Newsletter Signup

Sign-up to stay in touch with Saint George FC

Reagent/Protectorator
Yidnekatchew Tessema
Mengistu Worku

St. George Gallery

News

ትኩረት ለስፖርታዊ ጨዋነትትኩረት ለስፖርታዊ ጨዋነት

በሁሉም የአዲስ አበባ ስታዲየቦታዎች የሚገኙ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊ አስጨፋሪዎች በስፖርታዊ ጨዋነት እና በስታዲየም ስነምግባር ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ፅህፈት ቤት ተገኝተው ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡ በዚህም መሰረት የስፖርት ክለቡ ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ የታየው ጥሩ የአደጋገፍ ስነ ስርዓት ደጋፊዎቹን እያመሰገነ ወደ ፊትም ክለቡን ብቻ የተመለከቱ ዜማዎች እና የድጋፍ አይነቶችን ከአስጨፋሪዎች እንደሚጠብቅ ይገልፃል፡፡

የችግሩ ባለቤት ማነው ? የችግሩ ባለቤት ማነው ?

አሁን በሥራ ላይ ያለው የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች መስከረም 28 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገ ጠቅላላ ጉባኤ የሃገሪቱን እግር ኳስ ለመጭዎቹ አራት አመታት በበላይነት አንዲመሩ በእግር ኳሱ ባለድርሻ አካላት ተመረጡ:; ከተመረጡ ዛሬ ሁለት ዓመት ከአንድ ወር አስቆጥረዋል:: በዚህ የሁለት ዓመት የኃላፊነት ዘመናቸው ሊያስመሰግናቸው የሚችል መልካም ሥራ ቢጠቀስ ከአስራ ሰባት ዓመት በታች የፕሪሚየር ሊግ ውድድር እንዲጀመር ማድረጉና የፕሪሚየር ሊጉን መጠሪያ ለመሸጥ ያደረገው ጥረት ጅምር ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ ሰርተዋል::

     የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዚህ የሁለት ዓመት የስራ ቆይታቸው ባብዛኛው የሚሰራቸው ስራዎችና የሚወስዳቸው ውሳኔዎች የስፖርቱን መንደር ነጋ ጠባ ሰላም እየነሳው በእግር ኳሱ ባለድርሻ አካላት መካከል መተማመን እንዳይኖር ስፖርተኞች ተረጋግተው ሥራቸውን እንዳይሰሩና ኃላፊነታቸውን እንዳይወጡ ወዘተ----ወዘተ እያደረጉት ይገኛሉ:: እስቲ በእነዚህ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ተላልፈው የተገኙ ውሳኔዎችንና በእንዝላልነት የተፈፀሙትን ዋና ዋና ስራዎች አንስተን እንመልከትና ፍርድ እንስጥ::

1ኛ በአቶ ጁነዲን በሻህ የሚመራው የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ወደ ሥልጣን በመጣ በ10ኛ ወር ሐምሌ 13 ቀን 2006 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በ2015 በኒጀር አዘጋጅነት ለሚካሄደው /ተካሂዷል/ የአፍሪካ ታዳጊዎች ዋንጫ ማጣሪያ የጋቦን አቻውን በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲገጥም ሲደረግ ሃገርን ያዋረደ የስፖርት ቤተሰቡን በእጅጉ ያሳዘነና ያስደነገጠ ተግባር ፈፅመዋል::

     ይኸውም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዕድሜ ችግር በአንድ ተጠባባቂ ተጨዋች ብቻ ወደ ሜዳ እንዲገባ ተደርጓል:: ይህ ስህተት የተፈፀመው በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የአሰራርና የመረጃ አያያዝ ዝርክርክነት ነው::

2ኛ/ እስከ 2007 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ሲሰራበት የነበረውና ኋላቀሩን የተጨዋቾች ዝውውር ደንብ ሲያረቁ ኃላፊነት በተሰጣቸውና የጉዳዩ ባለቤቶች ከሆኑት ተጨዋቾች ጋር ጥልቅ ትንተና በቂ ጊዜ ወስዶ ፍተሻ ሣያደርግበትና ስምምነት ላይ ሣይደርስበት በችኮላ በማን አለብኝነት ከጥር 25/2007 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ለክለቦች መመሪያ አስተላልፎ ብዙም ሳይቆይ በተጫዋቾች ዘንድ ጩኸቱ ሲበረታበት “ለጊዜው” በሚል ተግባራዊ ሣይደረግ ቀርቶ ከሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ተደረገ /የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ከባህላዊ የተጨዋቾች ዝውውር ወደ ዘመናዊ ህግና ደንብ ያለውን ዝውውር አይቃወምም የሚቃወመው ያለጥናት መካሄዱና ሥምምነት ላይ ሳይደርስ ተግባራዊ እንዲደረግ የተላለፈው ውሳኔን ነው::

3ኛ/ ከሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ አንድ ክለብ 3 የውጭ ሃገር ተጨዋቾች ብቻ ማስመዝገብ እንዳለባቸው የሚደነግግ መመሪያ አውጥቶ ተግባራዊ እንዲደረግ ለክለቦች በተነ እንጎዳለን መመሪያው ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ተገቢው ጊዜ ተወስዶ ሳንወያይበትና ሣንመካከርበት የወጣ መመሪያ ነው ብለው ክለቦች አቤቱታ አቀረቡ ብዙም ሣይቆይ ቀድሞ ወደነበረበት 5 የውጭ ተጨዋቾች ማስመዝገብና ማጫወት እንዲችሉ ተወስኗል::ይህም ውሳኔ ከመተላለፉ በፊት በውይይት እንዳልዳበረና ሥምምነት ላይ እንዳልደረሰ የችኮላ ውሳኔ መሆኑን ያሳውቃል::

