Newsletter Signup

Sign-up to stay in touch with Saint George FC

Reagent/Protectorator
Yidnekatchew Tessema
Mengistu Worku

St. George Gallery

News

የቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን የኤሌትሪክ አቻውን ሶስት ለአንድ አሸነፈ • ዛሬ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይጫወታል

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በየአመቱ ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ውስጥ አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ ተስፋ ቡድኖች ውድድር እንደቀጠለ ነው፡፡ ስምንት የተስፋ ቡድኖችን በማሳተፍ ውድድሩን የጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ ተስፋ ቡድኖች ውድድር ቅዱስ ጊዮርጊስ ባሳለፍነው ሳምንት የኤሌትሪክ አቻውን ሶስት ለአንድ በማሸነፍ በውድድሩ ያማረ ጉዞን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ ውድድር ቡድናችን በደደቢት ተሸንፎ የሰውነት ቢሻውን ቡድን 2ለ1 ፤ አዳማ ከተማን 3ለ0 ፤ እንዲሁም ኤሌትሪክን ሶስት ለአንድ በሆነ ውጤት በማሸነፍ በሰበሰበው ዘጠኝ ነጥብ የሶስተኛ ደረጃን ይዞ ይገኛል፡፡የተሰፋ ቡድኖች ውድድሩን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምስት ጨዋታን አድርጎ ባገኘው በ11 ነጥብ በአንደኝነት ሲመራ መከላከያ በ5 ጨዋታ በሰበሰበው 10 ነጥብ በሁለተኝነት ይከተላል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን ከአራት ጨዋታዎች በሰበሰበው ዘጠኝ ነጥብ የሶስተኛ ደረጃን የያዘ ሲሆን ዛሬ በ5 ሰአት በሚካሄደው ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድንን የሚያሸንፍ ከሆነም መሪነቱን የሚረከብ ይሆናል፡፡

የዚህ ውድድር አላማ ወጣቶችን ለዋናው ቡድን ማበርከት እና የጨዋታ ልምድ እንዲያገኙ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ በተለያዩ ዘመናት ከተስፋ ቡድኑ ባሳደጋቸው ተጨዋቾች ብዙ ሲጠቀም ቆይቷል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል ገቢ ማሰባሰቢያ የእግር ጉዞ ዝግጅት ላይ ተጋበዘ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በተዘጋጀው እና መጋቢት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ከ5000 ሰዎች በላይ ሰዎች የሚሳተፉበትን የ5 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ ዝግጅት ላይ ደጋፊዎቹ እንዲሳተፉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡ በዚህም መሰረት በእግር ጉዞው ላይ ለመሳተፍ ለዝግጅቱ የተዘጋጀውን ቲሸርት መግዛት አስፈላጊ መሆኑን ማህበሩ ለግብዣ በላከው ደብዳቤ ላይ አስታውቋል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ህዝባዊ ክለብ እንደመሆኑ መጠን ህዝብ ሲጎዳ ፤ ህዝብ ሲራብ እና ሲጠማ አይዞህ አለሁለህ የሚለው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ነው፡፡ ባለፉት ጊዜያት ክለባችን የተጠሙና የታረዙትን በማብላት እና በማጠጣት፤ የደከሙትን በማንሳት ማህበራዊ ሃላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል፡፡ በተለይም ጧሪ እና ቀባሪ የሌላቸውን አረጋውያንን በመመገብ፤ የኤች አይቪ ኤድስ ህሙማንን ቀርቦ በመጠየቅ እና በመመገብ፤ ተጨዋቾቻችን እና መላው የቡድኑ አባላት በቅዱስ ጴጥሮስ ቲቢ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት በሳንባ በሽታ የተያዙ ህሙማንን በመጠየቅ እና ብሎም በሽታውን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ አጋዥ ለመሆን ሁለቱ ተጨዋቾቻችን ደጉ ደበበ እና አዳነ ግርማ የፀረ ቲቢ አምባሳደሮች በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

በያዝነው 2008 ዓ.ም እያከበርነው የምንገኘው በ80ኛ አመት ክብረ በዓላችንን ምክንያት በማድረግም የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የምንጊዜም ኩራታችን ለሆኑት ለጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የሚውል የመቶ ሺህ ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በቅርቡ የተከበረውን የገናን በዓል በጥሩ ሁኔታ ያከብሩ ዘንድ ጧሪ እና ቀባሪ ለሌላቸው ለ500 አረጋውያን ለበአሉ ማክበሪያ የሚውል ለእያንዳንዳቸው አንድ ዶሮ ከስድስት እንቁላል ጋር በመለገስ በአሉን ተደስተው እንዲያከብሩ ለማድረግ ብር 100000 (አንድ መቶ ሺህ) ለግሷል፡፡

