Newsletter Signup

Sign-up to stay in touch with Saint George FC

Reagent/Protectorator
Yidnekatchew Tessema
Mengistu Worku

St. George Gallery

በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሲሸልሱ ቅዱስ ሚካኤል ይጫወታል

ኢትዮጵያን በመወከል በ2016ቱ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ የሚሳተፈው ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጪው ሳምንት መጨረሻ እሁድ የካቲት 6 ቀን 2008 ዓ.ም ከሲሸየልሱ ቅዱስ ሚካኤል ክለብ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዚህ አህጉራዊ ውድድር ሀገራችን መወከል የቻለው የ2007 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ሻምፒዮን በመሆኑ ነው፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በቅዱስ ሚካኤል ቡድኖች መካከል የሚካሄደው ጨዋታ ቀደም ተብሎ ለሀዋሳ ከተማ በተሰራው አዲሱ የሀዋሳ ስታዲየም ለማካሄድ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ከጥር 25 በፊት ተቀባይ ቡድኖች ለእንግዳው ቡድን የሚጫወትበትን ሜዳ እና ከተማ ማሳወቅ አለበት በሚለው ህግ መሰረት የሀዋሳን ስታዲየም የጎብኙት ኮሚሽነር ለዚህ ቀን መድረስ ባለመቻላቸው ጨዋታው አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ እንዲሆን ተወስኗል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቅዱስ ሚካኤል የሚያደርገውን ጨዋታ የሚመሩት ዳኞች እና የመሰመር ዳኞች ከሶማልያ ናቸው፡፡ ሀሰን መሀመድ ሀጂ ዋና ዳኛ፣ በሺር አብዶ ሱሌይማን እና ሳላህ ኦማር አቡካር ረዳት ዳኞች ሲሆኙ ተጠባባቂ ዳኛ በሺር ኦላድ በመሆን ተመርጠዋል፡፡ ይህንን የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣርያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ደቡብ ሱዳናዊው ማርኮ አብርሃም ላዶ በኮሚሽነርነት የሚመሩት ይሆናል፡፡

ሀሰን ሞሀመድ ሀጂ (የእለቱ ዋና ዳኛ)

በሙሉ የመዝገብ ስማቸው ሀሰን ሞሀመድ ሀጂ ከማል የምታወቁት እና እ.ኤ.አ. በ1988 ሶማልያ ውስጥ የተወለዱት አልቢትር በመጪው ሳምንት የሚካሄደውን የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ሚካኤል ጨዋታ በዋና አልቢትርነት እንዲመሩ በአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ተመድበዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2014 ጀምሮ የፊፋ አለም አቀፍ አልቢትር የሆኑት ሀሰን ሞሀመድ ሀጂ እስከአሁን ድረስ ሰባት ያህል በካፍ እውቅና የሚሰጣቸውን ጨዋታዎች አጫውተዋል፡፡ ከሰባቱ ውስጥም አንዱ እ.ኤ.አ. 2015 ለግሪ ዊልቨስ እና በደደቢት መሀከል የተካሄደውን ጨዋታ መምራታቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያም አዛም ከኤልሜሪክ፣ ያንጋ አፍሪካ ከኮሞሮዛየን ጋር ያደረጓቸውን ጨዋታዎች መምራታቸው ታውቋል፡፡

እኝህ አልቢትር በዋና ዳኝነት በመሩዋቸው ሰባት ጨዋታዎች ውስጥ በአንዱ ብቻ ፍፁም ቅጣት ምት የሰጡ ሲሆን ለባለ ሜዳ ቡድኖች 12 ቢጫ ከሜዳቸው ውጭ ለሚጫወቱ ቡድኖች ደግሞ 11 በአጠቃላይ 23 ቢጫ ካርድ አሳይተዋል፡፡ እስከ አሁን ድረስ ምንም ቀይ ካርድ አልመዘዙም፡፡

ስለአልቢትሩ ቁጥሮች ምን ያሳያሉ

 

በሜዳው

ከሜዳው ውጪ

አጠቃላይ

ፍጹም ቅጣት ምት

1

0

1

ቀይ

0

0

0

ቢጫ

12

11

23

 

በሜዳው

ከሜዳው ውጭ

አጠቃላይ

ፍጹም ቅጣት ምት

0.16%

0.00%

0.48%

ቀይ ካርድ

0.00

0.00%

0.00%

ቢጫ ካርድ

1.71%

1.57%

3.29%

                                                                             