4ኛ/ ከባለድርሻ አካላቱ ጋር ሳይመካከር ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲን ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ማድረጉና በኋላም ክለቦችን ይቅርታ መጠየቁ የውዝግብ ቤት መሆኑን ያሳያል፡፡ 5ኛ/ ካለፈው ሳይማር እንደገና የታይትል ስፖንሰርሺፕ ለማድረግ የሄደበት አግባብ አወዛጋቢ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡

6ኛ/ የሴት ብሔራዊ ቡደናችን በ2016 በሚያከናውነው የአፍሪካ ዋንጫና የኦሎምፒክ ማጣሪያ ከዕጣ ድልድል ውጭ እንዲሆን መደረጉን ደግሞ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እየሰማን እንገኛለን ይህ ደግሞ ፌዴሬሽኑ ከባለፈው ስህተቱ የማይማርና በባለሙያ እንደማይመራ በድጋሚ አረጋግጧል::

     የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሁለት ዓመት የስራ ዘመኑ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ችግሮችና ልብ አሻካሪ ውሳኔዎችን ፈፅሟል ጠለቅ ተብሎ ሲፈተሽ ብዙ ጉዳጉድ ማውጣት እንደሚቻል ይታወቃል የተፃፈ ህግ ትተው ሽምግልናና ድርድር ሲያደርጉ መመልከት የተለመደ ሆኗል:: በዚህም ነው ፌዴሬሽኑ ምን እየሰራ ነው ብለን እንድንጠይቅ የተገደድነው ቀደም ሲል የነበረውና በአቶ ሳህሉ ገ/ወልድ ይመራ የነበረው የፌዴሬሽኑ አመራሮች ሁለት ቢጫ ካርድ የተመለከተውን ምን ያህል ተሾመን በቦትስዋና ጨዋታ ላይ አሰልፈው በመገኘታቸው ፊፋ በብሔራዊ ቡድኑ ላይ የ3 ነጥብ ቅነሣ በማድረጉ የስፖርት ቤተሰቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተቋውሞውን ማሰማቱ የሚታወስ ነው:: በወቅቱ የነበረው የፌዴሬሽኑ አመራሮች ኃላፊነቱ የአሰልጣኙ ነው፣ የቡድን መሪው ነው፣ የፅ/ቤት ኃላፊው ፣የተጨዋቾች ወዘተ-- እየተባለ ሚዛን የማይደፋ ምክንያቶች ቢደረደሩም ተቀባይነት አላገኙም በዚህም አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት በግልፅ የተፈጠረውን ሰህተት ይቅርታ በመጠየቅና በመጨረሻም ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል::

   አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከበፊቱ ከአቶ ሣህሉ ገ/ወልድ ሥራዎች ጥሩውንና በጎውን መውሰድ ሲገባቸው በዕዛው በጥፋት መንገድ መጓዛቸው አነጋጋሪ ሆኗል:: አሁን በሴት ተጨዋቾች ላይ የፈፀሙት ሥህተት የሴት ተጨዋቾችን ቅስም እንዲሰብርና ተስፋ እንዲቆርጡ መጭውንም ጊዜ እንዲጨልምባቸው አድርገዋል::

     በኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች በችኩልተኝነት የሚሰሩት ሥራዎች ተገቢው ጥናትና ምክክር ሳይደረግባቸው ያለሙያተኛ የሚወጡ መመሪያዎች እግር ኳሱ ከሚመራበት ውጭ መውጣት የተፃፈ ህግን ከመተርጎም ይልቅ በባህላዊ ሽምግልና ለመስራት የሚያደርጉት ጥረት የሃገራችንን እግር ኳስ በእጅጉ እየጎዳው ይገኛል:: በፌዴሬሽኑ ውስጥ የተሰባሰቡ “ሙያተኞች” ተብዬዎች እስከዛሬ አውቀውም ሆነው ሳያውቁ በሚፈፅሙት ጥፋት በወቅቱ አለመጠየቃቸው ጥፋቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና እያደገ እንዲሄድ አድርጎታል ቀደም ሲል በወጣት ቡድኑ በሉሲዎች ስህተት ተፈፅሞ የተገኘ ቢሆንም የተወሰደ የዕርምት ዕርምጃ የለም በእነሱ ቸልተኝነት ለተፈጠረው ሃገራዊ
ውርደት የሚመለከታቸው ሃላፊዎች ተጠያቂ መሆን ይኖርባቸዋል::

     አሁን የተፈጠረው ስህተት ለሁላችንም ማንቂያ ደውል ነው ሃገራችን ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለውን የሴት እህቶቻችን የእግር ኳስ መነቃቃት አስቡ፤ ትልቅ ቦታ እንደርሳለን ፕሮፌሽናል ሆነን የሃገራችንን ስም እናስጠራለን እያሉ ላባቸውን የሚያፈሱትን እነ ሎዛ አበራንና የሌሎች ታዳጊዎች ተስፋቸው በእንጭጩ አንዳይቀር ተግታችሁ ሥሩ::

የኢትዮጵያ እግር ኳስ በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች የእስካሁን አሰራራቸውን ቆም ብለው መፈተሽና መመርመር ይጠበቅባቸዋል:: ከምንም በላይ ደግሞ ተቋሙ የተጠያቂነት ሥርዓት በተገቢው መንገድ ማበጀት ይኖርበታል፡፡ እግር ኳሱ በሰው ሰራሽ መሰናክሎች እንዳይተበተብ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ከእንግዲህ በኋላ ተመሳሳይ ሥህተቶች እንዳይደገሙ አሰራራቸውን በሙያተኛ የታገዘ ማድረግ ይኖርባቸዋል ስህተት እንኳን ተሰርቶ ከተገኘ ፈጥነው መግለጫ መስጠትና ሰህተቱን ለማረም መጣር ያስፈልጋል:: ይህንን ማድረግ ደግሞ የሁሉም ኃላፊነት መሆን ይኖርበታል::