ይህ ክለባችንን ላለፉት 80 አመታት አቅፎ እና ደግፎ ለዚህ ላበቃው ህዝብ ያደረግነው ነገር እጅግ በጣም ውስን መሆኑን እናውቃለን፡፡ በተለይም እግር ኳስ ከጨዋታነት ባለፈ ለሀገር እና ለወገን በማህበራዊውና በኢኮኖሚያዊው ዘርፍ ልዩ አስተዋፅዖ ማድረግ እንዳለበት የሚያምነው ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣይም በድርቅ ለተጎዱት ወገኖች የሚውል የወዳጅነት ጨዋታ ከማዘጋጀት ጀምሮ ሌሎች እርዳታዎችን ለማድረግ እንደሚንቀሳቀስ በዚሁ አጋጣሚ ቃል እንገባለን፡፡

ክቡራን ደጋፊዎችም አላማው ሰብአዊነትን እና የዜግነት ድርሻን የምንወጣበት ነውና ቲሸርቱን በመግዛትና በእግር ጉዞው ላይ በመሳተፍ እንደ ሁልጊዜው የክለባችንን አርማ ከፍ እንድናደርግ በክለባችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ለዋናው የወንዶች ቡድን የሚሰጠው የጨዋታ ማበረታቻ (Incentive) ገንዘብ አሳደገ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ባሳለፍነው ማክሰኞ በክለቡ የተጨዋቾች መኖርያ ካምፕ በመገኘት ለዋናው የወንዶች ቡድን የሚሰጠውን የጨዋታ ማበረታቻ ገንዘብ ማሳደጉን በተጨዋቾች ሽልማት አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ ተናግሯል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የቅዱስ ጊዮርጊስ ሰፖርት ማህበር ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ደንበል ባልቻ፤ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ዋና ፀሃፊ አቶ ንዋይ በየነ፤ እንዲሁም የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ አባል እና የዋናው ወንዶች ቡድን የቡድን መሪ የሆኑት አቶ ታፈሰ በቀለ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አሰኪያጅ አቶ ሰለሞን በቀለ ናቸው፡፡

በዝግጅቱ ላይ የመጀመሪያውን ንግግር ያደረጉት አቶ ታፈሰ በቀለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዚህ በፊት ለተጨዋቾች ይሰጥ የነበረው የጨዋታ ማበረታቻ 700 ብር እንደነበር ገልፀው ከዚያም በኋላ 300 ብር ጭማሪ በማድረግ ለተጨዋቾች የሚሰጠው የጨዋታ ማበረታቻ ገንዘብ ብር 1000 መደረጉን አስታውሰዋል፡፡ የተጨዋቾች ኢንሴንቲቭ 1000 ከተደረገ በኋላ ምንም አይነት ጭማሪ ሳይደረግ ረዘም ያለ ጊዜ መቆየቱን በማስታወስ የስራ አመራር ቦርዱ ተጨዋቾቻችንን የበለጠ ሊያተጋ የሚችለው ኢንሴንቲቭ ምን ያህል ነው ? ተጨዋቾቻችን የክለቡን ባህልና እሴት በሜዳ ላይ ይዘው እንዲቀጥሉ የሚያደርገው ኢንሴንቲቭ ምንያህል ቢሆን ነው የሚሉት ሃሳቦች ላይ በመወያየት ቦርዱ ተጨዋቾችን ያነቃቃል፤ ለበለጠ ድል ያዘጋጃል ያለውን የጨዋታ ማበረታቻ ገንዘብ ከብር 1000 ወደ 1500 ብር ማደጉንና ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወላይታ ዲቻ ከሚያደርጉት ጨዋታ ጀምሮ እንደሚታሰብ ተናግረዋል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ደንበል ባልቻ ከገለፃው በኋላ እንደተናገሩት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሻምፒዮን ሁሌም ሻምፒዮን መሆን የሚፈልግ ክለብ ነው፡፡ ስለዚህም በዘንድሮው አመትም ሻምፒዮን እንድንሆን እንፈልጋለን፡፡ ስለዚህም ሁሉንም ጨዋታ በሜዳዬ እና ከሜዳዬ ውጭ ነው የምጫወተው ብላችሁ ሳትለዩ እኩል ክብደት ሰጥታችሁ እንድትጫወቱ ይህንን የማበረታቻ ሽልማት ጭማሪ አድርገናል፡፡ አመቱ ሲጠናቀቅም ከእናንተ ሻምፒዮንነትን እንጠብቃለን ብለዋል፡፡

