Newsletter Signup

Sign-up to stay in touch with Saint George FC

Reagent/Protectorator
Yidnekatchew Tessema
Mengistu Worku

St. George Gallery

ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ

ታዳጊው ወጣት በማደሪያ ቆጡ ለመተኛት ሲዘጋጅ ሁሌም ጸሎቱን ያደርሳል፡፡  እናቱን ለማግኘትና ለማየት ፈጣሪውን መለመኑን አልተወም፡፡ገና በሶስት አመቱ የእናቱን ፍቅር ሳይጠግብ ነው የተለያዩት፡፡አባቱ  በጣሊያን ጦርነት ጊዜ ዘመቱ፡፡ከጦርነቱ እንደተመለሱ አባትና እናቱ ተለያዩ፡፡

           እናቱ ወደ አዲስ አበባ መጥታ ዘመዶቿ ጋር ተቀመጠች፡፡ታዳጊው እድሜው ከፍ ብሎ እራሱን በደምብ ሲያውቅ ትምህርት ቤት መግባት ነበረበት፡፡የእናቱ ታናሽ ወንድም ዲያቆን ነበር፡፡በኋላም ቄስ ሆነ፡፡ ታዳጊው ወጣት እንዳጎቱ ቄስ ሆኖ ቤተክርስቲያንን ለማገልገል ትልቅ ፍላጎት ነበረው፡፡

        እዚያ ለመድረስ በየደረጃ ያለውን የቅስና ትምህርት መውሰድ ነበረበት፡፡እዚያው በገጠር የሚገኝ የቄስ ትምህርት ቤት ገባ ፡፡ትምህርት ቤቱ አዳሪ ነው፡፡ ቆጥ ተሰራለት፡፡ እዚያው እያደረ መማር ጀመረ፡፡ ቤተሰቦቹ በሶና ቆሎ ይልኩለታል፡፡አንዳንዴም ቤተክህነት እየሄደ እየበላ ትምህርቱን ገፋበት፡፡ትንሹ  ወልደመስቀል ኮስትሬ፡፡

                        በቦታው የሚገኙ ብዙዎቹ ተማሪዎች ከተለያየ ቦታ የመጡ ናቸው፡፡አንዳንድ ጊዜ ቤተሰቦቻቸው እየመጡ ይጠይቋቸዋል፡፡ብዙ ጊዜ እናቶቻቸው ነው የሚመጡት፡፡‹‹የእከሌ እናት መጡ›› ሲባል በተማሪው አቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡ የተወሰነ ጊዜም እዚያ ይቆያሉ፡፡

       ሁል ጊዜም ቢሆን የወልደመስቀል  እናት መጥተው አያውቁም፡፡በእናቱ ጉዳይ ቢጠየቅም በማዘን ነበር የሚናገረው፡፡ሁልጊዜም እናቱን ይናፍቃል፡፡‹‹አንድ ቀን መጥታ አገኛታለሁ›› እያለ ተስፋ ያደርጋል፡፡በእናቱ ጉዳይ ልቡ እየደማ የእናትነት ፍቅሩ ብቻ ይዞ መቀመጥ ተገደደ፡፡እናቱ ወደ ገጠር አትመጣም፡፡ እርሱም ወደ እናቱ መሄድ አይችልም ፡፡ማን ያገናኛቸው?

                        አንድ ቀን አዲስ አበባን ጎብኝቶ እንዲመጣ እድሉን አገኘ፡፡ያስመጡት ደጃዝማች ኃይለስላሴ ነበሩ፡፡እርሳቸው ዘመዱ ናቸው፡፡ የሚኖሩት  ካሳንቺስ ነው፡፡ትንሹ ወልዴ ይናገራል ‹‹ያን ጊዜ እድሜዬ 13 ደርሷል፡፡ እኔ ወደ አዲስ አበባ የመጣሁት ለመቆየት ሳይሆን የድቁና ትምህርት ተከታትዬ ወደ ገጠር ለመመለስ ነበር፡፡ደጃዝማች ኃይለስላሴ ግን  ለጊዜው አቆዩኝ፡፡ያን ጊዜ እግራቸውን ታመው በጋሪ ነበር የሚገፉት፡፡የኔም ስራ እርሳቸውን ማጫወት ነበር፡፡