‹‹ጊዮርጊስ ማንንም ተለማምጦ አያጫውትም››ይድነቃቸው‹‹ጊዮርጊስ ማንንም ተለማምጦ አያጫውትም››ይድነቃቸው

የቱርክን ቡድን በወዳጅነት ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ የገጠመው የኢትዮጵያ ቡድን ግብ ማግኘት አልቻለም፡፡ቱርክ እየመራ ነው፡፡ተመልካቹ መመራቱን አልወደደውም፡፡ከመንግስቱ ግብ ይፈልጋል፡፡መንግስቱ ደግሞ ኳስ ስላጣ ተናዷል፡፡

   ወዲህና ወዲያ ቢሯሯጥም ኳስ የሚባል ነገር የሚሰጠው አላገኘም፡፡በእረፍት ተጫዋቾቹ ወደ ውስጥ ገቡ፡፡ መንግስቱ ይናገራል‹‹.....ጋሽ ይድነቃቸው በእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል መጣ፡፡ ወደ ውስጥ ስገባ ተጨዋቾቹን ለምን ኳስ ትከለክሉኛላችሁ እያልኩ እየተጨቃጨቅሁ ነበር፡፡

       እኔ ተናድጄ ቁጭ ብያለሁ፡፡ጋሽ ይድነቃቸው  መልበሻ ክፍል ገብቶ እየመከረን ሳለ  በእኔ ግብ ያለማግባት ቅር ተሰኝቶ ጠራኝና‹‹ስማ መንግስቱ!! አበድክ እንዴ!!እንደዚያ ምን ያደርግሀል?›› ሲለኝ የባሰ ተናደድኩኝ፡፡

               እርሱ አባባሉ ዛሬ ምን ሆንክ፡፡፡ያለኳስ ለምን ትሮጣለህ?ለማለት ነው፡፡እኔ ደግሞ ተማሪ ስለሆንኩ ልጅነትም ስላለ ሜዳ ላይም ኳስ በማጣቴ ስለተናደድኩኝ ‹አበድክ እንዴ?› ሲለኝ‹‹እኔ ነኝ እብድ?እኔ ካበድኩኝ ጤነኛ ሰው ፈልገህ አጫውት፡፡ፌዴሬሽን ድሮም ምንም አላደረገልኝም››ብዬ ማሊያዬን አውልቄ ወረወርኩ፡፡ጫማዬን ወደዚያ ጣልኩና በሩን በሀይል መትቼ ወጥቼ በትሪቡን አደረግሁና ሄድኩ፡፡

    የምጓዘው ወደ ትምህርት ቤት ነው፡፡የምማረው መድሀኒያለም  ነው ፡፡ያንጊዜ አዳሪ ስለነበር ከዚያ እየመጣሁ ነው የምጫወተው፡፡ይታያችሁ!! ከስታዲየም ትምህርት ቤት ድረስ በንዴት በእግሬ ልሄድ ወጣሁ፡፡ትሪቡን የነበሩት ሰዎች ወዲያውኑ ነገሩን ሰምተው መኪና ይዘው ተከትለውኝ መጡ፡፡ብዙዎቹ የኛ ቲፎዞዎች ናቸው፡፡ወደ ሜዳ ሊመልሱኝ ነው የመጡት፡፡

    እኔም ንዴት ስላለብኝ እንዳይጠጉኝ ነገርኳቸው፡፡እየሄድኩ ሲጠጉኝ ድንጋይ አንስቼ መወርወር ጀመርኩ፡‹‹እሺ እናድርስህ›› ሲሉኝም አባረርኳቸው፡፡በእግሬ ነገር እየበላሁ ት/ቤት ገባሁና ሁለተኛ ኳስ የሚባል ነገር አልጫወትም ብዬ ቀረሁ፡፡የወሰንኩት በንዴት ነው፡፡

      በሌላ ቀን ጓደኞቼ ጋዜጣ አምጥተው አሳዩኝ‹‹ከሜዳ ጥሎ በመውጣቱ መንግስቱ 2 ወር ተቀጣ››ይላል››፡፡እኔም እንኳን 2 ወር እስከ ዘልአለሙ ይቅጡኝ ብዬ ወሰንኩ፡፡

      ከጊዜ በኋላ ግን የእኔ ከኳስ ሜዳ መጥፋት ብዙዎቹን ስላሳሰበ ወደ ጋዜጦች ክፍል ይደወል ጀመር፡፡ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ ጋር  እንግባባለን ብቻ ሳይሆን በጣም እንዋደዳለን፡፡ሰለሞን ትምህርት ቤት መጣና‹‹ስማ መንጌ!!አንተ ገና ወጣት ነህ፡፡እኔ የችግሩን መንስኤ ስሰማ ያለመግባባት መሆኑን ተረድቻለሁ ፡፡

                ጋሽ ይድነቃቸው በአንተ ከሜዳ ጥሎ መሄድ ተገርሟል፡፡ይቅርታ ብትልና ወደ ሜዳ ብትመለስ ጥሩ ነው፡፡ብዙዎቹ የአንተ አድናቂና ቲፎዞዎች በአንተ ከኳስ ሜዳ መለየት ደስተኛ አይደሉም፡፡አንተ ይቅርታ ይደረግልኝ ብትል ፌዴሬሽኑ ወዲያውኑ ቅጣትህን ያነሳልሃል፡፡