አልቢትር ሀሰን ሞሀመድ ሀጂ በሜዳ            አልቢትር ሀሰን ሞሀመድ ሀጂ በሜዳ እና እና ከሜዳ ውጭ የሚሰጧቸው ፍፁም        ከሜዳ ውጭ የሚሰጧቸው ፍፁም ቅጣት ቅጣት ምትና ቀይና ቢጫ ካርዶች                  ምትና ቀይ ካርድ በፕርሰንት                         በቁጥር

በሽር አህመድ ሱሌይማን ( ረዳት አልቢትር)

የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የቅዱስ ሚካኤል የቅድመ ማጣሪያ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታውን በረዳት ዳኝነት የሚመሩት ሱማሊያዊው ረዳት ዳኛ በሽር አህመድ ሱሌይማን ይባላሉ፡፡ እኚህ አልቢትር የፊፋ ኢንተርናሽናል ረዳት አልቢትር የሆኑት እ.ኤ.አ በ2013 ሲሆን ዘጠኝ ዕውቅና ያላቸውን ጨዋታዎች በረዳት ዳኝነት መርተዋል፡፡

ሳላህ አማር አቡካር (ረዳት አልቢትር)

ሶማልያዊው ሳለህ አሜር አቡበካር ኢንተርናሽል የረዳት ዳኛ በመሆን የተሾሙት እ.ኤ.አ በ2001 ነው፡፡ አልቢትሩ በ2001 የኢንተርናሽል ዳኝነታቸውን ያገኙ እንጂ ከሶማሊያ ቀደምት ከሚባሉት ረዳት አልቢትሮች መካከል ይመደባሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ1975 ሶማሊያ ውስጥ የተወለዱት እኚህ አልቢትር በመጪው ሳምንት የሚደረገውን የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የቅዱስ ሚካኤል ጨዋታን በረዳት ዳኝነት የሚመሩ ይሆናል፡፡

ማርኮ አብርሃም ላይ (ኮሚሽነር)

ይህንን ጨዋታ እንዲታዘቡ ከደቡብ ሱዳን የተመደቡት ማርኮ አብርሃም ነዶ ኢትዮጵያን በደንብ ከሚያውቁት ኮሚሽነሮች ተርታ ይመደባሉ፡፡ የቅርብ ጊዜውን እንኳን ብናነሳ ባህር ዳር ላይ የተከናወነውን እና የኬንያ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ በኮሚሽነርነት የመሩት እኝህ ነበሩ፡፡

ቅዱስ ሚካኤል (st.Michel United FC)

ቅዱስ ሚካኤል ክለብ የሲሸየልስ ክለብ ሲሆን የተመሰረተውም እ.ኤ.አ 1996 ነው፡፡ ከተመሰረተ አጭር የሚባል እድሜ ቢሆንም ዲቪዚዮን የሚባለውን የሲሸልስ ሊግ አስራ ሦስት ጊዜ በማንሳት ሀገራቸውን በአፍሪካው ትልቁ የክለባችን ውድድር መወከል ችለዋል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ቡድን ሲሸየልስ ውስጥ በምትገኘው ከአንሴ አውዝ ፒንስ ግዛትን ወክሎ የሚጫወት ሲሆን የመጨረሻ አፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታውንም ባሳለፍነው አመት በፈረንጆቹ የካቲት ወር ላይ አከናውኖ በድምር ውጤት በደቡብ አፍሪካው ማዋሎዳ ሰንዳውንስ አራት ለአንድ ተሸንፎ ከወድድር ውጭ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ስኬቶችን ካነሳን የሲሸየልስ ሊግን 13 ጊዜ፣ የሲሸየልስ ኤፍ ኤ ካፕን 10 ጊዜ፣ ሲሸየልስ ሊግ ካፕ አምስት ጊዜ፣ ሲሸየልስ ፕሮዝዳንትስ ካፕን አስር ጊዜ ማሸነፍ ችሏል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ክለብ ለጨዋታ የሚጠቅመው ስታዴ ሊንቴ ተብሎ የሚጠራውን 10,000 ተመልካች ማስተናገድ የሚችለውን የሲሽየልስ ስታዲየም ይጠቀማል፡፡ ይህ ስተዲየም ባለ አርተፊሻል ሳር ሲሆን ሣሩ የተተከለላትም እ.ኤ.አ በ2007 ነው፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ እና ቅዱስ ሚካኤል ክለብ በወድድር ደረጃ ሲገናኙ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በመጪው እሁድ የካቲት 6/2008 ዓ.ም ሁለቱ ቡድኖች በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲገናኙ ስታዲየሙ በቡርትካናማው የቅዱስ ጊዮርጊስ መለያ ይደምቃል፡፡