Newsletter Signup

Sign-up to stay in touch with Saint George FC

Reagent/Protectorator
Yidnekatchew Tessema
Mengistu Worku

St. George Gallery

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ዲቻን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ በነገው እለት ከአርባ ምንጭ ከተማ ይጫወታል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከአንድ ወር መቋረጥ በኋላ እንደ አዲስ ተጀምሯል፡፡ ውድድሩ ከመቋረጡ በፊት አንዳንድ ቡድኖች እጅግ በጣም ጥሩ አቋማቸውን ሲያሳዩ አንዳንዶቹ ደግሞ ነጥብ ማግኘት አቅቷቸው ሲዋዥቁ ተስተውሏል፡፡ ፕሪምየር ሊጉ ሩዋንዳ ላይ በተዘጋጀው የቻን አፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ለአንድ ወር ሲቋረጥም በተለይም አቋማቸውን ማስተካከል ለሚፈልጉት ክለቦች ያልታሰበ ሲሳይ ሲሆን በአቋማቸው ጥሩ ለነበሩት ቡድኖች ግን ዱብ እዳ ሆኖባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክለቦች ከዚህ ቀን እስከ እዚህ ቀን የመጀመሪያውን ዙር ጨዋታ ያከናውናሉ ብሎ መርሀ ግብር ለተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ከበተነ በኋላ የጨዋታ ቀን እና ሰአትን መቀያየሩ ልማድ ሆኗል፡፡ በ2008 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን እንኳን ቡድኖች የስምንት ሳምንት መርሀ ግብራቸውን ሳያከናውኑ በተለያዩ ወቅቶች በድምሩ ለ75 ቀናት ያህል ተቋርጧል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ሰባተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ድረስ በሰባት ጨዋታዎች በሰበሰባቸው 16 ነጥቦች አዳማ ከተማን በመከተል የሁለተኛ ደረጃን ይዞ ቆይቷል፡፡በስምንተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የካቲት 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ወላይታ ዲቻን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስት ለዜሮ በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ቢረከብም በማግስቱ በሜዳው ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው አዳማ ከተማ አንድ አቻ በመለያየቱ ወደ ሊጉ መሪነት መመለስ ችሏል፡፡  

አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ በተደረገው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የወላይታ ዲቻ ጨዋታ ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል ሮበርት ኦዶንካራ፤ አንዳርጋቸው ይላቅ፤ መሀሪ መና፤አይዛክ ኢሴንዴ፤ዘካርያስ ቱጂ ፤ ምንተስኖት አዳነ፤አሉላ ግርማ፤ አዳነ ግርማ፤አቡበከር ሳኒ፤ራምኬል ሎክ እና ብራየን ኡሞኒ በአራት ሶስት ሶስት የጨዋታ አሰላለፍ ጨዋታውን መጀመር ችለዋል፡፡

ቡድናችን በጨዋታው የግብ እድሎችን በመፍጠር፤ የተሳኩ ሙከራዎችን በማድረግ እና የባላጋራ ቡድንን የግብ ክልል በተደጋጋሚ በማስጨነቁ በኩል የተሻለ ነበር፡፡ በተለይም በጨዋታው የቡድናችን ዋንኛ የማጥቃት መንገድ መጀመሪያ የሆኑት አቡበከር ሳኒ እና ራምኬል ሎክ ኳስን ወደ ተጋጣሚ ግብ ክልል ይዘው የሚገቡበት መንገድ እጅግ አደገኛ እንደነበር በግልፅና በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡ በአስረኛው ደቂቃ ራምኬል ከግራ መስመር ሰብሮ ወደ ወላይታ ድቻ ግብ ክልል በመግባት ለአዳነ ግርማ ያሻማውና አዳነ ሳይደርስበት የቀረው፤በ27ኛው ደቂቃ ዘካርያስ ቱጂ እና ራምኬል ሎክ አንድ ሁለት ተቀባብለው ለብራየን ኡሞኒ ያቀበሉት እና ብራያን በጭንቅላት መትቶ የወጣበት፤በ36ኛው ደቂቃ ብራየን ከአቡበከር ሳኒ ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ያገኘውንና አንድ ተከላካይ እና የወላይታ ድቻን ግብ ጠባቂ በማለፍ ወደ ግብ መቶ አስቆጠረ ሲባል በተከላካይ ከመስመር የተመለሰው ኳስ ቡድናችን በሁለቱ የመስመር አጥቂዎች ሲጠቀም እንደነበር ማሳያዎች ቢሆኑም ጨዋታው ግብ ማስተናገድ የቻለው በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ነበር፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በወላይታ ዲቻ ጨዋታ የሁለተኛው ግማሽ የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አሰልጣኝ ማርት ኖይ ዘካርያስ ቱጂን አስወጥተው ተስፋዬ አለባቸውን በማስገባት የአሰላለፍ ለውጥ ሲያደርጉ ተጨዋችን በተጨዋች በመለዋወጥ ግብን መፈለግ ጀመሩ፡፡ ማርት ኖይ የተስፋዬ አለባቸውን መግባት ተከትሎ በመሀል አማካይነት ተሰልፎ የቆየው አሉላ ግርማ ወደ ቀድሞ የቀኝ መስመር ተከላካይነት ሚናው እንዲመለስ በተከላካይ አማካይነት ሲሰለፍ የቆየው ምንተስኖት አዳነም ወደ አጥቂዎቹ በመጠጋት እንዲጫወትና ተስፋዬ አለባቸውም በለመደው ሚና ከአራቱ ተከላካዮች ፊት በመቆም ሽፋን እንዲሰጥ አደረጉ፡፡