         አማርኛዬ የገጠር በመሆኑ በምናገረው ነገር ሁሉ ያስቃቸው ነበር፡፡ግቢ ውስጥ ካሉት ልጆች ጋር ትግል እንድጋጠም ያደርጉኛል፡፡ ሳሸንፍ ደስ ይላቸዋል፡፡ ሁሌም ከአጠገባቸው እንድለይ አይፈልጉም›› ይላል ፡፡

        ትንሹ ወልዴ አዲስ አበባ ነው የሚገኘው፡፡እናቱም ያለችው እዚሁ ከተማ ነው፡፡ እንዴት ያግኛት!!!፡፡የዘወትር ሀሳቡ ለረጅም አመት ያጣትን እናቱን ማየት ነበር፡፡

    አንድ ቀን ደጃዝማች ወልዴ ወደ ሳሎን ጠሩት ፡፡ወደ ውስጥ ዘልቆ እንደገባ በሶፋው ላይ ሴቶች ተቀምጠዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ተመሳሳይ የሀገር ልብስ ለብሰዋል ፡፡የ13 አመቱ ታዳጊ ወጣት በዛ ያሉት ሴቶች በአንድ ስፍራ ተቀምጠው ሲመለከት እንግዳ ነገር ስለሆነበት ግራ ተጋባ፡፡ደጃዝማች ወደ አጠገባቸው ጠሩትና‹‹ሁሌም ስለ እናትህ ትጠይቀኝ የለ?››አሉት

‹‹አዎ››

‹‹ማግኘት ትፈልጋለህ?››

‹‹በጣም እንጂ››

‹‹እናትህን ታውቃታለህ?››

‹‹ማለት››

‹‹ መልኳ ምን አይነት ነው? ››

‹‹አሁን አላስታውስም››

‹‹  መልኳን ባታውቅም የምታስታውሰው ነገር አለ››

‹‹አዎ››

‹‹ምን››

‹‹እኔ እንጃ ግን....››

                 ወልዴ እናቱን ማግኘት ፈልጓል፡፡እዚህ የመጡት ሴቶች እናቴ ያለችበትን ያውቁ ይሆን? ብሎ አሰበ፡፡ደጃዝማች አጠገባቸው እንዲቆም ነገሩትና ወደ ስምንቱ ሴቶች እንዲመለከት አደረጉት፡፡‹‹እናትህ ከስምንቱ አንዷ ናት፡፡የትኛዋ እንደሆነች ለይተህ ንገረኝ›› አሉት፡፡ወልዴ ደነገጠ፡፡ደግሞም ውስጡ በደስታ ታመሰ፡፡ሲጠብቀው የነበረው  እናቱን የማግኘት ጉጉት እውን ሊሆን ነው፡፡

             እዚህ ቤት ከመጣ ጀምሮ የሚመጡት እንግዶች እናቱ የት እንዳለች እንዲነግሩትና እንዲያሳዩት ቢጠይቅም አንዳቸውም አናውቃትም ስላሉት ሁሌም ግን ፍለጋውን እንደቀጠለ ነበር፡፡ ዛሬ ይሄው እናቱ እርሱ ያለበት ድረስ መጥታለች፡፡ ግን ከስምንቱ ሴቶች እንዴት ለይቶ ይወቃት?፡፡ ደጃዝማች እንደነገሩት‹‹ለይተህ ካላወቅሀት ማግኘት አትችልም ››ስላሉት ተጨነቀ፡፡

           እያንዳንዱን ሴቶች ከእግር አስከራሳቸው ማየት ጀመረ፡፡እናቱ የተለየችው በሶስት አመቱ ነበር፡፡ ያኔ በጥቂቱ ከሚያስታውሰው በስተቀር ያን ያህል መለያ የለውም፡፡ግን በውስጡ የተቀረጸ የሆነ ነገር ነበር ፡፡እናቱን ሲያስብ፡፡እሷ ነች ብሎ ቀርጾ በውስጡ ያስቀመጠው ምስል ነበር፡፡በዚያ ምስል ተረድቶ እርሷ ናት  ብሎ የገመተው  ሴት ላይ ሄዶ ሊጠመጠም ፈለገ፡፡ነገር ግን ይሄን ከማድረጉ በፊት እናቴ ናት ብሎ የሚጠቁማትን ለደጃዘማች ነገሮ ሲረጋገጥ ነው ወደ እናቱ የሚሄደው፡፡

