#ፈረሰኞቹ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫን ለስድስተኛ ጊዜ አነሱ
ከሰበታ ከተማ ጋር ለፍፃሜ የደረሱት ፈረሰኞቹ 2 ለ1 በሆነ ዉጤት በመርታት ነው ዋንጫውን ያነሱት።
ዋንጫውን ምንተስኖት አዳነ ከእለቱ የክብር እንግዳ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተቀብሏል።ኢንጅነር ታከለ ለተጫዋቾቻችንም የሜዳሊያ ሽልማት አበርክተዋል።
ተጫዋቾቻችን ከጨዋታው ፍፃሜ በኃላ ስታዲየሙን በመዞር ከደጋፊዎቻችን ጋር ደስታቸውን ተጋርተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ለ12 ጊዚያት ያህል የተሳተፈው ክለባችን የዘንድሮውን ጨምሮ ለ6 ጊዜ ዋንጫ ያነሳ ሲሆን ለ2 ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች በውድድሩ አልተሳተፈም።
የእለቱ ኮከብ ተጫዋች የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተጫዋች
ያአብሰራ ተስፋዬ ሆኗል።

