዋቾች ምርጫ እንዲያካሂዱ ተደርገዋል፡፡ በዚሁ ውድድር ላይ በኳስ ችሎታቸው ብቁ መሆናቸውን ከታመነባቸው መካከል ከአዲስ አበባ እና ከክልል ተሳታፊ ክለቦች ሃምሳ ያህል ታዳጊ ተጨዋቾችም በቅድሚያ እንዲመረጡ ተደርጓል፡፡

ከአዲስ አበባ ከአርሲ የታዳጊ ቡድኖች የተመረጡ ተጨዋቾች ባለፈው ቅዳሜ በመድን ድርጅት እግር ኳስ ሜዳ ላይ ተገኝተው የእርስ በእርስ ግጥሚያ ካደረጉ በኋላ ለመጨረሻ ጊዜ የተጨዋቾች ምርጫው እንዲካሄድ ተደርጓል፡፡ ሃያ አምስት ተጨዋቾች መያዛቸው ታውቋል፡፡ በዚሀ የተጨዋቾች ምርጫ ላይ ሆላንዳዊው ሚስተር ሬይን ሂድንክ እንዲሁም የተስፋ ቡድን አሰልጣኝ አሳምነው ገ/ወልድ፣ የታዳጊ ቡድናችን አሰልጣኘ በላቸው ኪዳኔና የሴቶች ቡድናችን አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ በምርጫው ላይ ተገኝተዋል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ኤሚ በቦታው ላይ በመገኘት በረኞችንም እንዲመርጥ ተደርጓል፡፡

ርዕሰ አንቀፅ የእግር ኳስ ባህላችን ወዴት እያመራ ነው

ዘመናዊ ስፖርት ወደ ሀገራችን ከገባና የእግር ኳስ እንቅስቃሴአችን ከተጀመረ ረጅም አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ህዝባችን የእግር ኳስ ፍላጐቱ በመጨመሩ ትኩረቱን ወደ እዚሁ ስፖርት ላይ አድርጓል፡፡ ወርቃማ የሆነውን የእረፍት ጊዜውንም የሚያሳልፍበት የሚዝናናበት ስፖርቱን በመከታተል ሆኗል፡፡ በጨዋታ ሜዳ በመገኘት የሚውደውን ክለብ ለመደገፍ ሲልም በውድድር ስፍራ በመገኘት ያሳልፋል፡፡ ቀደም ሲል በነበሩት የእግር ኳስ አፍቃሪያን የክለብ ደጋፊዎች ግንኙነት ጠንካራ ነበር፡፡ በጨዋታ ሜዳ ከሚደገፋቸው ክለቦች ጋር በስፖርታዊ ጨዋነት የድጋፍ አሰጣጣቸው ላይ ሰላማዊ ነበር፡፡ ለዚህም የአንድ ክለብ ደጋፊዎች ከሌላ ክለብ ደጋፊዎች ጋር ቀጠሮ በመያዝ በመፈቃቀርና በመግባባት ያሳለፉ እነደነበር እና ይሄም የአብሮነት መገለጫም ለበርካታ አመታት ዘልቆ ይወደስ ነበር፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን እንዲህ አይነት የድጋፍ አሰጣጥ መልኩን ቀይሮ የመጣበት በመሆኑ በተግባር እየታየ መጥቷል፡፡ የተሳዳቢ ተመልካቾች ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል፡፡ ለህሊናና ለጆሮ የሚዘገንኑ ስድቦች የሚስተናገዱበት አስፀያፊ ተግባሮች የሚከናወኑበት መደማመጥ እና መከበባበር የማይታይበት መሆኑ በተግባር እየታየ ነው ይህ አካሄድ አፋጣኝ እልባት ካላገኘ ለእግር ኳሳችን እድገት አደጋ ነው፡፡ ስለዚህም የእግር ኳስ ባህላችን ወዴት እያመራ ነው ለሚለው ጥያቄ አስቸኳይ መፍትሄ የሚያስፈልገው ይሆናል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋች ፍፁም ገ/ማርያም በውሰት ኤሌትሪክ ገባ

በዘንድሮው የውድድር ዘመን የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የሀገር ውስጥ ውድድሮች እና ከዚህም በተጨማሪ ሀገራችንን በመወከል በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ጨዋታዎች ይጠበቁታል፡፡ በነዚህ ውድድሮች ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ እና ውጤታማ ለመሆንም ክለቡን የሚያጠናከሩ ስራዎችን መስራት የሚያስፈልጉ በመሆኑ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ክለባችንን በችሎታቸው መጥቀም የሚችሉ ተጨዋቾችን እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡ ከነዚህም መካከል ከኤሌትሪክ ራምኬል እንዲሁም ከደደቢት እስቻለው ታመነ ቡድናችንን የተቀላቀሉ አዳዲስ ተጨዋቾች ናቸው፡፡