በለውጡ የማርት ኖዩ ቅዱስ ጊዮርጊስ በተለይም በሁለተኛው ግማሽ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ብልጫን ወሰደ፡፡ በዕለቱ ጨዋታ እጅግ ድንቅ እንቅስቃሴን ሲያደርግ የቆየው ታዳጊው ተጨዋቻችን አቡበከር ሳኒ በወላይታ ዲቻ የግብ በር ግራ መስመር ላይ ያገኛትን ኳስ ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ይዞ ከገባ በኋላ በተሰራበት ጥፋት የተሰጠውን ፍጹም ቅጣት ምት አዳነ ግርማ መትቶ በቀላሉ በማስቆጠር ግብ ጠምቶት የነበረውን ጨዋታ አራሰው፡፡

በግቡ የተነሳሱት የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች በወላይታ ዲቻ ቡድን ላይ ተደጋጋሚ የግብ ሙከራን ማድረግ ቀጠሉ፡፡ በጨዋታው 57ኛው ደቂቃ ላይ አሉላ ግርማ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ተከላካዩ አይዛክ ኢሴንዴ አግኝቶ በጭንቅላት ቢሞክራትም ኳስና መረብን ሳይገናኙ ቀሩ፡፡ ተስፋ ያልቆረጡት የቡድናችን ተጨዋቾች ኳስን በሚገባ በመመስረት ኳስ መሀል ሜዳ ላይ ተስፋዬ አለባቸው ጋር ደርሳለች፤ ተስፋዬ ወደ ግራ ጥላ ፎቅ አድልቶ በሁለት የወላይታ ዲቻ ተጨዋቾች ተይዞ ለሚገኘው አዳነ ግርማ ሰጠው፡፡ አዳነም በሚገርም ሁኔታ ከሁለቱ ተጨዋቾች መሀል ዞሮ ከወጣ በኋላ ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውጭ በግራ እግሩ አክርሮ በመምታት ለራሱም ለክለቡም ሁለተኛውን ግብ አስቆጠረ፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ የአመቱ ምርጥ ግብ የሚመረጥ ቢሆን ቀደም ሲል የቡድናችን ተጨዋቾች የሆኑት አሉላ ግርማ እና በሀይሉ አሰፋ ካስቆጠሩት ግብ ጋር ይህች ግብ ለውድድር ትቀርብ ነበር፡፡

የግቡን መቆጠር ተከትሎ ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ማርት ኖይ ሌላ ግብ ፍለጋ በሚመስል መልኩ ራምኬልን በ74ኛው ደቂቃ አስወጥተው ናትናኤል ዘለቀን ሲያስገቡ የጨዋታው ኮከብ የነበረው አቡበከር ሳኒም በዳዋ ሁጤሳ ተቀይሮ ወጥቷል፡፡ ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 2ለ0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ ተብሎ የአልቢትሩ ፊሽካ በሚጠበቅበት ሰአትም ብራየን ኡሞኒ ከአሉላ ግርማ የተሻማለትንና በአዳነ ግርማ የተዘጋጀለትን ኳስ በመጠቀም አንድ ግብ አክሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ዲቻን ሶስት ለዜሮ እንዲያሸንፍ አድረገ፡፡

በጨዋታው በዛ ያሉ ጥሩ የሚባሉ ክስተቶች ተከስተዋል፡፡ በተለይም በዚህ ጨዋታ በቡድናችን በተለያየ ጊዜያት በሲ እና በቢ ቡድን ውስጥ አልፈው ዋናው ቡድናችን ውስጥ በመጫወት ላይ ከሚገኙት ተጨዋቾቻችን መሀከል ስድስቱን( አንዳርጋቸው ይላቅ፤ ዘካርያስ ቱጂ፤ አሉላ ግርማ፤ ምንተስኖት አዳነ፤ ናትናኤል ዘለቀ እና አቡበከር ሳኒ) አሰልጣኙ ማሰለፋቸው በወጣቶች ላይ ያላቸውን እምነት ያሳያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ከሚያውቁት ቦታ ተቀይረው እየተጫወቱ ካሉት ተጫዎቾች ውስጥ በተለይም መሀሪ መና የወዳጅነት ጨዋታዎችን ጨምሮ በሊጉ ጨዋታ ላይ ያሳየው ብቃት አሰልጣኙ በተከላካይ ስፍራ አማራጭ እንዲኖራቸው ማድረግ ችሏል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በየ አመቱ ቢያንስ አንድ አዲስ ታዳጊ ለሊጉ በማበርከት ይታወቃል፡፡ ልምዱም አድርጎታል፡፡ ካሳለፍነው አመት እንኳን ብንጀምር ዘካርያስ ቱጂን ያስተዋወቀው ቅዱስ ጊዪርጊስ በዘንድሮው አመት ደግሞ አይደክሜውን አቡበከር ሳኒን ለሊጉ አበርክቷል፡፡ ዘካርያስ ወደ ዋናው ቡድን በተቀላቀለ የመጀመሪያው አመት ከ20 በላይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ተራው የአቡበከር ሳኒ ይመስላል……. በቀጣዩ አመትስ ?????

በነገው ጨዋታም አሰልጣኝ ማርት ኖይ ባሳለፍነው ሳምንት የነበረው ጨዋታ ላይ የተጠቀሟቸውን ተጨዋቾች በተወሰነ መልኩ እንደሚቀይሩ ፍንጭ የሰጡ ሲሆን በአብዛኛው ግን ያንኑ አሰላለፍ ሊከተሉ እንደሚችሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ጨዋታው በነገው እለት ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ላይ አርባ ምንጭ ከተማ ላይ የሚካሄድ ሲሆን የፌስ ቡክ አድራሻ ያላችሁ ደጋፊዎችም ጨዋታውን St George በሚለው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ኦፊሻል የፌስ ቡክ አካውንት ላይ መከታተል ትችላላችሁ፡፡