               በቅርብ ጨዋታ ስላለ በዚያ ግጥሚያ እንድትሰለፍ ሁሉም ይፈልጋል፡፡ ሰዎች በስልክ እየደወሉ ስላንተ ጉዳይ እየጠየቁ እኔንም አስቸግረውኛል፡፡ ስለዚህ ይቅርታ ጠይቅ፡፡እነርሱ ለማንሳት ዝግጁ ናቸው››አለኝ ፡፡

    እኔም አነጋገሩ ልብ የሚነካ ስለነበር ያለውን ብቀበልም እልህ ስለያዘኝና ማንም መጥቶ ያነጋገረኝ ስላልነበር ‹‹ተዋቸው!! ምንም ችግር የለውም ዞረን ዞረን ልንገናኝ እንችላለን›አልኩት በዚያው ተለያየን፡፡ወደያውኑ እኔን ተችቶ ጋዜጣ ላይ አወጣ፡፡ ዝም አልኩት በሌላ ቀን መንግስቱ ይቅርታ ጠየቀ ብሎ ጻፈ ፡፡በዚህን ጊዜ በጣም ተናደድኩ ፡፡እንዴት እንደዚህ ይጽፋል ብዬ ቅር ተሰኘሁ››ይላል ፡፡

በሰለሞን ሁኔታመንጌ ተቆጣ፡፡ ቁጣውንም አምቆ ያዘ፡፡ ከጥቂት ቀን በኋላ ሁለቱም መንገድ ላይ ተገናኙ፡፡ ሰለሞን ወደ መኪናው እየገባ ነበር፡፡ መንግስቱ በፍጥነት ወደ ሰለሞን መኪና ሄደ፡፡ ሰለሞንንም ከመኪና አወረደው፡፡ ሰለሞን ግራ ተጋባ፡፡ መንግስቱ በቴስታ አለው፡፡ ተጨማሪም ድብደባ አካሄደ፡፡ ሲበቃው ትቶት ሄደ፡፡ ሰለሞንም ተጐዳ፡፡ ሰዎች ተሰበሰቡ፡፡ ግርግር ተፈጠረ ፡፡ፖሊሶች መጡ መንግቱን ወደጣቢያ ወሰዱት፡፡

                ሰለሞን ታክሞ ሲመጣ መንግስቱ ታስሯል፡፡ በእርሱ ምክኒያት መታሰሩ የሚያመጣው ጣጣ እንዳለ ሆኖ ጓደኛው በመታሰሩ ነገሩን ሊቀበለው አልቻለም ፡፡ፖሊሶች አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መንግስቱን አስገብተው ሰለሞንን ሸኙት፡፡ምሽት ላይ ተረኛ ፖሊሶች አብዛኛዎቹ በኳስ ሜዳ የሚገቡ የመንግስቱ አድናቂዎች ስለነበሩ ከውስጥ አስወጥተው እነርሱ ያሉበት ክፍል አስገቡትና ካፖርታቸውንና መለዮውን ሰጥተውት  በምሽት የሚመጡትን ጥፋተኞች እየመዘገበ ገቢ እንዲያደርግ መዝገቡን ሰጥተው አስቀመጡት ፡፡በነጋታው ሰለሞን የበላይ አለቆቹን በማሳመን እርሱ ከሳሽ እንዳልሆነና በእርሱ ጥፋት መንግስቱ እንደደበደበው በማሳወቅ አስፈታው፡፡ነገሩ በዚህ አላቆመም ፡፡መንግስቱ የተጣላው ከጋሽ ይድነቃቸው ነው፡፡ያን ግዜ ጊዮርጊስን የሚያሰለጥነው ይድነቃቸው ነበር፡፡መንግስቱ ልምምድ አልመጣም፡፡

              በሁለተኛውም ቀን ቀረ፡፡በሶስተኛ ቀን መጣ፡፡ለምን እንደቀረ ምክኒያቱን ተጠየቀ፡፡በተፈጠረው ሁኔታ ተናዶ መሆኑን ተናገረ፡፡ይድነቃቸውም‹‹የህዝብ አድናቆት እያገኘህ ስትመጣ ጸባይህ እየተበላሸ ነው››ብሎ ገሰጸው፡፡መንግስቱ የይድነቃቸውን ተግሳጽ አልተቀበለውም፡፡ የተናገረው በተጨዋቾች ፊት በመሆኑ ተናደደ‹‹ከዛሬ ጀምሮ እንዲያውም ለጊዮርጊስ አልጫወትም››ብሎ ትቶ  ሄደ፡፡መንግስቱ ለጊዮርጊስ ወሳኝ ተጫዋች ነው፡፡ደጋፊው ሁኔታው ግራ አጋባቸው፡፡ በጣምተበሳጩ ፡፡ይባስ ብሎ የመጣው ወሬ አናደዳቸው፡፡ መንግስቱ ገነት ጦር ትምህርት ቤት የወጣውን ፈተና መውሰዱን ሰሙ፡፡ይሄ ደግሞ አደገኛ ነው ፡፡