ቀደም ሲል ባለፉት አመታቶች ለቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በመጫወት ካሳለፉት ተጨዋቾች መካከል መካከል በቅድሚያ ለሁለት አመት ኮንትራት በመፈረም በ2007 ዓ.ም ቡድናችን ተቀላቅሎ በመጫወት ያሳለፈው ተጨዋች ፋሲካ አስፋው የአንድ አመት ኮንትራት ቢኖረውም በዘንድሮው የወድድር ዘመን በውሰት እንዲጫወት አዳማ ከተማ ቡድን ውስጥ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ሌላው ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሦስት አመታት ለቡድናችን በፊት አጥቂ መስመር ስፍራ በመጫወት ያሳለፈው ፍፁም ገ/ማርያም የአንድ አመት ኮንትራት ቢቀረውም በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለኤሌትሪክ ቡድን በውሰት እንዲጫወት መደረጉ ታውቋል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ አምስት አባል ደጋፊዎቻችን የአመታት ክፍያቸውን አጠናቀቁ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የበርካታ ደጋፊዎች ባለቤት ነው፡፡ ለረጅም አመታትም ክለቡን ከልብ የሚወዱ አፍቃሪ ደጋፊዎች አሉት፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የሚያደርጋቸውንም ጨዋታዎች በቅርበት ሆነው በመከታተል እና የሞራል ድጋፍ በመስጠት ለውጤቱ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጾ እያበረከቱም ይገኛሉ፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን አዛውንቶች ወጣቶች ሴት እህቶቻችን እንዲሁም ህፃናቶች የአባልነት ካርድ መታወቂያ በማውጣት ወርኃዊ ክፍያቸውን በመክፈል የክለቡ አፍቃሪና ደጋፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ አባል ደጋፊዎች በመሆን መታወቂያ በማውጣት ለረዥም አመታት ያሳለፉ አሁንም እንዲሁም ወደፊትም ለመቀጠል ለክለባቸው ያላቸውን አጋርነት በማሳየት ላይ የሚገኙ በርካታ ደጋፊዎች እንደሚገኙ የሚታወቅ ነው፡፡ በአሁን ወቅትም አዲሱን የአባልነት የመታወቂያ ካርድ በማውጣት ወርኃዊ ክፍያቸውን በመክፈል ላይ የሚገኙ በርካታ ደጋፊዎች እንደሚገኙ የሚታወቅ ይታወቃል፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ተመዝግበው የአባልነት የመታወቂያ ካርድ ለማውጣት የበቁ በአጠቃላይ ከአስራ ሁለት ሺህ በላይ ደጋፊዎች ሲሆኑ ይህም በኢትዮጵያ ክለቦች ታሪክ የመጀመሪያው ያደርገዋል፡፡ በተለይ ቅርብ ቀናት ጀምሮ የበፊቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ የአባልነት የመታወቂያ ካርድ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ካርድ እየተቀየረ በመሆኑ የክለባችን በርካታ ደጋፊዎች በቅሎ ቤት በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ጽ/ቤት በመምጣት የበፊቱን ካርድ አዲስ በተዘጋጀው የአባልነት መታወቂያ ካርድ በመቀየር እና የ2008 ዓ.ም ክፍያቸውንም እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡ ሰሞኑንም ከወራት ክፍያ አልፈው የአመታት ክፍያቸውን በመፈፀም የቀድሞ የአባልነት የመታወቂያ ካርዳቸውን አዲስ በተዘጋጀው የመታወቂያ ካርድ ሲለወጡና አምስት በአርያነት የሚጠቁ ደጋፊዎችን መመልከት ችለናል፡፡ እነርሱም አቶ የኔታ ሙልጌታ እስከ 2014 ዓ.ም፣ አቶ አስመላሽ መላኩ የመ.ቁ 002838 እስከ 2011፣ አቶ ወልዴ ኃ/ማርያም የመ.ቁ 005148 እስከ 2010፣ አቶ ቴዎድሮስ በዳኔ የመ.ቁ 001062 እስከ 2010፣ ኢንጅነር ዮሐንስ ገ/ጊዮርጊስ እስከ 2009 ዓ.ም የአባልነት ክፍያቸውን አጠናቀው መክፈላቸው ታውቋል፡፡