Newsletter Signup

Sign-up to stay in touch with Saint George FC

Reagent/Protectorator
Yidnekatchew Tessema
Mengistu Worku

St. George Gallery

ከአዲስ አበባ እስከ ባህር ዳር - ታንጎ ከካዛንችስ

ቀኑ ቅዳሜ መጋቢት 3 ቀን 2008 ዓ/ም ንጋት ላይ ቦታው መስቀል አደባባይ ሲሆን ከንጋቱ 10፡30 ሲል ከስፍራው ደረስኩኝ፡፡ መስቀል አደባባይ በዛ ሰአት ለጉዞ የተዘጋጁ በርካታ ቁጥር ያላቸው አውቶብሶች በረድፍ ቆመዋል፣ እነዚህ በረድፍ የቆሙት አገር አቋራጭ አውቶብሶች የሚጠብቁት እንደዚህ ቀደሙ የተለያዩ መንገደኞችን ጭኖ ወደ ተለያዩ ስፍራዎች ለማድረስ ሳይሆን ቢጫና ቀይ ቡርቱካናማ መለያ የለበሱትን የሳንጆርጅ ልጆችን ወደ ሁለተኛ ቤታቸው ባህር ዳር ለመውሰድ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ላይ ቅ/ጊዮርጊስ ከቲፒ ማዜምቤ ጋር በባህር ዳር ግዙፍ ስታዲየም የሚያደርጉትን ጨዋታ ለመታደም ነው፡፡

ደጋፊው ከተነገረው የጉዞ መነሻ ሰአት ቀደም ብሎ ከ11 ጀምሮ መስቀል አደባባይ መሰባሰብ ጀምሯል፣ መስቀል አደባባይ በዛ ሰአት ከአውቶብሶቹና ከተጓዦቹ ግርግር ሌላ ዘወትር ጠዋት ስፖርት በሚሰሩ ወጣቶች፣ ጎልማሶችና አዛውንቶች ትደምቃለች፡፡ ለጉዞ የተዘጋጁት የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ግማሹ ቡቡዜላን ይነፋል፣ ሌላው ይዘምራል፣ ገሚሱ የተቀጣጠሩ ጓደኛሞች ጋር በስልክ ይፈላለጋሉ፣ ሌላም ሌላም እኔና ጓደኞቼ ቀደም ብለን ቲኬት የቆረጥነው የሰላም ባስ ሊነሳ በመሆኑ ወደ አውቶብሳችን ገባን፡፡ ጉዟችንን ከመጀመራችን በፊት በሰልፍ የተደረደሩትን የፈረሰኞቹ አውቶቢሶች በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማና በክለቡ አርማ ደምቀዋል፣ የደጋፊው ውበት፣ ፍቅርና አንድነት በአእክምሮዬ እየመጡብኝ ሳልወድ በግድ ወደ ሰላም ባስ ገባሁኝ፡፡ የተሳፈርኩበት የሰላም ባስ 11፡30 ሲል ጡሩምባውን በረዥሙ እየለቀቀ ከመስቀል አደባባይ ወደ አራት ኪሎ እሽክርክሪቱን ጀመረ በቃ ከአዲስ አበባ ባህርዳር የ532 ኪሎ ሜትር ጉዞ በዚህ የጎማ ሽክርክሪት ተጀመረ አራት ኪሎን አቋርጠን በሀገር ፍቅር በኩል ሽቅብ በጊዮርጊስ ቤት ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ ሰሜን ማዘጋጃ አቀናን፣ የጉዞ ማስታወሻነቱ አ/አበባን ለማስቃኘት እንዳልሆነ ትረዱልኛላችሁ የሚል ዕምነት አለኝ፡፡

ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በምቹ ወንበሮቹ ተሳፋሪውን ሸክፎ ግስጋሴውን በመቀጠል ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ አ/አበባን ለቆ የአዲስ አበባ ጫፍ ላይ ሱሉልታ ደረሰ በኋላም የአዲሰ አበባን ከተማ ሙሉ ለሙሉ ለቆ ለመውጣት 33 ደቂቃ ወስዶበታል ማለት ነው ደብረሊባኖስን አለፍ ብለን ሰውነታችንን ለማፍታታት ለ5 ደቂቃ ከተሳፈርንበት አውቶብስ ወረድን፣ በአውቶብሱ ውስጥ ካለነው ተሳፋሪዎች መካከል 75% የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች መሆናቸው በለበሱት መለያና አንገታቸው ላይ የጠመጠሙት እስካርብ ያሳብቅባቸዋል፣ የሰላም ባስ በጊዜ ግባ የተባለ ይመስል ፍጥነቱን ጨምሮ የገጠሯ ማንነትና የከተሜነት ባህሪ በጥምረት የሚታይባቸውን ከተሞች አልፈን ልክ 5 ሰአት ሲሆን ለምሳ አውቶቢሱ ቆመ ረዳቱ የተፈቀደልን 30 ደቂቃ ብቻ መሆኑን ነግሮን ለምሳ ደብረማርቆስ ወረድን፡፡ ለሰላሳ ደቂቃ የተፈቀደው የምሳ ፕሮግራሙ 15 ደቂቃ ተጨምሮበት 5፡45 ላይ ክፍል ሁለት ጉዟችንን ቀጥለናል ብዙ ተጉዘን በ9፡15 ውቢቷ ባህርዳር ከተማ ደረስን፡፡ ውቢቷ ባህር ዳር ከተማ ቀደም ብለው በተለያዩ የመገናኛ ትራንስፖርት በሄዱና ለዚሁ ለቅ/ጊዮርጊስ እና ቲፒ ማዜምቤ ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት በሄዱ የክለባችን ደጋፊዎችና አመራሮች በተሰራው ቅስቀሳ ባህርዳር አንድ ልጇን ቅ/ጊዮርጊስን ለመሞሸር ሽር ጉድ ላይ እንዳለች የከተማው ድባብ አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡

ሊነጋጋ ሲል መስቀል አደባባይ ጥያቸው የመጣሁት እነዛ 26 አውቶብሶች የፈረሰኞቹን ደጋፊዎች በጉያቸው ሸክፈው 11 ሰአት ሲል የባህርዳር ከተማ መግቢያ ላይ መድረሳቸውን በመስማቴ ወደ ስፍራው አመራሁ በስፍራው ስደርስ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ብርቅዬ የሆኑትን የሀገራችን እግር ኳስ እድገት ናፋቂ ለክለባቸው ቅ/ጊዮርጊስ ሟች የሆኑ ደጋፊዎችን ለመቀበል ቃላት ከሚገልፀው በላይ ተዘጋጅተዋል፣ የግል የመንግስት ለንግድ የስራ በርካታ ቁጥር ያላቸው የተለያዩ መኪናዎችና ባጃጆች የፈረሰኞችን ደጋፊዎች ለመቀበልና ለማጀብ ተደርድረዋል ጡሩምባው ያለሟቋረጥ ይነፋል፣ የመኪናም ክላክሱ ይጮሃል፣ ቡርቱካናማውና ቀዩ የሳንጆርጅ አርማ ይውለበለባል፣ ደጋፊው በመጣበት አውቶብሶች በመስኮትና በአውቶብሱ አናት ላይ ወጥተው አርማውን ከፍ አድርገው ያውለበልባሉ፣ በፍቅር ይጮሃሉ፣ ያዜማሉ፣ ይህ ሁሉ የሚያደርጉት በፍቅሩ ለተሸነፉለት ክለባቸው ቅ/ጊዮርጊስ ነው ዋው ምንኛ መታደል ነው የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊ መሆን፣ በእውነት ስለእውነት ነው የምላቸሁ ያኮራል የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊ የሁልጊዜም ኩራቴ ነው፡፡

የባህርዳር እና የአካባቢዋ ነዋሪ በመንገዱ ግራና ቀኝ በመሆን ለአቀባበሉ ልዩ ድምቀት በሰጡት ነዋሪው እጁን እያውለበለበ በሶስት አይን እየተመለከተ ለነዚህ ብርቅዬ ደጋፊዎች አይዟችሁ ታሸንፋላችሁ! ሳንጆርጅ ጊዮርጊስ እያለ ተስፋ ሲሰጣቸው በአጠፋው የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊ ለባህር ዳር ከተማ ልዩ ድባብን ፈጠሩ፡፡