የዋናው ቡድን አምበል ደጉ ደበበ በበኩሉ እየተሰራ ማግኘት ማለት ይሄ ነው፡፡ የጨዋታ ማበረታቻ ክፍያው ከፍ መደረጉ የተጨዋቾችን የማሸነፍ መንፈስ የበለጠ ከፍ እንደሚያደርገው ገልጿል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ለዋናው ቡድን ተጨዋቾች ሽልማት ሰጠ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ የዋናው እግር ኳስ ቡድናችን የ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ በመሆኑ ባሳለፍነው ማክሰኞ በተጨዋቾች መኖርያ በመገኘት ሽልማት አበረከተ፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስራ አመራር ቦርድ አባልና የዋናው ቡድናችን ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ታፈሰ በቀለ ስለ ሽልማት አሰጣጥ ሂደቱ ሲገልጹ ሽልማት አሰጣጡ ከዚህ አመት በፊት ሲሰጥ እንደነበረው በአመቱ ውስጥ ቡድናችን ከሚያካሂደው የሊግ ጨዋታ ውስጥ አባዛኛውን የተጫወተ ተጨዋች ከፍተኛውን ሽልማት ያገኝ እንደነበር ገልፀው የዘንድሮው አመት ሽልማትም በዚሁ ሁኔታ እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሰረትም የአመቱን ከፍተኛ ቁጥር ያላውን ጨዋታ የተጫወቱት ተጨዋቾች ብር 50000 በሽልማት መልክ ያገኙ ሲሆን በዘንድሮው አመት ጥቂት ጨዋታዎችን የተጫወቱ ተጨዋቾች የ20 ሺህ ብር ሽልማት እንዳገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ማክሮን ከተሰኘው የትጥቅ አምራች ኩባንያ ጋር በፈጠረው ስምምነት መሰረት አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የተጨዋቾች ማልያ አሰራ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ከመጪው የካቲት ወር ጀምሮ ሀገራችን ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ላይ ይሳተፋል፡፡ ይህንን ውድድር በስኬት ለመወጣት ይቻል ዘንድም ስፖርት ማህበራችን የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ዝግጅቶች ውስጥም አንዱ ተጨዋቾቻችን በውድድር ወቅት የሚለብሱትን ማልያ በአለም ደረጃ ታዋቂ የትጥቅ አምራች ከሆነው ማክሮን ኩባንያ ጋር በመነጋገርና ከፍተኛ ክፍያ በመፈፀም በማሰራት ማልያው በአሁን ሰአት ሀገራችን እንዲገባ አድርጓል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዚህ ትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር ለመስራት ያበቃው በተለይም በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በወጣው ደረጃ መሰረት በአፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ ኤሊት ክለቦች አንዱ በማለት ክለባችንን ስለሰየመው ነው፡፡

ማክሮን ክሪስፓሌኖ በምትባለዋ የጣልያኗ ቦሎኛ ግዛት የሚገኝ ኩባንያ ሲሆን በአውሮፓ ከሚገኙት የትጥቅ አምራች ኩባንያዎች በመሪነት ተርታ የሚመደብ ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው የተለያዩ የስፖርት ትጥቆችን ለአለም ክለቦች እና ብሄራዊ ቡድኖች የሚያመርት ሲሆን በእግር ኳሱ ዘርፍም ለቦሎኛ ክለብ፤ለቻርልተን አትሌቲክ፤ለሚል ዎል፤ለላዚዮ፤ ለናፖሊ፤ለሪያል ቤቲስ፤ለአስቶን ቪላ፤ክሪስታል ፓላስ፤ሼፊልድ ዩናትድ፤ ቦልተን ዎንደረርስ፤1860 ሙኒክ፤ለዛማሌክ ክለብ የስፖርት ትጥቆችን ማቅረብ የቻለ ታላቅ ድርጅት ነው፡፡

ክለባችን ይህንን ዘመናዊ ትጥቅ ከፍተኛ ክፍያን በመክፈል ያስመጣው ተጨዋቾቻችን በተለያዩ የአየር ፀባዮች እንዲጫወቱ ለማስቻል ሲሆን መለያው እንደ አየር ጸባዩ መለበስ የሚችል ነው፡፡

የክለባችን ተጨዋቾችም በመጪው እሁድ በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ከሲሺየልሱ ቅዱስ ሚካኤል ቡድን ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ማልያውን ለብሰው የሚገቡ ይሆናል፡፡

በማክሮን እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አርማ የተሰሩ ሌሎች የተጨዋቾች መጠቀሚያ እቃዎችም በመጪዎቹ ሳምንታት እንደሚገቡ ታውቋል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን ኢትዮጵያ ቡናን ሲያሸንፍ ነገ ከደደቢት ይጫወታል

