0
Items : 0
Subtotal : 0.00Br
View CartCheck Out

The 14th edition of the Addis Ababa City Cup Football Federation has been voted the All-Star Player, Coach of the Year

በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በተካሄደው ስነ- ስርዓት የፈረሰኞቹ የፊት አጥቂ ሳላሀዲን ሰኢድ የወድድሩ ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን ተመርጧል፡ሳላሀዲን ዋንጫ፣ የምስክር ወረቀትና የ60ሺ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡የወድድሩ ኮከብ አስልጣኝ ሆኖ የተመረጠውም የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ዚቮዥኖቭ ሰርዣን ሲሆን የምስክር ወረቀትና 75 ሺ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ሳላሀዲን በወልቂጤ ከነማ ላይ ያስቆጠራት ጎል የውድድሩ ምርጥ ጎል ተብላለች፣ሳላ የ10ሺ ብር ተጨማሪ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ የተመረጠው ደግሞ የኢትዮጵያ ቡናው ተከላካይ ፈቱዲን ጀማል ሲሆን የ65 ሺህ ብር እንዲሁም ዋንጫና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል፡፡
ለሁለት ሳምንታት በቆየው 14ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በአጠቃላይ 8 ቡድኖች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን 33 ጎሎችም መርብ ላይ አርፈዋል፡፡
ታላቁ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ለ12 ጊዜ ተሳትፎ ለስድስት ጊዜ ዋንጫ አንስቷል፡፡
ለመላው ለቅዱስ ጊዮርጊሳዊያን እንኳን ደስ አለን !!

Leave a Reply

Our Shop

Cart