የክለባችን ተከላካይ አማካይ ተጫዋች የሆነው ሀይደር ሸረፋ በ14ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ሜዳ ላይ ባሳየው ያልተገባ ባህሪ መላውን እግር ኳስ አፍቃሪ ህዝብ ይቅርታ ጠየቀ።
ተጫዋቹ ትናንት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበረው ጨዋታ ላይ ተቀይሮ ከገባ ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ከቡናው ተጫዋች በተሰነዘረበት አስነዋሪ ስድብ ራሱን መቆጣጠር ባለመቻሉ ድርጊቱን በመፈፀሙ መላውን የስፖርት ቤተሰብ ከልቡ ይቅርታ ጠይቋል።
ሀይደር በእለቱ በመሀል ዳኛው ውሳኔ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል ።