               ገነት ጦር ትምህርት ቤት ከገባ ወታደር ሆኖ ለመቻል ይጫወታል ማለት ነው፡፡ደጋፊው ተሯሩጦመንግስቱ ቤቱ ድረስ ሄደው አልቅሰው ለመኑት፡፡የሚፈልገውን እንደሚያደርጉለት  ቃል ገቡለት፡፡ወደ ልምምድ ሜዳ ይዘውት ሄዱ፡፡ይድነቃቸው ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም፡፡መንግስቱ ተለምኖ ነው የመጣው ፡፡ይድነቃቸው ግን‹‹›ጊርጊስ አይከፍልህም እናውቃለን እኛ ምንም ገንዘብ የለንም፡፡ለክለባችን በጣም ታስፈልጋለህ ደጋፊው እግርህ ላይ ወድቆ ያመጣህ ወሳኝ ተጫዋች ስለሆንክ ነው፡፡ ነገር ግን ጊዮርጊስ ማንንም ለምኖ ስለማያጫውት  አንፈለግህም፡፡መመለስ ከፈለግህ ትሬኒንግ ረግጠህ በመሄድህ ጣፋተኛ መሆንህን አውቀህ ቅርታ ስትጠይቅ ብቻ ነው፡፡

                      ይቅርታው ክለቡን ብቻ ሳይሆን እዙሁ ሜዳ ልጆቹን ይቅታ መጠየቅአለብህ ምክኒያቱም እነዚህ ልጆች ናቸው ላንተ ኳስ እየሰጡህ ያሳወቁህ ››አለው መነግስቱ ተለምኖ በመምጣቱ አሁን ይድነቃቸው የተናገረውን አልተቀበለም፡፡እንደገና ተወቶ ሄደ፡፡ደጋፊው የይድነቃቸውን ውሳኔ ታቀወሙ፡፡መንግስቱ ወታደርነት ተቀጥሮ መቻል ሊገባ መሆኑን ነገሩት፡፡እሱ ግን ምንም አላስፈራውም‹‹ጊዮርጊስ የሚፈልገውን እንጂ የማይፈልገውን አይቀበልም፡፡ ክለባችን ማንንም ተለማምጦና ለምኖ አያጫወትም››ብሎ ነገራቸው፡፡የደጋፊው ስጋት መንግስቱ ተቃራኒው ክለብ ይገባል በሚል ነው፡፡ ከቀናት  በኋላ መንግስቱ ወደ ጽፈት ቤት መጣ፡፡

                     ነገሩን እንዲህ ያስታውሳል‹‹ጊዮርጊስን ወዳለሁ ይድነቃቸው ሲናገረኝ ወጣት ስለሆንኩኝ ግንፍል የሚል ስሜት ስለነበረኝ ትቼ ሄድኩኝ፡፡ ነገሩን ሳስበው የታወቅሁት በጊርዮጊስ ነው፡፡  ስነስርአት በማክበር እኔ ለሌላው አርአያ ካልሆንኩኝ ክለቡን እጎዳለሁ፡፡ በቀጥታ ቢሮ ሄጄ ይድነቃቸውን አገኘሁት ፡፡ይቅርታ ጠየቀሁኝ፡፡ብዙ ነገር መከረኝ ፡፡በእግር ኳስ ትልቅ መሆን የሚቻለው በዲስፕሊን መመራት ከተቻለ ብቻ እንደሆነ ነገረኝ፡፡ ከዚያ ወዲህ ሁሉንም ነገር ለጊዮርጊስ ሰጠሁና መጫወት ጀመርኩ፡፡ አንድም ቀን ደሞዝ ሰጥተውኘም እኔም ጠይቄ አላውቀም››ይላል፡፡ ደጋፊዎቹ በይድነቃቸው አመራር እና በተገኘው ውጤት ተገረሙ፡፡ከዚያ ወዲህ ማንም ደጋፊ ተጫዋች ባኮረፈ ቁጥር እየተለማመጠ መጫወት እንዴለበት ስለወቁ ይሁን ነገር ተውት፡፡

ዲስፕሊን፡- አንዱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሻምፒዮንነት ሚስጥርዲስፕሊን፡- አንዱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሻምፒዮንነት ሚስጥር

                                    የጊዮርጊስ ቡድን ከአየር መንገድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ እየተጠበቀ ነው፡፡አየርመንገድ ተከላካዩ አስቸጋሪ በመሆኑ ይሄንን መስመር ሰብሮ ጎል ለማግባት ይችላል ብለው የሚተማመኑበት መንግስቱ ወርቁ ነው፡፡በዛሬው ጨዋታ ከመንግስቱ ደጋፊው ብዙ ይጠብቃል፡፡ ወደ ሜዳ የገባው ቡድን ሲታይ የሚጠብቁትበና የሚፈልጉት ተጫዋች ሜዳ ላይ የለም፡፡ምናልባት ቶሎ ከመልበሻ ክፍል ሳይወጣ ቀርቶ ነው በሚል ገመቱ፡፡

                                   ወደ ሜዳየገባውን ተጨዋች ሲቆጥሩ አስራ አንድ ናቸው፡፡ነገሩ ግራ ገባቸው ፡፡ተጠባባቂ ተጫዋቾች ከመልበሻ ክፍል ወጥተው ወደ መቀመጫቸው እየሄዱ ነበር፡፡ከነዚህ ውስጥ መንግስቱን ተመለከቱት አንዳንዶቹ‹‹አይናችን ነው ወይስ....››እስከማለት ደረሱ፡፡እነዚህ ሰዎች መንግስቱን  በችሎታው ቤንች ሆኖ አይተውት አያውቁም፡፡አሁን ስላዩት ተገረሙ፤ተደነቁ፤ግራ ተጋቡ፤እንዴት ይሆናል ብለው መቃወም ጀመሩ፡፡አሰልጣኙ በቅርብ ጊዜ  ነው ቦታውን የተረከበ ፡፡እንዴት ደፈረን ?አይነት በመንግስቱ ቤንች መሆን መቆሚያ መቀመጫ አሳጡት፡፡