የ2008 ዓ.ም የታዳጊ እና የተስፋ ቡድኖች ውድድር እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እድሜእቸው ከአስራ ሰባት አመት በታች የታዳጊ ቡደኖች ውድድርን ሲያካሂድ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እድሜቸው ከሃያ አመት በታች የተስፋ ቡድናችን ውድድሮች ያካሂዳል፡ የታዳጊዎችን ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲሁም የተስፋ ቡድኖች ውድድር ደግሞ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ እስካሁንም የታዳጊ እና የተስፋ ቡድኖች በወጣላቸው የጨዋታ ፕሮግራም መሠረት እኩል የአራት ሳምንት ጨዋታቸውን ተጫውተዋል፡፡ በታዳጊዎች ውድድር ላይ ደግሞ የክልል ተካፋይ ክለቦች ይገኙበታል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን እስካሁን ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ከሐረር ሲቲ ዜሮ ለዜሮ ኢትዮ አካዳሚን ሦስት ለዜሮ ሲያሽንፍ በኢትዮ ንግድ ባንክ አንድ ለዜሮ ተሸንፎ በአራተኛው ሳምንት የቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን የኢትዮ ቡና ታዳጊ ቡድንን ሁለት ለአንድ አሸንፍል፡፡ በአስልጣኝ ደረጀ ተስፋዬ (አንገቴ) የሚሰለጥነው ታዳጊ ቡድናችን እስካሁን ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች በተጋጣሚው ላይ አምስት ግብ አስቆጥሮ ሁለት ግብ ተቆጥሮበት ሰባት ነጥብ አስመዝግቧል፡፡ በአሰልጣኝ አሳምነው ገ/ወልድ የሚሰለጥነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን ደግሞ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች በደደቢት ሁለት ለዜሮ ተሸንፎ አዳማ ከተማ ሦስት ለሁለት የሰውነት ቢሻው ቤተሰቦች ቡድንን ሁለት ለአንድ በማሸነፍ ባለፈው እሁድ ከኤሌትሪክ ባደረገው ጨዋታ ሦስት ለአንድ በማሸነፍ በተጋጣሚው ላይ ስምንት ግብ ሲያስቆጥር ስድስት ግብ ተቆጥሮበት ዘጠኝ ነጥብ ላይ ስምንት ግብ ሲያስቆጥር ስድስት ግብ ተቆጥሮበት ዘጠኝ ነጥብ ላይ ተቀምጧል፡፡ ይህ ውጤት ደግሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን ነገ በአስራ አንድ ሰዓት ከደደቢት ታዳጊ ቡድን በአዲስ አበባ ስታዲየም የአምስተኛ ስምንት ጨዋታውን ያካሂድ ይሆናል በአሰልጣኝ አሳምነው ገ/ወልድ የሚሰለጥነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን የአምስተኛ ሳምንት ጨዋታውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም           ጨዋታውን ያካሂዳል፡፡

በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሲሸልሱ ቅዱስ ሚካኤል ይጫወታል

ኢትዮጵያን በመወከል በ2016ቱ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ የሚሳተፈው ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጪው ሳምንት መጨረሻ እሁድ የካቲት 6 ቀን 2008 ዓ.ም ከሲሸየልሱ ቅዱስ ሚካኤል ክለብ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዚህ አህጉራዊ ውድድር ሀገራችን መወከል የቻለው የ2007 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ሻምፒዮን በመሆኑ ነው፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በቅዱስ ሚካኤል ቡድኖች መካከል የሚካሄደው ጨዋታ ቀደም ተብሎ ለሀዋሳ ከተማ በተሰራው አዲሱ የሀዋሳ ስታዲየም ለማካሄድ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ከጥር 25 በፊት ተቀባይ ቡድኖች ለእንግዳው ቡድን የሚጫወትበትን ሜዳ እና ከተማ ማሳወቅ አለበት በሚለው ህግ መሰረት የሀዋሳን ስታዲየም የጎብኙት ኮሚሽነር ለዚህ ቀን መድረስ ባለመቻላቸው ጨዋታው አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ እንዲሆን ተወስኗል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቅዱስ ሚካኤል የሚያደርገውን ጨዋታ የሚመሩት ዳኞች እና የመሰመር ዳኞች ከሶማልያ ናቸው፡፡ ሀሰን መሀመድ ሀጂ ዋና ዳኛ፣ በሺር አብዶ ሱሌይማን እና ሳላህ ኦማር አቡካር ረዳት ዳኞች ሲሆኙ ተጠባባቂ ዳኛ በሺር ኦላድ በመሆን ተመርጠዋል፡፡ ይህንን የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣርያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ደቡብ ሱዳናዊው ማርኮ አብርሃም ላዶ በኮሚሽነርነት የሚመሩት ይሆናል፡፡

