የስፖርት ማህበራችን ከውጭ አገር በትእዛዝ ያሰራቸውንና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን 7 ሺ200 አዳዲስ ማልያዎች በዛሬው እለት ተረክቧል፡፡
ስለሆነም መላው የክለባችን ደጋፊዎች ከፊታችን ህዳር 29 እለተ ሰኞ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ አዳዲሶቹን ማልያዎች በጽህፈት ቤታችን በመምጣት በ400 ብር ብቻ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
በተጨማሪም ከ7ሺ 800 በላይ
አዳዲስ ማልያዎችም ወደ አገር ውስጥ የገቡ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የጉምሩክ ሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡
በዚህ አጋጣሚ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በክለባችን አርማና መለያ የታተሙ ማልያዎች በገበያ ላይ እየተሸጡ እንደሆነ በሰነድና በፎቶግራፍ የተደገፉ መረጃዎች ደርሰውናል፡፡ከዚህ ቀደም በዚህ ህገ ወጥ ድርጊት የተሳተፉ ግለሰቦች ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ የሰጠናቸው ቢሆንም ከአሉታዊ ተግባራቸው ሊቆጠቡ ስላልቻሉ የስፖርት ማህበራችን ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ውሳኔ ላይ የደረሰ መሆኑን እየገለጽን ትክክለኛው የማልያ ሽያጭ የሚከናወነው በጽህፈት ቤታችን ብቻ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ
የተከበራችሁ ቤተሰቦቻችን ህገወጥ መለያዎች ሽያጭ ሲያጋጥማችሁ ለስፖርት ማህበራችን በመጠቆም የአባልነት ግዴታችሁን እንድትወጡ በአክብሮት እንጠይቃለን ።