           ሴቶቹን ተመለከተና አነጣጥሮ ወደ አንዷ  ተመለከተ፡፡ከመሀላቸው አንዲቷ ሰረቅ አድርጋ ትመለከተው ነበር፡፡ እርሱም ልቡ ትር ትር ይል ጀመር፡፡ በቃ!! እርሷ ናት ብሎ ደመደመ፡፡፡የትላንቱ ታዳጊ የዛሬው አንጋፋ ሙያተኛ  ዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ሁኔታው አስታውሶ እናቱን እንዴት ፈልጎ እንዳገኘ ይናገራል‹‹ ሶፋው ላይ የተቀመጡት ሴቶች አንዳንዶቹ ቀይ ናቸው ፡፡ሌሎቹ ጠይም ነበሩ፡፡እናቴን ለማግኘት ብፈልግም ግራ ተጋባሁ፡፡

           በኋላ ግን ከመሀላቸው አንዷ ትኩር ብላ አየችኝ፡፡እኔም አፍጥጬ ሳያት አለቀሰች፡፡እናቴ እርሷ ናት ብዬ ሄጄ ተጠመጠምኩባት ፡፡መጠምጠም ብቻ ሳይሆን አለቅም ብዬ እዚያው እንቅ አድርጌ ያዝኳት፡፡ከዚያ ማን ያላቀን?በዚያን ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ሳስታውስው ከእናቴ ተለይቼ ብዙ ጊዜ በመቆየቴ ለረጅም ጊዜ ታምቆ የነበረውን ናፍቆቴን ተጠምጥሜባት አለቀስኩ፡፡አልቅሼ  እንኳን ሊወጣልኝ አልቻለም፡፡ገጠር ትምህርት ቤት እያለሁ ሌሎች ህጻናት ልጆች እናቶቻቸው መጥተው ሲጠይቋቸውና አብረው ሲሄዱ ሳይ በጣም ይሰማኝ ነበር፡፡እናቴን ትልቅ ሆኜ አገኛታለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡.....››ይላሉ

                          ታዳጊው ወልዴና እናቱ ተገናኙ ተቃቀፉ ፤ተሳሳሙ እንደገናም ተቃቀፉ፡ሁለቱም ጋር ያለው ናፍቆት ተመሳሳይ ነበር፡፡  አሁን ሲፈላለጉ የነበሩት እናትና ልጅ ተገናኝተዋል ፡፡ልጅ ከእናቱ መለየት አልፈለገም፡፡ እናትም ልጇን ይዛ ወደ ቤቷ ልትሄድ ተሰናዳች፡፡ወልዴም ጨርቁን ሊያመጣ ወደ ጓዳ ገባ፡፡ደጃዝማች ወደ እናቲቱ እያዩ‹‹ ምንድነው ነገሩ›› አሉ፡፡

‹‹ይዤው ልሄድነው››

‹‹ወደዬት?››

‹‹ወደቤቴ››

‹‹አትወስጅውም››

‹‹እወስደዋለሁ››

‹‹ኃይለስላሴ ይሙት!!!!ማንም ሰው ልጁን ከዚህ ቤት መውሰድ አይችልም ››

ደጃዝማች‹‹ኃይለስላሴ ይሙት!››ካሉ፡ነገሩ ያበቃለት ነው፡፡ምንም የሚሻር ነገር የለውም ወልዴ ይናገራል‹‹ደጃዝማች ከማሉ እንደቆረጡ ስለሚታወቅ እናቴ እርሷ ጋር ይዛኝ ልትሄድ አልቻለችም፡፡እዚያው ጊቢ ውስጥ ብዙ ልጆች ያስተምሩ ስለነበር ከነርሱ ጋር አብሬ እንድሆን ተደረገ፡፡

         አዲስ አበባ ያለው አጎቴ የተማረና ባንክ የሚሰራ ስለነበር እዚያው ግቢ ውስጥ ቄስ ትምህርት ከጨረስኩ በኋላ ዘመናዊ ትምህርት ቤት እንድገባ ተደረገ፡፡የወሰዱኝ ዘነበወርቅ ትምህርት ቤት ነበር፡፡እዚያ ሴቶች ስለሚበዙ ለመግባት ፈቃደኛ አልነበርኩም፡፡ አስታውሳለሁ በአሉ ግርማ እዚያ እየተማረ ነበር፡፡  አስፋው ወሰን ት/ቤት አስመዘገበኝ ከዚያም ቆይቶ ወንድራድ ገባሁ›› ይላል