                             አሰልጣኝ ወልደ መስቀል ኮስትሬ ግን ተቃውሞውን ከምንም አልቆጠረም‹‹ከሀንጋሪ እንደተመለስኩ ኮተቤ ነበር የተመደብኩት፡፡ለኮተቤ ምርጥ እነዶክተር ተቀዳ፤ሸዋንግዛው፤ያረጋልና ሌሎችም ይጫወቱ ነበር፡፡ እዚያ እያሉ አሰራቸው ነበር፡፡ፍሰሃ ለጋሽ ይደነቃቸው ነገረውና ጊዮርጊስን እንዳሰለጥን እድሉ ተሰጠኝ፡፡ ወደ ቡድኑ ስመጣ ነባሮቹ እየለቀቁ ወደ ውጭ ሄደው ነበር፡፡ቡድኑ ባዶ ሆነ፡፡  ከታችኛው ቡድን እነ ስዩም አባተ፤ መሀመድ ቱርክ፤ተስፋዬ ስየምና ዘሪሁንን አሳደግኋቸው፡፡ መንግስቱ ያን ጊዜ ገባ ወጣ ይል ነበር፡፡

                 አንድ ቀን ወሳኝ ግጥሚያ እያለን ለመጫወት መጣ፡፡እኛ ቡድን ውስጥ ህግ አውጥቼ ነበር፡፡ይሄንን ኮሚቴውም አጽድቆልኛል፡፡ በሳምንት  4 ጊዜ ነው ልምምድ የምናደርገው፡፡ ሁለቱን ቀን ቴክኒክ፤ሁለቱን ቀን ደግሞ የአካል ብቃት እንሰራለን፡፡የጊዮርጊስ ተጫዋቾች በተለያየ መስሪያ ቤት ነው የሚሰሩት፡፡ ለልምምድ ፍቃድ ጠይቀው ነው የሚመጡት፡፡ ይሄንን ግምት ውስጥ በማስገባት የወጣው ህግ ማንኛውም ተጫዋች አንድ ቴክኒክና አንድ አካል ብቃት ትሬኒንግ መስራት ግዴታ ነው፡፡ ይሄን ካላሟላ አይሰለፍም፡፡

                                    መንግስቱ ልምምድ መቅረት ጀመረ ፡፡አስርቀን ቆይቶ  ሊሰለፍ መጣ፡፡ወሳኝ ጨዋታ ስለነበር ቲፎዞዎች ናቸው ይዘውት የመጡት ፡፡ እንደሚሰለፍ ነው የሚያውቁት፡፡ተጫዋቹ ለሁለት ተከፈለ ፡፡የጨዋታውን ክብደት አይተው ግማሹ  ይግባ ሌላው ደግሞ መግባት የለበትም አሉ፡፡አሰልጣኙ እኔ ስለሆንኩ መወሰን ነበረብኝ፡፡ ህጉ መከበር እንዳለበት አመንኩ፡ መንግስቱን ጠራሁትና‹አንተ ከኔ ጋር ወንበር ላይ ሆነህ ትረዳኛለህ› አልኩት፡፡ተጠባባቂ ሆነ፡፡ ልጆቹ ቤንች መሆኑን አላመኑም፡፡ ከዚያ ሁሉም ለህጉ ተገዢ ሆነ፡፡

                  እርሱም ቢሆን ከዚያ በኋላ ልምምድ አክብሮ በመምጣት ለሌሎች አርአያ ሆነ፡፡ከዚያም በኋላ ቢሆን በሌሎች ወሳኝ ጨዋታ መንግስቱ ቤንች ሆኗል፡፡በችሎታ ሳይሆን ልምምድ ባለመሟላቱ ነው፡፡እንዳውም ቢ ቡድን ወርዶ እንዲጫወት ተደርጓል፡፡ ደጋፊው ስለሚወደው የ ቢ ውድድር ላይ እየሄደ ይመለከት ነበር፡፡ጊዮርጊስ ቡድን ውስጥ ዲስፕሊን በመከበሩ ነው ውጤታማ መሆን የተቻለው፡፡

ርዕሰ አንቀፅ ሰማንያኛ አመት የምስረታ በአላችንን የተሳካ ለማድረግ የሁላችንም ርብርቦሽ ያስፈልጋልርዕሰ አንቀፅ ሰማንያኛ አመት የምስረታ በአላችንን የተሳካ ለማድረግ የሁላችንም ርብርቦሽ ያስፈልጋል

የሀገራችን ኢትዮጵያና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ የበኩር ስፖርት ማህበር የሆነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የተመሰረተበትን ሰማንያኛ አመት በመጪው ታህሳስ ወር እጅግ በደመቀ ሁኔታ ያከብራል፡፡ ይህንን ክብረ በአል እጅግ የደመቀ ለማድረግ ክለቡ ደጋፊዎችን በማሳተፍ ጭምር ከአንድ አመት በላይ ለሆነ ጊዜ ዝግጅችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

