የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ከዳሽን ባንክና ከአሞሌ ጋር የአዲስ አበባ ስታዲየምን የመግቢያ ቲኬት አሻሻጥ
በኢንተርኔት አማካኝነት ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል፡፡የስፖርት ማህበራችን የቲኬት ሽያጭ
ኮሚቴ እና ከስቲዋርድ ኮሚቴ አባላት ከአሞሌ ባለሙያዎች ጋር በዛሬው እለት ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል፡፡
በቲኬት አሻሻጡ ወቅት ሊያጋጥሙ በሚችሉ እንከኖችና ተያያዥ ጉዳች ላይ በተከታታይ ተገናኝተው ለመወያየትም
ተስማምተዋል፡፡
ስለሆነም የፊታችን ማክሰኞ ታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ዐ.ም በአዲስ አበባ ስታየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሰበታ
ከተማ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ለመመልከት ዛሬ ህዳር 26 ቀን 2012 ከዚህ ሠዓት ጀምሮ በዳሽን ባንክ ሁሉም
ቅርንጫፎች የስታዲየም መግቢያ ቲኬቶቻችሁን በቀላሉ መግዛት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡
የስፖርት ማህበራችን ወደፊትም ቲኬቶችን ለደጋፊዎቻችን በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ እንዲረዳው በኢትዮጵያ ፖስታ
አገልግሎት ድርጅትና በሸዋ ሱፐር ማርኬት ቅርንጫፎች በኩል ሽያጩን ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እያከናወነ
ሲሆን ሂደቱ እንደተጠናቀቀ ይፋ የምናደርግ ይሆናል፡፡ከዚህ በሁዋላ የስታዲየም መግቢያ ቲኬቶች ፈጽሞ የእጅ በእጅ
ሽያጭ አይከናወንም፡፡
በዚሁ አጋጣሚ ለመላው ደጋፊዎቻችን ጨዋታዎችን ለመከታተል ቲኬት ስትገዙ መግባት የምትችሉት በቆረጣችሁበት
ቦታ/ለምሳሌ ከማን አንሼ ከሆነ መግባት የምትችሉት በዚሁ ቦታ ብቻ/መሆኑን አክብሮት እንገልፃለን፡፡
