0
Items : 0
Subtotal : 0.00Br
View CartCheck Out

የፍቅር ለቅዱስ ጊዮርጊስ የዋትሰአፕ ግሩፕ አባላት ለበጎ አድራጎት ተግባር ያሰባሰቡትን ገንዘብ ገቢ አደረጉ፡፡

ፍቅር ለቅዱስ ጊዮርጊስ የዋትሰአፕ ግሩፕ አባላት በ2012ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንዲውል ከአባላቱ ያሰባሰቡትን 41ሺ 50 ብር ለጽህፈት ቤታችን ገቢ አደረጉ፡፡
አባላቱ እርስ በርሳቸው የማህበራዊ ትስስር መረብን በመጠቀም ቡድን ያቋቋሙ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ይታወቃሉ፡፡
የስፖርት ማኅበራችን ከአባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር በመተባበር በዘንድሮው ዓመት የትምህርት ዘመን በሺዎች የሚቆጠሩ የመማሪያ ደብተሮችን በክለቡ አርማና መለያ አሳትሞ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለማከፋፈል እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡
የስፖርት ማህበራችን ደብተሮችን ለማሰባሰብ የጀመረውን ዘመቻ የፍቅር ለቅዱስ ጊዮርጊስ የዋትሰአፕ ግሩፕ አባላት በመደገፍ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋናውን አቅርቦ የመማሪያ ደብተሮቹ በቅርቡ ለተማሪዎቹ እንደሚከፋፈል አስታወቋል፡፡

Leave a Reply

Our Shop

Cart