የያዝው የህዳር ወር የበአሉ ዋዜማና የቅድመ ዝግጅታችን ማጠናቀቂያ እንደመሆኑ መጠን አብዛኞቹ የየኮሚቴዎቹ ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ሲሆን የዝግጅት እና የቦታ መረጣ ተከናውኖ በአሉ የሚከበርባቸው ቦታዎች ከወዲሁ በመያዝ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢንተርናሽል የወዳጅነት ጨዋታዎች፤ ከጀግኖች አርበኞች ጋር በመተባበር የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብን የአርበኝነት ታሪክን የሚዘክር ዝግጅት፤ ሲምፖዚየም፤የሽልማት ፕሮግራሞች፤ የደጋፊዎች የእግር ኳስ ጨዋታ ውድድር፤ የገና ባዛር እና ኤግዚቢሽን፤ የሙዚቃ ዝግጅት እና የቁንጅና ውድድር በአሉን ለማክበር ከተዘጋጁት ዝግጅቶች ውስጥ ዝግጅታቸው የተጠናቀቁና እንደሚካሄዱ የተረጋገጡት ናቸው፡፡ በቀጣይ ሳምንታትም ቀሪ ኮሚቴዎች ዝግጅታቸውን ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሰማንያኛ አመት ክብረ በአሉ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ የመጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን ድምቀቱና ስኬቱ እንዲሁም ፕሮግራሞቹ ታሪካዊነቱን የጠበቁ ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡ ይህንንም ለማድረግ የስፖርት ማህበሩ አመራር አካላት፤ የፅህፈት ቤት ሰራተኞች፤ የቀድሞ እና የአሁን ዘመን የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች፤ ሰፊው ደጋፊ ከበአሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር አንድ ላይ በመሆን ለበአሉ ስኬት ርብርቦሽ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ የኮሚቴዎቹ ስራ እንዳለ ሆኖ ሰማንያኛ አመት የምስረታ በአላችንን የተሳካና ደማቅ ለማድረግ ፀሀይ ዝናብ፤ ተራራ ቁልቁለትት፤ ረዥም አጭር መንገድ ሳይሉ ምንጊዜም ከክለባቸው ጎን የማይለዩት የደጋፊዎች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህም ሁላችንም የቅዱስ ጊዮርስ ስፖርት ማህበር ቤተሰቦች ከፅህፈት ቤት ሳምንታዊ በሆነው በምንጊዜም ጊዮርጊስ የራድዮን ፕሮግራም እና በየ15 ቀኑ ለንባብ በሚወጣው ልሳነ ጊዮርጊስ ጋዜጣ ላይ የሚሰጠውን የጊዜ ሰሌዳ እና መመሪያ በመከተል ለበአሉ ስኬት ከወዲሁ ዝግጅት እናድርግ፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ የአባልነት ክፍያ ክብረ ወሰን ተሰበረየቅዱስ ጊዮርጊስ የአባልነት ክፍያ ክብረ ወሰን ተሰበረ

ስሙ ገዛኸኝ ደገፉ ይባላል፡፡ቅዱስ ጊዮርጊስን ከአስር አመቱ ጀምሮ አየደገፈ ነው ያደገው፡፡ባሳለፍነው ሳምንት አርብ እለት በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በመገኘት የዛሬ ሳምንትያከብረው የነበረውን የልደት በአሉን ምክንያት በማድረግ የመጪዎቹ አስር አመታት የአባልነት ክፍያውን በመክፈል ሪከርዱን ሰብሯል፡፡ ገዛኸኝ የአባልነት ክፍያውን ከከፈለ በኋላ ከምን ጊዜም ጊዮርጊስ የሬድዮ ዝግጅት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ አባላት የሚከፍሉት ክፍያ ለክለቡ የሚጠቅም መሆኑን በመረዳቱ በልደቱ ዋዜማ ይህንን ለማድረግ እንደወሰነ ተናግሯል፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ታሪክ እስከ አሁን ድረስ የተከፈለው አስቀድሞ ክፍያ ሪከርድ ለአራት አመታት ሲሆን ገዛኸኝ ግን ለአስር አመታት ማለትም እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ በመክፈል ሪከርዱን ለአንድ ሳምንት ጨብጧል፡፡

በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የገዛኸኝ ታላቅ ወንድም በሀይሉ ደገፉ ደግሞ ከልጅነቱ ጀምሮ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዳገፊ ቢሆንም ለስራ ጉዳይ እዛው አሜሪካን መኖር በመጀመሩ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ የአባልነት ክፍያውን በስራ እና በቦታ ርቀት ምክንያት አቋርጦት ነበር፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ግን የታናሽ ወንድሙን ታሪክ በምንጊዜም ጊዮርጊስ ሳምንታዊ የራድዮን ፕሮግራም ከሰማ በኋላ አቋርጦት የነበረውን የአባልነት ውዝፍ ክፍያን በማጠናቀቅና ለመጪዎቹ 20 አመታት የሚጠበቅበትን የአባልነት ክፍያ በመዝጋት ሪከርዱን ከታናሸ ወንድሙ ተረክቧል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም

አቶ ደጀኔ ፀጋዬ እስከ 2011 ድረስ

አቶ ያሬድ ሽፈራሁ 2011 ድረስ

አቶ ይዘንጋው ሽመልስ 2011 ድረስ ለአራት አመታት አባልነታቸውን ያደሱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አባል ደጋፊዎች ናቸው፡፡

አምስት የቅዱስ ጊዮርጊስ የታዳጊ እና ተስፋ ቡድን ተጨዋቾች ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን በቢጫ ቴሴራ ለመጫወት ተመዝግበዋል፡፡ • አምስት የታዳጊ ቡድን ተጨዋቾችም ወደ ተስፋ ቡድን አድገዋልአምስት የቅዱስ ጊዮርጊስ የታዳጊ እና ተስፋ ቡድን ተጨዋቾች ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን በቢጫ ቴሴራ ለመጫወት ተመዝግበዋል፡፡ • አምስት የታዳጊ ቡድን ተጨዋቾችም ወደ ተስፋ ቡድን አድገዋል

