Newsletter Signup

Sign-up to stay in touch with Saint George FC

Reagent/Protectorator
Yidnekatchew Tessema
Mengistu Worku

St. George Gallery

ርዕሰ አንቀጽ ባህር ዳር ላይ ኮርተናል

ሀገራችንን በመወከል በሃያኛው የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ በተሳታፊነት የቀረበው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን የመጀመሪያውን የማጣሪያ ጨዋታ የሲሼልሱን ቅዱስ ሚካኤል በደርሶ መልስ ውጤት አራት ለአንድ በማሸነፍ ወደ ሁለተኛዋ ዙር ለማለፍ በቅቷል፡ ቀጣይ ተጋጣሚው ሆኖ የቀረበው የወቅቱ የአህጉራችን ጠንካራ እና ውጤታማ ከሆነው ከዲሞክራቲ ኮንጐ ክለብ ቲፒ ማዜምቤ ነበር፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚ ቲፒ ማዜምቤ በመሆኑ በሁሉም እግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ የጨዋታው መድረሻ ጊዜ በናፍቆት እንዲጠበቅ አድርጐታል፡፡ ምክንያቱም ደግሞ ይህንኑ ታላቅ ስምና ዝና ያለውን ክለብ በሜዳ ላይ ለመከታተል ነው፡ እርግጥ ነው ቲፒ ማዜምቤ ከአሁጉራችን አፍሪካ በፋይናንስም ሆነ በአደረጃጀቱ አንቱ የሚባል ታላቅ ክለብ ነው፡፡ የቡድኑ ተጫዋቾች የተዋቀሩት ለዲሞክራቲክ ኮንጐ ብሔራዊ በድን የሚጫወቱ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች በፕሮፌሽናልነት በከፍተኛ ወጪ ግዥ በተካሄደባቸው ተጨዋቾች ነው፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የቲፒ ማዜምቤ የመጀመሪያ ጨዋታ ባለፈው እሁድ ባህር ዳር ከተማ በሚገኘው ስታዲየም ላይ ነበር፡፡

የቡድናችን የጀርባ አጥንት የሆኑት ደጋፊዎቻችን የሞራል ድጋፋቸውን ለመስጠት በቁርጠኝነት ተነሳስተው በሃያ ስድስት አውቶብስ ከመዲናችን አዲስ አበባ ተነስተው ባህር ዳር ላይ እስኪከትሙ ድረስ ከልብ በሚያፈቅሩት ክለባቸው ሙሉ እምነት በመጣል በደስታ እና በሆታ እየጨፈሩ ውቢቱ ባህር ዳር ደርሰዋል፡፡ በወቅታዊ ብቃቱ በጠንካራ እና ውጤታማነቱ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም የሆነውን ቲፒ ማዜምቤን ማሸነፍ እንደሚቻል ከጨዋታው በፊት በሚያሳዩት ደስታቸው በአብዛኛው ደጋፊዎቻችን ላይ ይታይ ነበር ቡድናችን ወደ ሜዳ ሲገባም ሆታና ጭፈራ ተቀብለወታል፡፡፡ ጨዋታው እንደተጀመረ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ በአስደናቂ ሁኔታ በጨዋታው ኮከብ በሀይሉ አሰፋ (ቱሳ) ግብ በባህር ዳር ስታዲየም የተገኘውን የእግር አፍቃሪ ህዝብ በደስታና በሆታ አድናቆቱን ገልጿል፡፡ ከጨዋታው ጅማሬ አንስቶ እስከ ማጠናቀቂያው ድረስም በልበ ሙሉነት አንገቱን ቀና አድርጐ የሚያበረታታው ደጋፊያችን ውጤቱ ሁለት ለሁለት ቢጠናቀቅም በፈረሰኞቹ የሜዳ ላይ ብቃት ታሪካዊ ደስታቸውን ለመግለጽ በቅተዋል፡፡ እንደውም የተቆጠሩብን ግቦች በጥቃቅን ስህተት እንጂ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለበ ማሸነፍ ነበረበት በማለት አብዛኞዎቹ በቁጭት ሲናገሩም ተደምጠዋል፡፡ እንደዛም ሆኖ ባህር ዳር ላይ ከልብ በምናፈቅረው ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስኮርተናል፡ በማለት ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡

ሀገራችንን በመወከል በሃያኛው የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ በተሳታፊነት የቀረበው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን የመጀመሪያውን የማጣሪያ ጨዋታ የሲሼልሱን ቅዱስ ሚካኤል በደርሶ መልስ ውጤት አራት ለአንድ በማሸነፍ ወደ ሁለተኛዋ ዙር ለማለፍ በቅቷል፡ ቀጣይ ተጋጣሚው ሆኖ የቀረበው የወቅቱ የአህጉራችን ጠንካራ እና ውጤታማ ከሆነው ከዲሞክራቲ ኮንጐ ክለብ ቲፒ ማዜምቤ ነበር፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚ ቲፒ ማዜምቤ በመሆኑ በሁሉም እግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ የጨዋታው መድረሻ ጊዜ በናፍቆት እንዲጠበቅ አድርጐታል፡፡ ምክንያቱም ደግሞ ይህንኑ ታላቅ ስምና ዝና ያለውን ክለብ በሜዳ ላይ ለመከታተል ነው፡ እርግጥ ነው ቲፒ ማዜምቤ ከአሁጉራችን አፍሪካ በፋይናንስም ሆነ በአደረጃጀቱ አንቱ የሚባል ታላቅ ክለብ ነው፡፡ የቡድኑ ተጫዋቾች የተዋቀሩት ለዲሞክራቲክ ኮንጐ ብሔራዊ በድን የሚጫወቱ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች በፕሮፌሽናልነት በከፍተኛ ወጪ ግዥ በተካሄደባቸው ተጨዋቾች ነው፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የቲፒ ማዜምቤ የመጀመሪያ ጨዋታ ባለፈው እሁድ ባህር ዳር ከተማ በሚገኘው ስታዲየም ላይ ነበር፡፡

የቡድናችን የጀርባ አጥንት የሆኑት ደጋፊዎቻችን የሞራል ድጋፋቸውን ለመስጠት በቁርጠኝነት ተነሳስተው በሃያ ስድስት አውቶብስ ከመዲናችን አዲስ አበባ ተነስተው ባህር ዳር ላይ እስኪከትሙ ድረስ ከልብ በሚያፈቅሩት ክለባቸው ሙሉ እምነት በመጣል በደስታ እና በሆታ እየጨፈሩ ውቢቱ ባህር ዳር ደርሰዋል፡፡ በወቅታዊ ብቃቱ በጠንካራ እና ውጤታማነቱ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም የሆነውን ቲፒ ማዜምቤን ማሸነፍ እንደሚቻል ከጨዋታው በፊት በሚያሳዩት ደስታቸው በአብዛኛው ደጋፊዎቻችን ላይ ይታይ ነበር ቡድናችን ወደ ሜዳ ሲገባም ሆታና ጭፈራ ተቀብለወታል፡፡፡ ጨዋታው እንደተጀመረ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ በአስደናቂ ሁኔታ በጨዋታው ኮከብ በሀይሉ አሰፋ (ቱሳ) ግብ በባህር ዳር ስታዲየም የተገኘውን የእግር አፍቃሪ ህዝብ በደስታና በሆታ አድናቆቱን ገልጿል፡፡ ከጨዋታው ጅማሬ አንስቶ እስከ ማጠናቀቂያው ድረስም በልበ ሙሉነት አንገቱን ቀና አድርጐ የሚያበረታታው ደጋፊያችን ውጤቱ ሁለት ለሁለት ቢጠናቀቅም በፈረሰኞቹ የሜዳ ላይ ብቃት ታሪካዊ ደስታቸውን ለመግለጽ በቅተዋል፡፡ እንደውም የተቆጠሩብን ግቦች በጥቃቅን ስህተት እንጂ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለበ ማሸነፍ ነበረበት በማለት አብዛኞዎቹ በቁጭት ሲናገሩም ተደምጠዋል፡፡ እንደዛም ሆኖ ባህር ዳር ላይ ከልብ በምናፈቅረው ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ ኮርተናል፡ በማለት ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