ሀሰን ሞሀመድ ሀጂ (የእለቱ ዋና ዳኛ)

በሙሉ የመዝገብ ስማቸው ሀሰን ሞሀመድ ሀጂ ከማል የምታወቁት እና እ.ኤ.አ. በ1988 ሶማልያ ውስጥ የተወለዱት አልቢትር በመጪው ሳምንት የሚካሄደውን የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ሚካኤል ጨዋታ በዋና አልቢትርነት እንዲመሩ በአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ተመድበዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2014 ጀምሮ የፊፋ አለም አቀፍ አልቢትር የሆኑት ሀሰን ሞሀመድ ሀጂ እስከአሁን ድረስ ሰባት ያህል በካፍ እውቅና የሚሰጣቸውን ጨዋታዎች አጫውተዋል፡፡ ከሰባቱ ውስጥም አንዱ እ.ኤ.አ. 2015 ለግሪ ዊልቨስ እና በደደቢት መሀከል የተካሄደውን ጨዋታ መምራታቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያም አዛም ከኤልሜሪክ፣ ያንጋ አፍሪካ ከኮሞሮዛየን ጋር ያደረጓቸውን ጨዋታዎች መምራታቸው ታውቋል፡፡

እኝህ አልቢትር በዋና ዳኝነት በመሩዋቸው ሰባት ጨዋታዎች ውስጥ በአንዱ ብቻ ፍፁም ቅጣት ምት የሰጡ ሲሆን ለባለ ሜዳ ቡድኖች 12 ቢጫ ከሜዳቸው ውጭ ለሚጫወቱ ቡድኖች ደግሞ 11 በአጠቃላይ 23 ቢጫ ካርድ አሳይተዋል፡፡ እስከ አሁን ድረስ ምንም ቀይ ካርድ አልመዘዙም፡፡

ስለአልቢትሩ ቁጥሮች ምን ያሳያሉ

በሜዳው

ከሜዳው ውጪ

አጠቃላይ

ፍጹም ቅጣት ምት

1

0

1

ቀይ

0

0

0

ቢጫ

12

11

23

በሜዳው

ከሜዳው ውጭ

አጠቃላይ

ፍጹም ቅጣት ምት

0.16%

0.00%

0.48%

ቀይ ካርድ

0.00

0.00%

0.00%

ቢጫ ካርድ

1.71%

1.57%

3.29%

አልቢትር ሀሰን ሞሀመድ ሀጂ በሜዳ            አልቢትር ሀሰን ሞሀመድ ሀጂ በሜዳ እና እና ከሜዳ ውጭ የሚሰጧቸው ፍፁም        ከሜዳ ውጭ የሚሰጧቸው ፍፁም ቅጣት ቅጣት ምትና ቀይና ቢጫ ካርዶች                  ምትና ቀይ ካርድ በፕርሰንት                         በቁጥር

በሽር አህመድ ሱሌይማን ( ረዳት አልቢትር)

የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የቅዱስ ሚካኤል የቅድመ ማጣሪያ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታውን በረዳት ዳኝነት የሚመሩት ሱማሊያዊው ረዳት ዳኛ በሽር አህመድ ሱሌይማን ይባላሉ፡፡ እኚህ አልቢትር የፊፋ ኢንተርናሽናል ረዳት አልቢትር የሆኑት እ.ኤ.አ በ2013 ሲሆን ዘጠኝ ዕውቅና ያላቸውን ጨዋታዎች በረዳት ዳኝነት መርተዋል፡፡

ሳላህ አማር አቡካር (ረዳት አልቢትር)

ሶማልያዊው ሳለህ አሜር አቡበካር ኢንተርናሽል የረዳት ዳኛ በመሆን የተሾሙት እ.ኤ.አ በ2001 ነው፡፡ አልቢትሩ በ2001 የኢንተርናሽል ዳኝነታቸውን ያገኙ እንጂ ከሶማሊያ ቀደምት ከሚባሉት ረዳት አልቢትሮች መካከል ይመደባሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ1975 ሶማሊያ ውስጥ የተወለዱት እኚህ አልቢትር በመጪው ሳምንት የሚደረገውን የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የቅዱስ ሚካኤል ጨዋታን በረዳት ዳኝነት የሚመሩ ይሆናል፡፡

ማርኮ አብርሃም ላይ (ኮሚሽነር)