መጋቢት 4 ቀን 2008 ዓ/ም እሁድ የባህርዳር ከተማ ሽርጉዷን ቀጥላለች የተቀበለቻቸውን የፈረሰኞቹ እንግዶች ከወዲያ ወዲህ ከታች እላይ የሚያመላልሱ ባጃጆች የቅ/ጊዮርጊስ አርማና ክለባችን በ2007 ሻምፒዮን ሲሆን ያሳተመውን ሙሉ የክለቡ ተጫዋቾች ያሉበትን ፖስተር ለጥፈው ይሯሯጣሉ ከተማው በቅ/ጊዮርጊስ መዝሙር በክለቡ አርማዎች እና ቢጫና ቡርቱካናማ መለያ በሙሉ የፈረሰኞቹ ጦር ከላይ እስከታች ደምቃለች ከቀኑ ስድስት ሰአት ሲሆን ግዙፉ የባህርዳር ስታዲየም ተከፍቶ ቲኬት መሸጥ ተጀመረ፡፡

ከአዲስ አበባ ባህርዳር የከተሙት የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎችና የስፖርት ቤተሰቡ ወደ ግዙፍ የባህርዳር ስታዲየም ይተማል ሁሉም ላይ የደስታ ስሜት ይነበባል ለጨዋታው መግቢያ የተዘጋጀውን ትኬት እየቆረጠ ወደ ውስጥ ይገባል፣ ስታዲየሙ በእነዛ በሚያማምሩ የክለቡ መለያዎችና አርማዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ 9፡15 ሲል ከዳር እስከ ዳር በደጋፊው ተሞላ በግዙፉ የባህር ዳር ስታዲየም የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ ለመታደም የታደሉት የስፖርት ቤተሰቦች በሙሉ ውበት ተላብሰውና ፈክተው ቅ/ጊዮርጊስን መስለው የተስፋ ብርሃን ነፀብራቅ እየረጩ በሚመስጥ ዜማ በስታዲየም ውስጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያሰማሉ፡፡ ሳንጆርጅ! ቅ/ጊዮርጊስ! እያሉ፡፡

ካስትሮ በሚያምረው ድምፁ የተለያዩ ጡዑም ዜማዎችን ያጫውታል፣ አቸኖ አረንጓዴ እግረ ጠባቡን ሱሪ ለብሶ ቢጫ መለያውን አጥልቆ በአርብኝነት ስሜት በስታዲየሙ ውስጥ እየተዟዟረ ደጋፊውን ያንቀሳቅሳል የአማራ ክልል ፖሊስ ማርሽ ባንድ የተለያዩ ዜማዎችን እያሰማ ለደጋፊው ተጨማሪ መነቃቃትን ፈጥሯል፡፡ ያ በሁሉም ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የዳዊትና ጎሊያድ ፍልሚያ 10 ሰአት ሲል ተጀመረ፡፡ ጨዋታው በተጀመረ በ11ኛው ደቂቃ በሀይሉ ቱሳ በታምረኛው እግሩ ከድንቅም ድንቅ የሆነ ምርጥ ኢንተርናሽናል ጎል አገባ ስታዲየሙ ከዳር እስከ ዳር በጩኸትና ፉጨት ደመቀ ጨዋታው ቀጥሏል፣ የመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በተጨማሪም ሁለት ደቂቃ ማብቂያ ላይ ቲፒዎች ባልተጠበቀ ሁኔታ ከጥንቃቄ ጉድለት ጎል አግብተው ለዕረፍት ወጡ ከዕረፍት መልስ አንድ ደጋፊ ወደ ሜዳ ገብቶ የቲፒ ማዜምቤ የግብ ክልል ውስጥ ገብቶ ተንበርክኮ ፀለየ ደጋፊው የእነሱ ነው አይደለም በሚል መላምቶችን ወረወረ የገባው ደጋፊ ወጥቶ ሁለተኛው አርባ አምስት ተጀመረ የደጋፊው ሀሳብ የነበረው ወደ ሜዳ በገባው ወጣት ላይ በነበረበት ሰአት በድጋሚ በራሳችን ስህተት ሁለተኛ ጎል ተቆጠረብን ደጋፊው ግን ቅ/ጊዮርጊስ ያገባ እስከሚመስል ባለ በሌለ ሀይሉ ለቡድናችን ደጋፉን መስጠት ቀጥሏል፡፡ በዚህ ጊዜ ቅ/ጊዮርጊሶች ልዩ ጫና ፈጥረው መጫወታቸውን ቀጥለዋል፡፡