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሶስት የወንድ እግር ኳስ ቡድኖች አሉት፡፡ የታዳጊ(ከ17 አመት በታች)፤የተስፋ(ከ20 አመት በታች) ቡድን እና የዋናው የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ቡድን፡፡ በዚህም መሰረት በየአመቱ ለውጦችን የሚያሳዩ እና ችሎታቸው ከታዳጊ ወደ ተስፋ ወይም ከተስፋ ወደ ዋናው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ያጫውታቸዋል ተብሎ በአሰልጣኞቹ የታመነባቸው ተጨዋቾች ሽግግር ያደርጋሉ፡፡

የቅርብ አመታትን ሽግግሮችን በምሳሌነት እናንሳ ካልን ከታዳጊ እና ተስፋ ቡድን ተነስተው እስከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን የደረሱትን ምንተስኖት አዳነን፤ ናትናኤል ዘለቀ፤ ዘካርያስ ቱጂ እና አንዳርጋቸው ይላቅን ማንሳት ይቻላል፡፡  በዘንድሮው አመትም ፍሬዘር ካሳ፤አቡበከር ሳኒ፤ አትክልት ስብሀት(ከተስፋ ቡድን)፤ ባህሩ ነጋሽእና ሚኪያስ ግርማ(ከ17 አመት በታች ቡድን) ተመርጠው በቢጫ ቴሴራ በመመዝገብ ለዋናው ቡድናችን መጫወት ጀምረዋል፡፡ በ2006 ዓ.ም በታዳጊ ቡድናችን ሲጫወት የቆየውና በ2007 ዓ.ም በተስፋ ቡድን እየተጫወተ የመጀመሪያ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታውን ያደረገው አቡበከር ሳኒ ዘንድሮም በሁለቱም የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ አድርጎ ተደናቂ አቋምን ማሳየት ችሏል፡፡ በአምናው የ17 አመት በታች ውድድርም ተደናቂ አቋም ያሳየው ሚኪያስ ግርማም በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መጫወት የቻለ ሲሆን በቀጣይነትም በፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን ሊያደርግ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተያያዘ ዜና በአሳምነው ገብረወልድ የሚሰለጥነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን ተጨዋቾች ምርጫ ካሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ እለትሮ ቦሌ አካባቢ በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ መለማመመጃ ስፍራ ላይ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በዘንድሮው የውድድር ዘመን የቅዱስ ጊዮርጊስ ሰፖርት ማህበር በዋናው፣ በተስፋ፣ በታዳጊ እንዲሁም በሴቶች እግር ኳሰ ቡድኖች ይወዳደራል፡፡ ባለፈው አመት በተካሄደው ውድድር የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮና እና የአሸናፊዎች አሸናፊን ዋንጫ በመውሰድ በመሆን አጠናቋል፡፡ እድሜቸው ከሃያ በታች በተካሄደው የክለቦች ውድድር ላይ የተካፈለው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ውድድሩን በሁለተኝነት ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ እድሜአቸው ከአስራ ሰባት አመት በታች በተካሄደው የታዳጊ ክለቦች ውድድር የቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ላይ ለዋንጫ ተፋላሚነት ቀርቦ በሁለተኝነት ሲያጠናቅቅ በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ላይ የሻምፒዮናው ባለድል ሆኖ የዋንጫ ባለቤት ለመሆን ሲበቃ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ባለቤትም ለመሆን ችሏል፡፡ በ2008 ዓ.ም በአሰልጣኝ አሳምነው ገ/ወልድ የሚሰለጥነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን በዘንድሮው ውድድር ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ እና ውጤታማ ሆኖ ለመገኘት ከወዲሁ በቡድኑ ውስጥ የሚቀላቀሉ አዳዲስ ተጫዋቾችን በመምረጥ ላይ ይገኛል፡፡ በአምናው የውድድር ዘመን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡደን ይጫወቱ ከነበሩት ተጫዋቾች መካከል ወደ ዋናው ቡደን ለማደግ የበቁ ተጫዋቾች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን ውስጥ በዘንድሮው የውድድር ዘመን የሚገቡ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለመምረጥ በቅድሚያ በቅሎ ቤት በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ጽ/ቤት ለሦስት ተከታታይ ቀናት የተጨዋቾች ምዝገባ እንዲካሄደ ተደርጓል፡፡ በወጣው ማስታወቂያም መሠረት በርካታ ወጣት ተጫዋቾች ከአዲስ አበባ እና እንዲሁም ከተለያዩ ክልሎች የተመዘገቡበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ለምርጫ የተመዘገቡት ተጫዋቾች በርካታ ቁጥር ያላቸው በመሆኑ በሦስት የተለያዩ ቀናት በመከፋፈል ቦሌ መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ የልምምድ ሜዳ ላይ በመገኘት ችሎታቸው እንዲታይ ተደርጓል፡፡

ለተስፋ ቡድኑ መጫወት እንፈልጋለን የሚሉ እድሜያቸው ከ20 አመት በታች ተጨዋቾችአምስት ቀናት የተመዘገቡ ሲሆን ከክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ መታሰቢያ ውድድር የተገኙ ተጨዋቾችን ጨምሮ ከአርብ እለት ጀምሮ ማጣርያ እየተደረገላቸው ሲሆን ማጣሪያውን የሚያልፉት ተጨዋቾችም ተስፋ ቡድኑን የሚቀላቀሉ ይሆናል፡፡ ጎን ለጎንም የቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን የ2008 ዓ.ም ዝግጅቱን ባሳለፍነው ሳምንት የጀመረ ሲሆን ከ17 አመት በታች ታዳጊ ቡድናችን የተገኙ አምስት ታዳጊ ተጨዋቾችን ማሳደግ ችሏል፡፡