ይህንን ጨዋታ እንዲታዘቡ ከደቡብ ሱዳን የተመደቡት ማርኮ አብርሃም ነዶ ኢትዮጵያን በደንብ ከሚያውቁት ኮሚሽነሮች ተርታ ይመደባሉ፡፡ የቅርብ ጊዜውን እንኳን ብናነሳ ባህር ዳር ላይ የተከናወነውን እና የኬንያ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ በኮሚሽነርነት የመሩት እኝህ ነበሩ፡፡

ቅዱስ ሚካኤል (st.Michel United FC)

ቅዱስ ሚካኤል ክለብ የሲሸየልስ ክለብ ሲሆን የተመሰረተውም እ.ኤ.አ 1996 ነው፡፡ ከተመሰረተ አጭር የሚባል እድሜ ቢሆንም ዲቪዚዮን የሚባለውን የሲሸልስ ሊግ አስራ ሦስት ጊዜ በማንሳት ሀገራቸውን በአፍሪካው ትልቁ የክለባችን ውድድር መወከል ችለዋል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ቡድን ሲሸየልስ ውስጥ በምትገኘው ከአንሴ አውዝ ፒንስ ግዛትን ወክሎ የሚጫወት ሲሆን የመጨረሻ አፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታውንም ባሳለፍነው አመት በፈረንጆቹ የካቲት ወር ላይ አከናውኖ በድምር ውጤት በደቡብ አፍሪካው ማዋሎዳ ሰንዳውንስ አራት ለአንድ ተሸንፎ ከወድድር ውጭ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ስኬቶችን ካነሳን የሲሸየልስ ሊግን 13 ጊዜ፣ የሲሸየልስ ኤፍ ኤ ካፕን 10 ጊዜ፣ ሲሸየልስ ሊግ ካፕ አምስት ጊዜ፣ ሲሸየልስ ፕሮዝዳንትስ ካፕን አስር ጊዜ ማሸነፍ ችሏል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ክለብ ለጨዋታ የሚጠቅመው ስታዴ ሊንቴ ተብሎ የሚጠራውን 10,000 ተመልካች ማስተናገድ የሚችለውን የሲሽየልስ ስታዲየም ይጠቀማል፡፡ ይህ ስተዲየም ባለ አርተፊሻል ሳር ሲሆን ሣሩ የተተከለላትም እ.ኤ.አ በ2007 ነው፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ እና ቅዱስ ሚካኤል ክለብ በወድድር ደረጃ ሲገናኙ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በመጪው እሁድ የካቲት 6/2008 ዓ.ም ሁለቱ ቡድኖች በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲገናኙ ስታዲየሙ በቡርትካናማው የቅዱስ ጊዮርጊስ መለያ ይደምቃል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ዲቻን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ በነገው እለት ከአርባ ምንጭ ከተማ ይጫወታል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከአንድ ወር መቋረጥ በኋላ እንደ አዲስ ተጀምሯል፡፡ ውድድሩ ከመቋረጡ በፊት አንዳንድ ቡድኖች እጅግ በጣም ጥሩ አቋማቸውን ሲያሳዩ አንዳንዶቹ ደግሞ ነጥብ ማግኘት አቅቷቸው ሲዋዥቁ ተስተውሏል፡፡ ፕሪምየር ሊጉ ሩዋንዳ ላይ በተዘጋጀው የቻን አፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ለአንድ ወር ሲቋረጥም በተለይም አቋማቸውን ማስተካከል ለሚፈልጉት ክለቦች ያልታሰበ ሲሳይ ሲሆን በአቋማቸው ጥሩ ለነበሩት ቡድኖች ግን ዱብ እዳ ሆኖባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክለቦች ከዚህ ቀን እስከ እዚህ ቀን የመጀመሪያውን ዙር ጨዋታ ያከናውናሉ ብሎ መርሀ ግብር ለተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ከበተነ በኋላ የጨዋታ ቀን እና ሰአትን መቀያየሩ ልማድ ሆኗል፡፡ በ2008 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን እንኳን ቡድኖች የስምንት ሳምንት መርሀ ግብራቸውን ሳያከናውኑ በተለያዩ ወቅቶች በድምሩ ለ75 ቀናት ያህል ተቋርጧል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ሰባተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ድረስ በሰባት ጨዋታዎች በሰበሰባቸው 16 ነጥቦች አዳማ ከተማን በመከተል የሁለተኛ ደረጃን ይዞ ቆይቷል፡፡በስምንተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የካቲት 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ወላይታ ዲቻን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስት ለዜሮ በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ቢረከብም በማግስቱ በሜዳው ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው አዳማ ከተማ አንድ አቻ በመለያየቱ ወደ ሊጉ መሪነት መመለስ ችሏል፡፡  

አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ በተደረገው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የወላይታ ዲቻ ጨዋታ ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል ሮበርት ኦዶንካራ፤ አንዳርጋቸው ይላቅ፤ መሀሪ መና፤አይዛክ ኢሴንዴ፤ዘካርያስ ቱጂ ፤ ምንተስኖት አዳነ፤አሉላ ግርማ፤ አዳነ ግርማ፤አቡበከር ሳኒ፤ራምኬል ሎክ እና ብራየን ኡሞኒ በአራት ሶስት ሶስት የጨዋታ አሰላለፍ ጨዋታውን መጀመር ችለዋል፡፡

ቡድናችን በጨዋታው የግብ እድሎችን በመፍጠር፤ የተሳኩ ሙከራዎችን በማድረግ እና የባላጋራ ቡድንን የግብ ክልል በተደጋጋሚ በማስጨነቁ በኩል የተሻለ ነበር፡፡ በተለይም በጨዋታው የቡድናችን ዋንኛ የማጥቃት መንገድ መጀመሪያ የሆኑት አቡበከር ሳኒ እና ራምኬል ሎክ ኳስን ወደ ተጋጣሚ ግብ ክልል ይዘው የሚገቡበት መንገድ እጅግ አደገኛ እንደነበር በግልፅና በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡ በአስረኛው ደቂቃ ራምኬል ከግራ መስመር ሰብሮ ወደ ወላይታ ድቻ ግብ ክልል በመግባት ለአዳነ ግርማ ያሻማውና አዳነ ሳይደርስበት የቀረው፤በ27ኛው ደቂቃ ዘካርያስ ቱጂ እና ራምኬል ሎክ አንድ ሁለት ተቀባብለው ለብራየን ኡሞኒ ያቀበሉት እና ብራያን በጭንቅላት መትቶ የወጣበት፤በ36ኛው ደቂቃ ብራየን ከአቡበከር ሳኒ ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ያገኘውንና አንድ ተከላካይ እና የወላይታ ድቻን ግብ ጠባቂ በማለፍ ወደ ግብ መቶ አስቆጠረ ሲባል በተከላካይ ከመስመር የተመለሰው ኳስ ቡድናችን በሁለቱ የመስመር አጥቂዎች ሲጠቀም እንደነበር ማሳያዎች ቢሆኑም ጨዋታው ግብ ማስተናገድ የቻለው በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ነበር፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በወላይታ ዲቻ ጨዋታ የሁለተኛው ግማሽ የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አሰልጣኝ ማርት ኖይ ዘካርያስ ቱጂን አስወጥተው ተስፋዬ አለባቸውን በማስገባት የአሰላለፍ ለውጥ ሲያደርጉ ተጨዋችን በተጨዋች በመለዋወጥ ግብን መፈለግ ጀመሩ፡፡ ማርት ኖይ የተስፋዬ አለባቸውን መግባት ተከትሎ በመሀል አማካይነት ተሰልፎ የቆየው አሉላ ግርማ ወደ ቀድሞ የቀኝ መስመር ተከላካይነት ሚናው እንዲመለስ በተከላካይ አማካይነት ሲሰለፍ የቆየው ምንተስኖት አዳነም ወደ አጥቂዎቹ በመጠጋት እንዲጫወትና ተስፋዬ አለባቸውም በለመደው ሚና ከአራቱ ተከላካዮች ፊት በመቆም ሽፋን እንዲሰጥ አደረጉ፡፡

በለውጡ የማርት ኖዩ ቅዱስ ጊዮርጊስ በተለይም በሁለተኛው ግማሽ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ብልጫን ወሰደ፡፡ በዕለቱ ጨዋታ እጅግ ድንቅ እንቅስቃሴን ሲያደርግ የቆየው ታዳጊው ተጨዋቻችን አቡበከር ሳኒ በወላይታ ዲቻ የግብ በር ግራ መስመር ላይ ያገኛትን ኳስ ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ይዞ ከገባ በኋላ በተሰራበት ጥፋት የተሰጠውን ፍጹም ቅጣት ምት አዳነ ግርማ መትቶ በቀላሉ በማስቆጠር ግብ ጠምቶት የነበረውን ጨዋታ አራሰው፡፡