“ያ” የወቅቱ የአፍሪካ ሻምፒዮን አሸናፊ የሆነ ቡድን ከላይ እታች በአጭር ኳስ የሚይዘውን አሳጡት በቅድሚያ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት የነበረው የማይሸነፍ የሚመስለው ቲፒ ማዜምቤ ለፈረሰኞቹ እጅ ሰጠ ድጋፍ ከዳር እስከዳር ቀጥሏል 57ኛ ደቂቃ በቲፒ ማዘምቤ ጎል አካባቢ የተሰጠውን የቅጣት ምት በእነዛ ቀጫጭን የበሀይሉ ቱሳ እግር ወደ ጎል ተመታ አዳነ ደገፍ እርጎ ወደ ጎል ቀየረው፡፡ ያ ግዙፍ ስታዲየም በጪኸት ተናጋ ፈረሰኞቹ የማይሸነፍ የሚመስለውን ቲፒ ማዘምቤን ለማሸነፍ በሙሉ አቅማቸው ያጠቃሉ፣ በደቂቃዎች ልዩነት አንድ ሁለት ተቀባብለው በሀይሉና በረኛ ተገናኝተው አገባ ተብሎ ሲጠበቅ በረኛው አዳነው ጨዋታው 2 ለ 2 ተጠናቀቀ ዳዊት ጎልያድን በማይታመን መንገድ ፈተነው ቲፒ ማዜምቤዎች ውጤቱ ያልጠበቁትና መራራ ሆነባቸው፣ በምትኩ ፈረሰኞቹ ባስመዘገቡት ውጤት መላው የስፖርት ቤተሰብ ተደሰተ ፈረሰኞቹን ብሎ የተመመው ደጋፊ በጨዋታው ያሸነፉ ያህል ተደሰቱ በዕርግጥም የዕለቱ ውጤት ያስደስታል ብዙ የተባለለት ብዙ የተዘፈነለት የተወራለት ቲፒ ማዘምቤ በተግባር የፈተኑት ፈረሰኞቹ ኩራት ይገባቸዋል፣ እኛም ደጋፊዎቹ ጥረታቸውን አድን ቀን ጨዋታችሁን በልባችን ፅፈነዋል፡፡

እናንተ በቅ/ጊዮርጊስ ፍቅር ተሸንፋችሁ ቅ/ጊዮርጊስን ብላችሁ ከሞቀ ቤታችሁ ወጥታችሁ፣ ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ፣ ስራችሁን ዘግታችሁ፣ ባህርዳር በመትመም ላሳያችሁት ቅንነት፣ መልካምነት እና ፍፁም ጨዋነት ለተሞላበት የመተሳሰብ ስሜት ዘር ሀይማኖት ሳይጋርዳችሁ እድሜ ሳይበግራችሁ፣ ለከፈላችሁት መስዋዕትነት ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነውና እግዚአብሄር ያክብራችሁ እውነትም ሳንጆርጆች ከክለብ በላይ መሆናችንን ተግባራችን መስክሯል ምክንያቱም አንገታችንን ቀና አድርገን እንድንጓዝ አድርገውናልና፡፡

መጋቢት 5 ቀን ጉዞ ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ሆነ አሁን እንግዲህ የመጣንበት መንገድ ስለሆነ በየመንገዱ እያተምኩኝ ጊዜያችሁን አልሻማም 11 ሰአት ሲል የተነሳው የሰላም ባስ በከፍተኛ ፍጥነት ተጉዞ 9፡15 ሲል አዲስ አበባ ገባን፣ መስቀል አደባባይ ደርሰን ሀላችንም ወረድን ክብር ለተጨዋቾቻችንና ለደጋፊዎቻችን ይሁንልኝ!! የእኛ አሸናፊዎች ፈረሰኞቹ!!  

ምንግዜም ቅ/ጊዮርጊስ!!