በግቡ የተነሳሱት የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች በወላይታ ዲቻ ቡድን ላይ ተደጋጋሚ የግብ ሙከራን ማድረግ ቀጠሉ፡፡ በጨዋታው 57ኛው ደቂቃ ላይ አሉላ ግርማ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ተከላካዩ አይዛክ ኢሴንዴ አግኝቶ በጭንቅላት ቢሞክራትም ኳስና መረብን ሳይገናኙ ቀሩ፡፡ ተስፋ ያልቆረጡት የቡድናችን ተጨዋቾች ኳስን በሚገባ በመመስረት ኳስ መሀል ሜዳ ላይ ተስፋዬ አለባቸው ጋር ደርሳለች፤ ተስፋዬ ወደ ግራ ጥላ ፎቅ አድልቶ በሁለት የወላይታ ዲቻ ተጨዋቾች ተይዞ ለሚገኘው አዳነ ግርማ ሰጠው፡፡ አዳነም በሚገርም ሁኔታ ከሁለቱ ተጨዋቾች መሀል ዞሮ ከወጣ በኋላ ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውጭ በግራ እግሩ አክርሮ በመምታት ለራሱም ለክለቡም ሁለተኛውን ግብ አስቆጠረ፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ የአመቱ ምርጥ ግብ የሚመረጥ ቢሆን ቀደም ሲል የቡድናችን ተጨዋቾች የሆኑት አሉላ ግርማ እና በሀይሉ አሰፋ ካስቆጠሩት ግብ ጋር ይህች ግብ ለውድድር ትቀርብ ነበር፡፡

የግቡን መቆጠር ተከትሎ ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ማርት ኖይ ሌላ ግብ ፍለጋ በሚመስል መልኩ ራምኬልን በ74ኛው ደቂቃ አስወጥተው ናትናኤል ዘለቀን ሲያስገቡ የጨዋታው ኮከብ የነበረው አቡበከር ሳኒም በዳዋ ሁጤሳ ተቀይሮ ወጥቷል፡፡ ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 2ለ0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ ተብሎ የአልቢትሩ ፊሽካ በሚጠበቅበት ሰአትም ብራየን ኡሞኒ ከአሉላ ግርማ የተሻማለትንና በአዳነ ግርማ የተዘጋጀለትን ኳስ በመጠቀም አንድ ግብ አክሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ዲቻን ሶስት ለዜሮ እንዲያሸንፍ አድረገ፡፡

በጨዋታው በዛ ያሉ ጥሩ የሚባሉ ክስተቶች ተከስተዋል፡፡ በተለይም በዚህ ጨዋታ በቡድናችን በተለያየ ጊዜያት በሲ እና በቢ ቡድን ውስጥ አልፈው ዋናው ቡድናችን ውስጥ በመጫወት ላይ ከሚገኙት ተጨዋቾቻችን መሀከል ስድስቱን( አንዳርጋቸው ይላቅ፤ ዘካርያስ ቱጂ፤ አሉላ ግርማ፤ ምንተስኖት አዳነ፤ ናትናኤል ዘለቀ እና አቡበከር ሳኒ) አሰልጣኙ ማሰለፋቸው በወጣቶች ላይ ያላቸውን እምነት ያሳያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ከሚያውቁት ቦታ ተቀይረው እየተጫወቱ ካሉት ተጫዎቾች ውስጥ በተለይም መሀሪ መና የወዳጅነት ጨዋታዎችን ጨምሮ በሊጉ ጨዋታ ላይ ያሳየው ብቃት አሰልጣኙ በተከላካይ ስፍራ አማራጭ እንዲኖራቸው ማድረግ ችሏል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በየ አመቱ ቢያንስ አንድ አዲስ ታዳጊ ለሊጉ በማበርከት ይታወቃል፡፡ ልምዱም አድርጎታል፡፡ ካሳለፍነው አመት እንኳን ብንጀምር ዘካርያስ ቱጂን ያስተዋወቀው ቅዱስ ጊዪርጊስ በዘንድሮው አመት ደግሞ አይደክሜውን አቡበከር ሳኒን ለሊጉ አበርክቷል፡፡ ዘካርያስ ወደ ዋናው ቡድን በተቀላቀለ የመጀመሪያው አመት ከ20 በላይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ተራው የአቡበከር ሳኒ ይመስላል……. በቀጣዩ አመትስ ?????

በነገው ጨዋታም አሰልጣኝ ማርት ኖይ ባሳለፍነው ሳምንት የነበረው ጨዋታ ላይ የተጠቀሟቸውን ተጨዋቾች በተወሰነ መልኩ እንደሚቀይሩ ፍንጭ የሰጡ ሲሆን በአብዛኛው ግን ያንኑ አሰላለፍ ሊከተሉ እንደሚችሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ጨዋታው በነገው እለት ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ላይ አርባ ምንጭ ከተማ ላይ የሚካሄድ ሲሆን የፌስ ቡክ አድራሻ ያላችሁ ደጋፊዎችም ጨዋታውን St George በሚለው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ኦፊሻል የፌስ ቡክ አካውንት ላይ መከታተል ትችላላችሁ፡፡